አንድ ሙስሊም ይህን ካደረገ በኃላ ፆምም ይሁን ሌሎች የፈጣሪ ትእዛዛት ውስጥ የሚገኙ መለኮታዊ ጥበቦችንና ሚስጥራትን ለማወቅ ጥረት ቢያደርግ ምንም ከልካይ የለም ።
ሁሉም የአሏህ ህግጋት ለባሪያዎቹ የሚበጁ ጥበቦች፣ ሚስጥራትና ጥቅሞች ላይ እንደተመሰረቱ ምንም ጥርጥር የለውም ነገር ግን ባሮቹ ይህን ማወቃቸው መስፈርት አይደለም ።
👉 የረመዷን ፆምም የራሱ የሆኑ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ፡ ከፊል ጥቅሞቹን ሙስሊም የሆነ ሰው ሊደርስባቸው ይችላል ፡ ከጥቅሞቹ መካከል :-
1/ ከፆም ባህሪ መካከል የሙስሊምን ልብ የአሏህ ቁጥጥር ( ሙራቀባ) አለብኝ ብሎ እንዲነቃ ማድረግ ነው ፡ ይህም አንድ ፆመኛ የሆነ ሰው ትንሽ የቀኑን ክፍለ ጊዜ እምደገፋ የረሀብ ስሜት ይሰማዋል ፡ ነፍሱ ወደ ምግብና መጠጥ ትጓጓለች ፡ ነገር ግን ፆመኛ እንደሆነ ማሰቡ የአሏህን ትእዛዝ ለመጠበቅ ሲል ይህን ፍላጎቱን እንዳያሳካ ያግደዋል ፡ በዚህ ግብግብ መሀከል ልቡ ይነቃል ፣ አሏህ እየተቆጣጠረኝ ነው የሚለው ስሜት እያደገ ይመጣል ፡ የአሏህን ጌትነትና የስልጣኑን ታላቅነት ከማስታወስ ፡ እርሱ ( ፆመኛው ) ደግሞ ለአሏህ ትእዛዝ የተዋረደና ለአሏህ ፍላጎት እጅ የሰጠ ባሪያ መሆኑን ከማስታወስ አይወገድም ።
2) ረመዷን ከአመቱ ወራቶች መካከል የተቀደሰ ወር ነው ፡ ባሮች ይህን ወር ወደ አሏህ በሚያቃርቡ ተግባራትና አምልኮዎች እንዲያሳልፋት አሏህ ይፈልጋል ፡ የላቁ የባርነት መገለጫዎችንም እንዲላበሱ ይፈልጋል። ይህ ደግሞ በምግብ ማእዶችና በመጠጥ ስብስቦች በመገኘት ብቻ ሊገኝ አይችልም ።
3) የጥጋብ ስሜት(ሁኔታ ) በሙስሊም ህይወት ውሰጥ መቀጠሉ ስሜቱን ጭካኔን በሚያስከትሉ ምክንያቶች ሊሞላው እና በነፍሱ ውስጥ የጭቆና ምክንያቶችን ሊያዳብር ይችላል ፡ እኚህ ሁለቱም ባህሪያት ደግሞ ከሙስሊም ባህሪ ጋር የማይጣጣሙ ናቸው። ስለዚህ የፆም ህግ የሙስሊሙን ነፍስ የማግራትና ስሜቱን የማለዘብ ጥበብን ይዟል።
4) ኢስላማዊ ማህበረሰብ ከተመሰረተባቸው መሰረታዊ መርሆች አንዱ የሙስሊሞች መተዛዘን እና ርህራሄ ነው። ባለፀጋ የሆነ ሰው የድህነት ስቃይና አስከፊነት፣ የረሃብ ምሬትና ጭካኔ ሳይሰማው ለድሆች ልባዊ ርኅራኄ ማሳየት አይቻለውም።
ባለፀጎች የድሆች ስሜት እንዲሰማቸውና በሥቃያቸውና በእጦት አብረው እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው የጾም ወር ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው። ስለዚህ ጾም በሀብታሞች ነፍስ ውስጥ የርኅራኄ፣ የምሕረትና የመጽናናት መነሳሳትን ለመቀስቀስ ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው።
✍ዘ.ሐ& አብዱል ፈቂር