🇳🇬 የናይጄሪያ ሕዝብ ቁጥር በጎርጎሮሳውያኑ 2050፣ 450 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ሪፖርት ገለጸ
"በየዓመቱ ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጋ ሰው በህዝባችን ላይ ጭማሪ አለ። ስለዚህ ይህንን ስትመለከት ብዙ ችግር እንደሚገጥመን ታወቃለህ" ሲሉ የስምንተኛው የናይጄሪያ የቤተሰብ እቅድ ኮንፈረንስ የአስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ኢጂኬ ኦጂ ከዝግጅቱ አስቀድመው ለመገናኛ ብዙሃን መናገራቸውን የሀገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል።
ይሁን እንጂ ኢጂኬ በአገሪቱ ውስጥ የወሊድ መጠን ከ5.3 በመቶ ወደ 4.8 በመቶ መቀነሱን ገልፀዋል።
በተመሳሳይ ጊዜ በሰሜን፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ማዕከል የ2030 የቤተሰብ እቅድ አጋርነት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ማርቲን ሚጉምባኖ በናይጄሪያ ያሉ ሴቶች ልጆችን በመውለድ እና በማሳደግ ረገድ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል ብለዋል።
"ነገር ግን ዋናው አንዲት ሴት የቤተሰብ እቅድ እንዴት ማግኘት ትችላለች ነው? ሸቀጦችን? የሕዝቡን ትምህርት በተመለከተስ? ስለዚህ ሁሉም አጋሮች ያስፈልጉናል። በጋራ የሚሰራበት መንገድ መኖር አለበት። እናም እንደገና ከሁለት ዓመት በኋላ ተመልሰን መጥተን ለውጦች አሉ ወይስ የሉም ወይስ ቆመናል የሚለውን እንገመግማለን፤ " ሲሉ መግለጻቸውን ጋዜጣው ጠቅሶ ዘግቧል።
ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ
👉 ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia