Forward from: AI-IKHILAS
የዳዕዋ መንሐጅ /አካሄድ/ በቤት ውስጥ
ቤት ውስጥ ያለው ዳዕዋ እና የልጆች የአስተዳደግ ስርዓት ፤ የኢስላማዊ ትምህርት አቀራረብ እና ተግባራዊነት ፤ ከመስጅድ እና ከትምህርት ቤት ለየት ማለት አለበት፡፡ በዚህ ላይ በተለይ ሙስሊሞች አናሳ በሆኑበትና የልጆች አስተዳደግ
በስርዓት በማይመራበት አካባቢ ፤ በቤት ውስጥ የሚደረገው ዳዕዋ አንገብጋቢነትና
የሴቶች ተሳትፎ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡
ሙስሊም እህቶቻችን በዳዕዋው ስራ እንዲሰማሩና ውጤት እንዲያመጡ
ከተፈለገ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-
✓ ሸሪዓዊ እውቀት ፤
✓ በእውቀት መስራት ፤
✓ ባወቁት ነገር ዳዕዋ ማድረግ እና
✓ ችግሮች ሲያጋጥሙ ትዕግስት ማድረግ ናቸው፡፡
የዳዕዋውን መንሐጅ በሚከተለው መልኩ አላህ ግልጽ አድርጎታል፡- ِ
“ይህች መንገዴ ናት ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ
ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም በል፡፡” ዩሱፍ
በዚህ መሰረት ዒልም (እውቀት) ለዳዕዋ ዝግጅት ዋና መሰረቱ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የቤት ውስጥ ዳዕዋ መሰረቶች
በቤት ውስጥ ለሚደረገው ዳዕዋ መሰረቶቹ በርካታ ሲሆኑ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርጉንን ዋና ዋና የሚባሉትን እንደሚከተለው ለመጠቆም እንሞክራለን፡-
1. ኢማን እና እውቀትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ ትምህርቶች/
2. ስነ-ምግባርን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ትምህርቶች/
3. ሞራልን በማነጽ ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ ትምህርቶች/
4. ማህበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
5. አካላዊ ጥንካሬን የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
6. ጾታዊ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
7. ዳዕዋን አስመልክቶ የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
https://t.me/AlIkhilasmedresa