🇷🇺 💰 ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር የነበረው የሩብል የገንዘብ ለውጥ ባለፈው መስከረም 72.1ፐርሰንት የሆነ አዲስ ሪከርድ አስመዘገበ እንደ ሩሲያ ማእከላዊ ባንክ ገለፃ
የፍይናንስ አስተዳደር ቢሮው እንዳስረዳው በተመሳሳይ ወር ሩሲያ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባችው እና በሩሲያ ሩብልስ የከፈለ የውጭ ሀገር ምርት እና አገልግሎት 48.5 ፐርሰንት የሆነ ሪከርድ አስመዝግቧል። ከዚህ በፊት ከፍተኛው የተመዘገበው ባለፈዉ ሀምሌ እንደነበር ድርጅቱ አክሏል።
ማእከላዊ ባንኩ እንዳለው ሩሲያ አጋር ከሆኑ የአፍሪካ ፣ የኢሲያ እና ደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጋር ባላት የገንዘብ ልውጥጥ ዶላር እና ዩሮን መጠቀምን እየቀነሰች ነው ብሏል። እነዚህን ገንዘቦች በመጠቀም ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች እና አገልግሎት የሚደረግ ክፍያ የገንዘብ ልውውጥ ወደ 18.4 ፐርሰንት ዝቅ ብሏል።
ሩሲያ ሲሪየስ ውስጥ በህዳር 9-10 በተደረገው የ #ሩሲያአፍሪካ ሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ወቅት በወጣው የጋራ መግለጫ ፤ ተሳታፊዎቹ ለጋራ ንግድ እና የገንዘብ ክፍያዎች የየሀገራቱን ገንዘብ ለልውውጡ መጠቀምን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥተውበት ነበር።
ለብሪክስ አባል ሀገራት የሚሆን የጋራ ገንዘብ መኖርን አስመልክቶም ውይይት ተደርጎ ነበር። ይሁን እንጂ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከህዳር 4-7 በቫልዳ አለምአቀፍ ስብሰባ ወቅት ስለ ብሪክስ የጋራ ገንዘብ ለማውራት ጊዜው ገና እንደሆነ እና ይሄንን አሰመልክቶ የተቀመጠ ግብ የለም ብለዋል።
ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ
👉 ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia