🇪🇹🇰🇪 የኢትዮጵያ እና ኬንያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ትብብራቸውን ማጎልበት በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ ተወያዩ
በኬንያ መከላከያ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ ጀነራል ቻርልስ ካሃሪሪ የተመራ የኬንያ ወታደራዊ የልዑካን ቡድን፤ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል።
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላቸው ያነሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለመቀጠል ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አያይዘውም፤ ኬንያ እና ኢትዮጵያ አልሸባብን በመዋጋት እና በሌሎች የሰላም እና የጸጥታ ዘርፎች፤ ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጅት እያጠናቀቁ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥ ጀነራል ቻርልስ ካሃሪሪ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በቀጠናው ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ ያላቸውን ሚና አንስተዋል።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia