🇰🇪 የኬንያ ባለሥልጣናት የግራሚ ሽልማትን ለማስተናገድ አቅደዋል መባሉን አስተባበሉ
💵 ቀደም ሲል የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ኬንያ ለግራሚ 500 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ (3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር) እንደከፈለች ገልፀው ነበር፤ ይህንን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የግራሚ ሽልማትን ለማስተናገድ የቀረበ እንደሆነ አድርገው ገልፀዋል። ይህም ባለስልጣናቱ የሚቀድመውን አላስቀደሙም በሚል ክስ ባቀረቡ ኬንያውያን ዘንድ ትችት አስነስቷል።
💬 "የወጣቶች ጉዳይ፣ የፈጠራ ኢኮኖሚ እና ስፖርት ሚኒስቴር እና የግራሚ ግሎባል ቬንቸርስ በጎርጎሮሳውያኑ መስከረም 25 ,2023 ስምምነት ተፈራርመዋል። በዚህም ሁለቱ አካላት አፍሪካ አካዳሚ ዋና መሥሪያ ቤት ወይም ማዕከል በኬንያ እንዲቋቋም ተስማምተዋል" ሲል ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
🇳🇬🇿🇦🇷🇼 ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሩዋንዳ የድርጅቱ የአፍሪካ ዋና መስሪያ ቤት መቀመጫ ለመሆን እየተወዳዳሩ ነው። ሚኒስቴሩ የአፍሪካ አካዳሚ በኬንያ ከተቋቋመ የሀገሪቱን ሙዚቀኞች ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኙ ይረዳቸዋል ብሎ ያምናል።
የአፍሪካ አካዳሚ ፕሮጀክት እንዲተገበር ቢያንስ ሁለት መስራች አባላት እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ማድረግ አለባቸው። በመግለጫው እንደተገለጸው ከሆነ ይህንን የተዋጣ ገንዘብ በአንድ አፍሪካዊ ሀገር የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን ለማካሄድ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia