Art of motivation


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Other


Public channel
Always be positive
Be self motivated

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Other
Statistics
Posts filter




ኦሜጋ ምግብ ቤት ይርጋለም

አርፍ ምግብ አለ ከኛ ጋ








Happy new Ethiopian year


የአሁኗ ቅፅበት የመጨረሻ የሕይወት ጊዜህ ልትሆን እንደምትችል ማሰብ አያስፈራም?

🟡ሁሌም ሌላ ዕድል ሲሰጥህ ይህንን በአእምሮህ ውስጥ አስገባ፣ ሁሉም ነገር እንደገና ላይመጣ ይችላልና ፣ምክንያቱም ሕይወት ሁልጊዜ ሁለተኛ ዕድል አትሰጥም ፣ በየጊዜው የሚመጡትን ዕድሎች እንደ ቀላል አድርገህ መውሰድ የለብህም።

🔴አሁን የሚታየውን ነገር ሁሉ ለመጨረሻ ጊዜ እያየህ እንደሆነ በማሰብ ከልብ ነገሮችን ተመልከት ፣ ሁል ጊዜ እያንዳንዱን ደቂቃ በማስተዋል እንዲቆጥር ማድረግ አስፈላጊ ነው ፡፡
ሕይወት አጭር ናትና

🟢አንድ ቀን ደስታ ቤቴ ይገባል ብለህ ደስታህን አትግፋ፣ ዛሬ ደስተኛ የምትሆንበት አንድ ነገር ይኖራል። የአሁኑን ደቂቃ በጥልቀት መመልከት ከቻልክ ሁል ጊዜም የሚያስደስት ነገር አታጣም ፡፡

🟡ደስታ የችግሮች መቅረት አይደለም ፣ ግን በችግሮች መካከልም እንኳን የምስጋና መኖር ነው ፡፡ሁልጊዜ ደስተኛ ለመሆን ሊኖርህ የሚገባው አመለካከት ይህ ነው፣ አሁን ባለህ ነገር ደስተኛ ሁን ፣ቅፅበትህ የምታመጣውን የተትረፈረፈ ደስታ አጣጥም፡፡

🔴ባለህበት ደስተኛ ካልሆንክ ወደ ምትሄድበት ስትደርስም ደስተኛ አትሆንም ፡፡ሕይወት አጭር ናት ፣ ለዘላለም አትኖርም ፣ ስለዚህ አሁን ደስተኛ ሁን ፡፡




Remind yourself every day:

" I am in charge of my happiness. I will not let anything outside of my self control me. I am creating a life that feels good on the inside and it will turn into experiences that are good on the outside."


🔑ሶስቱ በፍጹም ልታፍሩባቸው የማይገባችሁ ነገሮች

1. በተፈጥሮ ባገኛችሁት ማንነታችሁ በፍጹም አትፈሩ! ዘራችሁ፣ ቋንቋችሁ፣ መልካችሁ፣ ቁመናችሁ፣ የተፈጥሮ ዝንባሌያችሁ፣ አእምሯችሁ ለመገንዘብ የሚቀናውና የማይቀናው . . . እና መሰል በፈጣሪ ምርጫ የተሰጧችሁ ነገሮች በፍጹም አያሳፍሩም፡፡ ማንነታችሁን ተቀበሉና ቀና ብላችሁ ኑሩ፡፡ እነዚህን ነገሮች ባለመሸሸግ ማንም ሰው አወቀውም ሆነ አላወቀው፣ እንዲሁም ደግሞ ማንም ሰው ምንም አለና አሰበ ምንም አይነት ስሜት የማይሰጣችሁ ደረጃ እስከምትደርሱ ድረስ በራሳችሁ ላይ ስሩ፡፡

2. በየእለቱ በሚሰማችሁ ስሜት በፍጹም አትፈሩ፡፡ስሜት ሁሉ ወደ ትክክለኛ ተግባር እንደማይወስድ የማወቃችንና ስሜትን ተከትሎ ለምናደርጋቸው ነገሮች የመጠንቀቃችን እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚሰማን ስሜት ግን ልንሸማቀቅና ልናፍር አይገባም፡፡ የኃዘን ስሜት፣ የፍርሃት ስሜት፣ ግራ የመጋባት ስሜት፣ የመጸጸት ስሜትና የመሳሰሉት ስሜቶች ሰው የመሆናችንና በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የማለፋችን ማስረጃ ናቸው እንጂ በፍጹም ልናፍርባቸው የሚገቡ ነገሮች አይደሉም፡፡ ስለዚህ፣ የሚሰማችሁን ስሜት ሳትደባብቁና ሳታምቁ በትክክለኛው ቦታ፣ ጊዜና መጠን የመግለጥን ነጻነት ለራሳችሁ ስጡ፡፡

3. በኑሮአችሁ ደረጃ በፍጹም አትፈሩ፡፡
ከገንዘብ፣ ከቁሳቁስና ከመሳሰሉት እዚህ ምድር ላይ ለቃቅመናቸው በመጨረሻም እዚሁ ጥለናቸው በምንሄዳቸው ነገሮች ላይ የተመሰረተ የማንነትን ዋጋ ተመን በራሳችሁ ላይ ላለማውጣት የምትችሉትን አድርጉ፡፡ ያላችሁበትን የኑሮ ደረጃ ሰዎች አወቁትም ሆነ አላወቁት በስሜታችሁና በስነ-ልቦናችሁ ላይ ምንም አይነት ለውጥ እስከማያመጣ ድረስ ምልከታችሁን ለመቃኘት ሞክሩ፡፡

❤️ሁላችንም ብንሆን ሊያሳፍረን የሚገባን ነገር የክፉ ባህሪያችን ጉዳይ፣ ሊያኮራን የሚገባን ነገር ደግሞ በማንነታችንና በአቅማችን የሰራነው መልካም ተግባር ጉዳይ መሆኑን የማስታወስ ውሎ ይሁንልን!

✍ዶ/ር እዮብ ማሞ


ዕድሜህ ካለፈ በኋላ ያሳለፍከውን መለስ ብለህ ስታስብ ካደረካቸው ይበልጥ ያላደረካቸው ይቆጩሀል፣ 'ምናለ ሞክሬው ቢሆን አድርጌው ቢሆን ኖሮ' ትላለህ፤ እንዳትል ግን አሁን የምትቸለውን ሁሉ ሞክር እና ማን እንደሆንክ ለራስ አሳየው! አለዛ ቁጭት ነው ትርፍህ


ታላቅ


ሰዉ


Sugar & Salt may be mixed together, but ants reject the salt and carry away only sugar.

So select the right people in life and make your life sweeter...

Two simple lines:
Don't make any close relation without full understanding
And don't break any close relation with small misunderstanding!


Just 20 minutes of exercise three days a week will increase your happiness by around 10 to 20%


Martin Luther king says that
" not everybody can be famous, but everybody can be great because greatness determined by service "

Service make you a famous and success
@skbbepositivethinker


You can't be attached to a living thing like the running waters of a river or the moving mind. A living thing is a moving and changing thing; how can you be attached to it? You may have a feeling for a living thing,but you cannot be attached to a river which
is a moving thing.

🌊እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ

💦ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች።ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል።ጊዜው ሲደርስም ይጎላል

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው

💧ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል ገላችን፣ አእምሮአችን ይታመማል እንረበሻለን፣ እንጨነቃለን።

ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው

🌊ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል።ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ። መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው

💦የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ።ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ እንደሚለወጥ ስለማውቅ!

🌊'የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ ' ሲሉ አዛውንት 'ዝናቡን ፍራው ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው።ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው። አይመስልህም እንዴ?''


እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን 🙏🏾 ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ::
መልካም በአል።

Art of motivation wishesh a wonderful easter celebration for y'all Christians celebrating today.
@skbbepositivethinker


ነብሴን ጨፈለ‘ኳት ~ ስጋዬ አስገድዶኝ
ለኔ ብሎ ሲሞት ~ ለእርሱ መኖር ከብዶኝ
===||===



20 last posts shown.

59

subscribers
Channel statistics