የሱብሂ ሁለተኛው አዛን እየተደረገ ስለ መብላትና መጠጣት የተደረገ ውይይት
————————————————-
አዚዝ ፡ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ
ዘኪ: ወአለይኩም አስሰላም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ
አዚዝ:- ረመዳን ሙባረክ
ዘኪ:- ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም
አዚዝ:- የሱብሂ አዛን እያለ የያዝኩትን ምግብ ወይም መጠጥ መጨረስ እችላለሁ ወይስ አልችልም ⁉️
ዘኪ:- የሱብሂ አዛን ካለብህ አፍህ ውስጥ ያለውን መትፋት ነው ያለብህ ፤ አዛን እያለ ማንኛውንም ምግብም ሆነ መጠጥ ወደ ውስጥ ካስገባህ ቀዷእ ግዴታ ይሆንብሀል ።
አዚዝ:- ይህ ሀሳብ ከሀዲስ ጋር ይጋጫል
ዘኪ:-ከየትኛው ሀዲስ ጋር ?
አዚዝ :አቡ ዳውድ አቡ ሁራይራን ረዲየሏሁ ዐንሁ ዋቢ አድርገው በዘገቡት ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:-
" አንዳችሁ በእጁ እቃ እያለ የአዛን ጥሪ ከሰማ ፡ ጉዳዩን ሳይጨርስ ( መብላቱን ወይም መጠጣቱን ) አያስቀምጠው " ።
👉 ይህ ሀዲስ የሚያስረዳን አዛን ቢልም መጠጣትና መብላት እንደሚቻል ነው ፡ እቃው እጃችን ላይ እስካለ ማለት ነው።
ዘኪ:- ሲጀምር ይህ ሀዲስ ጠንካራ(ሰሂህ) ነው ወይስ ደካማ ነው በሚለው ላይ የኡለሞች አቋም ተለያይቷል ። አቡ ሀቲም ፣ ኢብኑ ቀጣን ፣ አብዱላህ ሲዲቅ አልጉማሪ ይህ ሀዲስ ሰሂህ መሆኑ አጠራጣሪ ነው ሲሉ ኢማሙ ሀኪም ፣ ዘሀቢ እንዲሁም ኢማሙ አህመድ ሰሂህ ነው ብለዋል።
ሁለተኛ : ይህ ሀዲስ ሰሂህ ነው የሚሉ ዑለሞችን አቋም ብንከተል እንኳ ውጫዊ መልእክቱን እንስራበት ካልን ከቁርአን አንቀፅ ጋር ይጋጫል ፡ ፆም ላይ ከየትኛው ሰአት እስከ የትኛው ሰአት መመገብ እንደምንችልና የትኛው ሰአት ላይ መመገብ እንደሌለብን ቁርአን በማያሻማ መልኩ እንዲህ በማለት ነግሮናል :-
“ ከጎህ የሆነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር ( ከሌሊት ጨለማ) ለእናንተ እስከሚገለፅላችሁ ድረስ ብሉ ፤ ጠጡም ። ከዚያም ፆምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ ። “
وَكُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّى يَتَبَيَّنَ لَكُمُ الْخَيْطُ الأَبْيَضُ مِنَ الْخَيْطِ الأَسْوَدِ مِنَ الْفَجْرِ [البقرة:187].
❇️ የሁለተኛው አዛን ሌሊት አልቆ ንጋት መግባቱን ማመላከቻ ነውና በዚህ ቁርአናዊ ትእዛዝ መሰረት በቀን መመገብ አይቻልም ።
ሶስተኛ : ይህ ሀዲስ ከሌላ የአሏህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ጋር ይጋጫል ፡ እርሱም :-
وسئل أنس عن ذلك، كم كان بين الأذان والسحور؟ قال: قدر خمسين آية،
ሰይዱና አነስ :- “ በአዛንና በሱሁር መካከል ምን ያክል ክፍተት ነበር “ ? ተብለው ተጠይቀዉ ፤ 50 አንቀፆችን የሚያስነበብ ጊዜ ያክል ሲሉ
መልሰዋል።
ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
👉 አይደለም አዛን እያለ ሊመገቡ ይቅርና አዛን ሊል ሀምሳ አንቀፅ የሚያስቀራ ያክል ጊዜ ሲቀር መመገብ ያቆሙ ነበር
አራተኛ :- ይህ አጠራጣሪ የሆነ ተግባር ነው ፤ አጠራጣሪ የሆነን ነገር መተው ደግሞ የተገባ ነው።
አምስተኛ :-በነብዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ሁለት አዛን ነበር የሚደረገው ፤ ስለዚህ ሀዲሱ የሚያወራው ስለ መጀመሪያው አዛን እንጂ ስለ ሁለተኛው አይደለም ።
ስለዚህ በጭራሽ አዛን እያለ መብላት አይቻልም ፣ የበላም ሰው ማካካሻ ማድረግ አለበት ፡ አዛን እያደረገ ተመግበህ ፆመኛ ነኝ ብለህ በከንቱ ደርቀህ ከመዋል ለፆምህ ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታ ነው ።
አዚዝ: ጀዛከሏህ
ዘኪ:-وإياك( ላንተም)
https://t.me/sufiyahlesuna