የረመዳን ወር መግባት የሚረጋገጥባቸዉ መንገዶች
የረመዳን ወር መግባት በሁለት ነገራቶች ይረጋገጣል።
1) የሻእባን ወር ሰላሳኛዉ ለሊት ( በነጋታዉ 30ኛው ሻእባን ሊሆንባት የምትችለዋ ምሽት ) ላይ ጨረቃ መታየት ።
ይህም አዲል የሆነ መስካሪ ቃዲ ፊት ቀርቦ ጨረቃን በእርግጥ እንደተመለከተ ሲመሰክር ነው።
2) የሻእባን ወር ሰላሳ ቀን የሞላ እንደሆነ ።
ይህም በደመና ምክንያት ጨረቃን ማየት ያስቸገረ ወይም ጨረቃን እንደተመለከተ የሚመስክር አዲል የሆነ ሰው ያልተገኘ እንደሆነ ሻእባንን ሰላሳ ቀን እንሞላለን ። ይህን የሚቃረን ነገር እስካልመጣ ድረስ መሰረቱ ይህ (ሻእባን ሰላሳ ቀን መሙላቱ) ስለሆነ ።
የነዚህ የሁለቱ ነገራቶች ማስረጃቸው :
1/ ነቢዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል :-
❝ጨረቃን አይታችሁ ፁሙ፤ እርሷኑ አይታችሁ ፆማችሁን ፍቱ ፤ ደመና ከሸፈናችሁ ሻእባንን ሰላሳ ቀን ሙሉ❞።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
2/ ኢብኑ አባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት ፦አንድ የገጠር ሰው ወደ አሏህ መልክተኛﷺ መጣና እንዲህ አላቸው ❝እኔ የጨረቃን የመጀመሪያ ውልደት ( መውጣት) ተመለከትኩ❞ አላቸው።
እርሳቸውም❝ላኢላሀ ኢለላህ❞ ብለሀል አሉት ?
❝ አው❞አላቸው።
እርሳቸውም፡❝የአሏህ መልክተኛ መሆኔን ትመሰክራለህ?❞ አሉት። አዎ አላቸው ፣ እርሳቸዉም : ❝ ቢላል ሆይ ! ሰዎችን ተጣራ ነገ ይፁሙ❞ አሉ።
ኢብኑ ሂባን ሰሂህ ነው ብለዉታል።
⭕️የፀሀይ መውጫ ልዩነቶችን ከግምት ውስጥ ማስገባት
አንድ ሀገር ላይ ጨረቃ ከታየ ቅርብ የሆኑ አካባቢዎችም ላይ መፆም ግዴታ ይሆንባቸዋል። ምክንያቱም ቅርብ የሆኑ እንደ ዲመሽቅ ፣ ሂምስ፣ ሀለብ ያሉ ከተማዎች እንደ አንድ ሀገር ነው የሚቆጠሩት ።ሩቅ የሆኑ ከተማዎች እንደ ዲመሽቅ ፣ቃሂራ እና መካ ያሉት እንደ አንድ ሀገር አይቆጠሩም ስለዚህ በአንዱ ሀገር ቢታይ በሌላው ሀገር ላይ ግዴታ አይሆንም።
⭕️ርቀቱ የሚታየው በፀሀይ መውጫ መለያየት ነው
ኩረይብ እንዳስተላለፈው ❝ ሻም እያለሁ ሰይዱና ዐልይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ረመዳንን አስጀመሩ ፡ የጁሙዐ ቀን ጨረቃን ተመለከትኩ.. በወሩ መጨረሻ ወደ መዲና መጣሁ ፡ ኢብኑ ዐብባስም መች ነበር ጨረቃን ያያችሁት አሉ ? እኔም ፡የጁሙዐ ለሊት ነበር ያየነው አልኩኝ ፡ አንተ በትክክል አይተሀልን ? አሉኝ ፡ እኔም ፡ አዎ ! ሰዎችም አይተውት ፆመዋል ፡ ሙአውያም ፆመዋል አልኳቸዉ ፡ እርሳቸዉም “ ሁላችንም ያየነው የቅዳሜ ለሊት ነው ፡ ሰላሳ ቀን እስኪሞላ ወይም ጨረቃን እስክናይ ከመፆም አንወገድም አሉኝ ። በሙዐዊያ እይታና ፆም አትብቃቁምን ? አልኳቸዉ ፡ አልብቃቃም ፡ የአሏህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንደዚህ ነው ያዘዙን❞ አሉኝ።
ሙስሊም ዘግበውታል
ከዚህ ሀዲስ ተነስተው ኡለማዎች እንዲህ ብለዋል :
አንድ ሰው ጨረቃ ከታየበት ሀገር ሌላ ሩቅ ወደሆነ ረመዷን ወዳልገባበት ሀገር ቢጓዝ ፣ እዚያች ሀገር በመግባቱ ምክንያት የዚያች ሀገር አንደኛው ነዋሪ ስለሚሆን ወደ አዲሱ ሀገር ከመምጣቱ በፊት የፆመው ሰላሳ ቀን ቢሆንም እንኳ የአዲሱን ሀገር ሰዎች በፆም ይገጥማቸዋል ወይም እነርሱ እስከፆሙ ድረስ እርሱም አብሯቸው ይፆማል
ጨረቃ ካልታየበት ሀገር ጨረቃ ወደ ታየበት ሀገር የተጓዘ ሰው እነርሱ ፆም ሲፈቱ እርሱም አብሯቸዉ ይፈታል ፣ ነገር ግን የፆመው ቀን ሲደመር ሀያ ስምንት ቀን ከሆነ አንድ ቀን ቀዷእ ያወጣል ምክንያቱም በአረብኛ አቆጣጠር አንድ ወር ሀያ ስምንት ቀን ስለማይሆን ፣ የፆመው ቀን ሲደመር ሀያ ዘጠኝ ከሆነ ግን ምንም የለበትም ።
ነገ ዒድ ነው የተባለበት ሀገር ላይ ካነጋ በኃላ የሀገሪቷ ነዋሪዎች ፆመኛ ወደሆኑበት ሀገር የተጓዘ እንደሆነ እነርሱን ለመግጠም ሲል የተቀረውን የቀን ክፍል ፆምን ከሚያበላሹ ተግባራት መቆጠብ አለበት
ዘ.ሐ& ፈቂር