🇳🇪 ኒጀር የሪቨር ብላይንድነስ በሽታን ስርጭት ያቆመች የመጀመሪያዋ የአፍሪካ አገር ሆነች
ይህ ስኬት ኒጀር በዓለም አቀፍ ደረጃ አምስተኛዋ የኦንኮሰርሲያሲስ የጥገኛ ትላትሎችን በሽታ ስርጭትን ያስወገደች ሀገር አድርጓታል፤ ለዚህም ስኬት የአለም ጤና ድርጅት በትላንትናው ዕለት አድናቆቱን ገልጿል።
🗣 " ኒጀር በጣም ድሃ በሆኑ ሰዎች ላይ ብዙ ስቃይን ከሚያስከትለው ከዚህ በሽታ ነፃ ለማውጣት ላሳየችው ቁርጠኝነት እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ " ሲሉ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ ገልጸው ይህ ስኬት "የማይታክት ቁርጠኝነት ይጠይቃል" ብለዋል።
ቴድሮስ የኒጀርን ስኬት ከዓለም ሁለተኛው ከፍተኛ አይነ ስውርነት አምጪ የሆነውን ሪቨር ብላይንድነስ ማስወገድ እንደሚቻል እንደ ማረጋገጫ አድርገው በማድነቅ ለተጎዱ ሌሎች ሀገሮች ተስፋ ይሰጣል ሲሉ ገልጸዋል።
በወንዝ አካባቢዎች በሚገኙ ጥቁር ዝንቦች የሚተላለፈው ይህ በሽታ በዋነኝነት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ፣ የመንና በላቲን አሜሪካ ክፍሎች የሚገኙ የገጠር ነዋሪዎችን ያጠቃል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia