🌷ከሱኒዋ እህት ለሱኒይቷዋ🌷🌷ﻣﺎ ﺃﺟﻤــﻞ ﺃﻥ ﺗﻜــﻮﻥ ﺍﻟﻤــﺮﺃﺓ🌷 👑ﻃﺎﻟﺒﺔ ﻋﻠﻢ ﻧﺎﺷﺮﺓ ﻟﻠﺨﻴﺮ ﻋﺎﺭﻓﺔ ﻟﻠﺴﻨﺔ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالأِنْسَ إِلاَّ لِيَعْبُدُونِ 
*ሱራህ 51, አያህ 56*
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
================================

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: AI-IKHILAS
ክፍል 2

ጥቂት ኢስላማዊ ስርዓቶች

1.የቤት አገባብና አወጣጥ ስርዓቶች
1.1 የቤቱ ሰው ማስፈቀድ
አንድ ሰው የራሱ ያልሆነን ቤት ከመግባቱ በፊት ማስፈቀድ ግዴታው ሲሆን የራሱ ቤት2 ሲገባም ቢያስፈቅድ መልካም ነው።
1.2 ሰላም ማለት (ኢስላማዊ ሰላምታ)
1.3 ወደ ቤት ሲገባ የሚባለውን አዝካር ማለት
1.4 ጥርስን መፋቅ
1.5 ቀኝ እግርን ማስቀደም
1.6 ከቤት ሲወጣ የሚባለውን አዝካር ማለት

2 የአመጋገብ እና የአጠጣጥ ስርዓቶች
2.1 ከመብላት በፊት ቢስሚላህ ማለት
2.2 በቀኝ እጅ መብላት
2.3 ከፊት ካለው እያነሱ መብላት
2.4 ከመብላት በፊትና ከተበላ በኋላ እጅን መታጠብ
2.5 ተደግፎ አለመብላት
2.6 በሆድ ተኝቶ አለመብላት
2.7 ከሳህን ዳር ዳር መመገብ
2.8 በወርቅ ወይም በብር ሳህን አለመብላት
2.9 በህብረት መብላት
2.10 በሶስት ጣት መብላት
2.11 ከልክ በላይ አለመመገብ
2.12 በጣም ትኩስ ምግብ በረድ እስኪል መጠበቅ
2.13 የምግብ አቃቂር አለማውጣት
2.14 አቅራቢያ ያለ ሰው መጋበዝ
2.15 አገልጋዩን አብሮ እንዲበላ ማድረግ ወይም ካቀረበው ምግብ መስጠት
2.16 ለሚስት ማጉረስ
2.17 መሬት የወደቀን በማንሳት ጠራርጎ መብላት
2.18 ሲጨረስ ጣቶቹን መላስ
2.19 የተበላበትን ሳህን መጠራረግ
2.20 ምግብ በልተው ሲያጠናቅቁ የሚባለውን አዝካር ማለት
የአጠጣጥ ስርዓቶች
2.21 ቢስሚላህ ማለት
2.23 በቀኝ መጠጣት
2.24 ተቀምጦ መጠጣት
2.25 በወርቅ ወይም በብር እቃ አለመጠጣት
2.26 ኩባያ ውስጥ አለመተንፈስ
2.27 ከብርጭቆው ውጭ ሶስት ጊዜ እያቆራረጡ መተንፈስ
2.28 በውሀ ማቅረቢያ በጆግ ወይም በጀሪካን በመሳሰሉት አለመጠጣት
2.29 ዝንብ መጠጥ ውስጥ ሲገባ አለመድፋት
3 የመኝታ ስርዓቶች

ይቀጥላል
https://t.me/AlIkhilasmedresa


Forward from: AI-IKHILAS
الله أكبر

ቁርአን ለመሀፈዝም ሆነ ለመማር ቆርጠው መንገድ ለጀመሩ አማኞች ትልቅ ብስራት

ኢብኑ አል ቀይም رحمه الله:

ቁርአንን እየተማረ የሞተ ሰው ከሞተ
ቡሀላ አላህ ያሟላለታል ይላሉ።"
📚[ تحفة المودود (ص١٦١) ]
👉ምንጭ
https://t.me/AlIkhilasmedresa


Forward from: AI-IKHILAS
ታላቅ የብስራት ዜና ለሰለፍዬች

            ከሰለፍያ ህትመት ስራ/المكتب السلفية

የሸይኽ የሱፍ አህመድ ከ100 በላይ ትርጉም
   መጸሐፎች ለገበያ ወጣ


❶, የዓቂዳ ምንጮች
❷,የተውሒድ_አንገብጋቢነትና_በኢስላም_ያለው_ደረጃ
❸,ፈትሁ_ረቢል'_በርየቲ_ቢተልኺሲል_ሀመዊየቲ
❹, ጅን አውድቅና ፈውሱ
❺,ጅሐድ_ፅንፍ_በመያዝና_በማጓደል_መካከል
❻,ጀርህ_እና_ተዕዲል_ምግብ_ውስጥ_እንደሚጨመር_ጨው_ዓይነት_ነውን
❼,ድግምተኛ_በመጣበት_ስፍራ_ሁሉ_አይቀናውም
❽, የጾም ትሩፋት
❾, የዓሹራ ቀን ትሩፋት
❿, የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
⓫, የአላህ_ ስምችና_መገለጫዎቹ_በአላህ ስሞችና_መገ.......
⓬, የኢማን -ትሩፋት_ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል
⓭, የኢኽዋን ሴራ በሁለቱ ሀረሞች
⓮, የኡዱሕያ ህግጋቶች
⓯,የአላህ_አምልኮት_እና_አምልኮትን_ለመፈፀም_የሚያግዙ_ነገሮች
⓰,የአላህ_ስሞችና_መገለጫዎቹ_በአላህ_ስሞችና_መገለጫዎች_ዙሪያ_አህለሱናዎች_ያላቸው_አቋም
⓱, የአላህ ባሮች መገለጫዎች
⓲, የተፍሲር መሰረታዊ ሕጎች
⓳,የአህለ'ሱና_ወል'ጀማዓህ_ዓቂዳ_እምነት
⓴, የተዘረጋው የአሏህ ገመድ
❷❶,የተውሒድ_አንገብጋቢነትና_በኢስላም_ያለው_ደረጃ
❷❷,የቢድዓ_ባለቤቶችን_በማወደስ_ላይ_ሙመይዑ_ኢብን_ሙነወር_ያቀረባቸውን_ማምታቻዎች_ማፈራረስ
❷❸,የበረካ_ትክክለኛ_ምንነትና_በረካ_የሚገኝባቸው_ምክንያቶች
❷❹,የሸይኹል_ኢስላም_ሙሐመድ_ብን_ዓብዲልወሃብ_ረሂመሁሏህ_የመጽሐፍ_ድርሰትና_ዝግጅት_መርሆ
❷❺,የሸሪዓው_ሙሉነትና_የቢድዓ_አደገኛነት_ይፋ_መሆን
❷❻, የሱና ደረጃ በኢስላም
❷❼, የሰራተኞች መብቶቻቸው
❷❽,የሰለፎች_ጎዳና_ለሙስሊሙ_ማህበረሰብ_አስፈላጊነቱ
❷❾, የረመዷን ወር መጣ
⓷⓪, የማይመለስ ዱዓ
❸❶, የማክፈር ብይን እና ህጎች
❸❷, የሙመይዓህ መገለጫዎች
❸❸የመጸዳጃ ቤት ስርዓትና ዚክሮቹ
❸❹, የመልካም ሚስት መገለጫዎች
❸❺,የሐሳብ፣_የጭንቀትና_የሐዘን_ማስወገጃ_ዱዓ
❸❻,የልጆች_አስተዳደግ_መሰረታዊ_ትኩረቶች
❸❼, የላኢላሃ ኢል'ለሏህ እውነታ.
❸❽,የአንገብጋቢ_ትምህርቶች_ለማያውቁ_ህዝቦች_ትንታኔ
❸❾,የ_“አየተል_ኩርስይ”_ትሩፋትና_ወደተውሒድ_ያላት_ጥቆማ
❹0,የ_“ተሶውፍ”_ምንነትና_በዲንና_በዒባዳ_መሰረቶች_ላያ_ሱፍያዎች_ያላቸው_አቋም
❹❶,ዝምድናን_መቀጠል_እና_እርሷን_ዝምድናን_ከመቁረጥ_ማስጠንቀቅ
❹❷, ዓቂዳን ማቀናዘል
❹❸,ወደአሏህ_በሚደረገው_ጥሪ_አህለስ'ሱና_ወል'ጀማዓህ_የሚከተሉት_ጎዳና
❹❹,ወደሐይማኖቶች_አንድነት_የሚደረገው_ጥሪ_ግልጽ_ክህደት_ነው
❹❺,ወደ_አላህ_መንገድ_የሚጣሩ_ሰዎች_መገለጫዎቻቸው
❹❻, ወደ እስልምና እምነት የመመራት ጸጋ
❹❼, ወልዩ ማን ነው
❹❽,ኸድር_ከሚሴ_በሸይኽ_ረቢዕ_አል'መድኸሊ_ላይ_ለቀጠፋቸው_ቅጥፈቶች_የተሰጠ_በቂ_ምላሽ_
❹❾,ከጅሐድ_ጥበብና_ህግጋት_ምርጥ_ፍሬዎች
➎0 , ከተውሒድ አርማዎች
❺❶,ከአላህ_ምህረትን_መጠየቅ_ያለው_ደረጃና_የምህረት_ጠያቂዎች_ባህሪ
❺❷, ከተውሒድ አርማዎች
❺❸,ከሱረቱል_በቀራህ_መጨረሻ_ላይ_የሚገኙ_ሁለት_አንቀጾችን_በየሌሊቱ_መቅራት_ያለው_ትሩፋት
❺❹,ከመካነ_መቃብሮች_ጋር_የሚደረጉ_ግንኙነቶችና_አደጋዎቹ
❺❺, እውነተኛ ንግግር በኸድር ከሚሴ ላይ
❺❻,ኢትዮጵያዊው_ሙሐዲስ_አሽ'ሸይኽ_ሙሐመድ_ብን_ዓልይ_ብን_አደምና_የህይዎቱ_ነጸብራቆች
❺❼, አደራን መወጣት
❺❽, አንድነት በአህለሱና መንሐጅ (ጎዳና)
❺❾, አትራፊ የንግድ ማዕከላት
❻0,አስር_ጾምን_የተመለከቱ_አንገብጋቢ_ነጥቦች
❻❶, አስሩ የቀጥተኛነት መሰረታዊ ህጎች
❻❷, አራት መሰረቶች ለሙስሊም ነጋዴዎች
❻❸,አል’አርበዑነ_አል’ለተሚየህ_ፊል’ዓቃዒዲ_ወል’መናሒጂ_አስ’ሰለፊየህ
❻❹, አል'ዓቂደቱ አል'ዋሲጢያህ
❻❺,አላህን_በብዛት_የማስታወስ_ትሩፋትና_እርሱን_ከማስታወስ_መዘንጋት_አስቀያሚነት
❻❻, ነብዩን ﷺ መውደድ ግዴታ ነው
❻❼, ታማሚው እንዲፈወስ የሚደረግ ዱዓ
❻❽, ታላቁ ዕውቀት
❻❾,ተውሒድ_በሙስሊሙ_ህይወት_ውስጥ_ያለው_ደረጃ
❼0, በዓቂዳ ዙሪያ የግንዛቤ ማስተካከያ
❼❶,በኢስላም_ውስጥ_ሰርጎ_ገብ_የሆነው_መውሊድ_ብዥታዎቹና_መልሶቻቸው
❼❷,በአስተማሪዎችና_በተማሪዎች_መካከል_ባለው_ስነ_ስርዓት_የምናገኛቸው_ጥቅሞች
❼❸, በአላህ ላይ የመመካት እውነታ
❼❹,በሶላት_ዙሪያ_ለቀረቡ_ጥያቄዎች_የተሰጡ_መልሶች_እና_የሰጋጂች_ስህተቶች
❼❺,በሴቶች_ምክንያት_የሚመጣው_ሁከትና_ከወንዶች_ጋር_የመቀላቀል_ጉዳቱ
❼❻,በሚጠቅምህ_ነገር_ላይ_ፍላጎቱ_ይኑርህ
❼❼,በሐበሻ_ምድር_የሚገኘው_የሙመይዓው_ሸይኽ_ኸድር_ከሚሴ_የቢድዓ_ባለቤቶችን_ማወደስ_በተመለከተ_የተጓዘባቸው
❼❽,በሐበሻ_ምድር_ሙመይዓዎች_እነማን_ናቸው
❼❾,በሁለት_ኹፎች_ላይ_ማበስን_በተመለከተ_የተሰጡ_ፈታዋዎች
❽0, ቁርኣንን ማላቅ
❽❶,ሸይኽ_አልዓላማ_ሙሐመድ_ብን_ዓልይ_አደም_አልኢትዮጵይ_“የተተነተነ_ትችትን”_አስመልክቶ_የሙመይዓው_ሸይኽ
❽❷, ሶስቱ መሰረቶች
❽❸, ሶሃቦችን አስመልክቶ ያለብን ግዴታ
❽❹,ሴቶችን_በረመዷን_የሚያሳስባቸው_ጉዳይ
❽❺, ሲሳይን የማግኛ መንገዶች
❽❻, ሱፍያነት የድንቁርና መገለጫ
❽❼,ሰዎች_ከሚያደርሱት_መከራ_ለመታገስ_የሚያግዙ_ነገሮች
❽❽, ሰዎች የሚዘነጉት ወር
❽❾, ሰላማዊ ሰልፍ ብዥታዎቹና መልሶቹ
❾0,ሰለፍይ_በሆነው_መንሐጅ_ላይ_የተመዩዕ_ወንጀል
❾❶, ምላስን በመጠበቅ የሚገኙ ፋይዳዎች
❾❷, ማመሳሰያዎችን ማጋለጥ
❾❸, ሙዚቃና የሙዚቃ መሳሪያዎች እርምነት
❾❹, ሙስጦለሁል ሐዲስ
❾❺, ሙስሊሟ ሴት በቤቷ
❾❻, ሙስሊሟ ሴት ሆይ ሒጃብሽን አደራ
❾❼,ሙስሊሞችን_“ሰለፍያ”_፣_“ሱፍያ”_፣_“አሻዒራ”_በሚሉ_ስያሜዎች_አትከፋፍሏቸው፡፡_ሁላችንም_ሙስሊሞች
❾❽,ሙስሊም_ካልሆኑ_ሰዎች_ጋር_በሚኖረን_ግንኙት_ላይ_ሸሪዓዊ_ህግጋቱ
❾❾, መጀመሪያ ዓቂዳ
❶00, መሰረተ ቢስ የሆኑ መጠበቂያዎች
❶0❶,ልጅ_በሶላት_ላይ_ትኩረት_እንዲያደረግ_ከአባት_የተቸረ_ጠቃሚ_መልዕክት
❶0❷, ልቦናን ማስተካከል
❶0❸,ለጀነት_ከተመሰከረላቸው_ሰዎች_መካከል_አንዷ_ስለሆነችው_ሴት_ታሪክ
❶0❹, ለሐጅና ዑምራ ፈላጊዎች ግልፅ ጎዳና
❶0❺,ሁከትን_ለመራቅ_መከተል_የሚገባን_ህጎችና_መመሪያዎች
❶0❻, 50 ጾምን የሚመለከቱ ፈትዋዎች (1)
❶0❼,21_የኡዱሑያ_እርድን_የሚመለከቱ_ፈትዋዎች
❶0❽,21_መልስ_የተሰጠባቸው_አንገብጋቢ_ጥያቄዎች
❶0❾, 18 ዘካን የሚመለከቱ ፈትዋዎች
❶❶0,10_ሶደቀተል_ፊጥርን_የሚመለከቱ_ፈትዋዎች (1)
❶❶❶, 'የሰርጋችን’ ኮ-ተ-ታ-ኮ-ተ-ቶ-ች
❶❶❷,“አላህ_ያለቦታ_አለ”_አህባሹ_በሰለፎች_ላይ_የቀጠፈው_ቅጥፈት


ማሳሰቢያ፦ይህን ታላቅ ዜና ለሰለፍዬች በማዳረስ የጋራ ሀላፊነታችንን እንወጣ።

🗝🗝በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበናል ይደውሉ ይዘዙ!!

ለበለጠመረጃ፦
0921566720
               
0707539719
ለማዘዝ
@mektebetuselefiya_bot

https://t.me/Mektebe
tu href='selefiya
https://t.me/Mektebet' rel='nofollow'>selefiya
https://t.me/Mektebetuselefiya
https://t.me/Mektebe
tuselefiy href='a' rel='nofollow'>a




Forward from: AI-IKHILAS
Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/AlIkhilasmedresa
👆👆👆👆👆👆👆
በዚህ ቻናል ቀጥታ ይከታተሉ


Forward from: AI-IKHILAS
🔖  ሚን ኡሱል አቂደቲ አህለል ሱነቲ ወል ጀመዓ

    አላህ ካለ በዚህ አሽረል አዋኺር በሀምዛ መስጂድ በፉሪ ( 20ሜትር)አካባቢ በሚገኝው መስጂድ ሚን ኡሱል አቂደቲ አህለ-ሱነቲ ወልጀመዓ ኪታብ የሚቀራ ይሆናል ።
   🧭ሰዓት    ከ10 : 30 – 11 : 30
📌ምናልባት ታይቶ ሌላ ሰዓት ጭማሪ ሊኖር  ይችላል

   ቂራኣቱ በዚሁ ቻናል ቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል ።  ለመከታተል የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇

    የአቡ ኢልሐም (ኡስታዝ ሙሀመድኑር) ፉሪ በሀምዛ መስጂድ ተቀርተው ያለቁ  እየተቀሩ ያሉ ደርሶችን መልቀቂያ ቻናል።

👇👇👇👇👇

https://t.me/sunah123
በተጨማሪም በቻናላችን አል ኢኽላህ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይሰጠዋል። እውቀት ከንግግር እና ከተግባር ይቀደማል። በእውቀት ላይ እንበርታ።
👇👇👇👇👇
https://t.me/AlIkhilasmedresa




#ስለ_____ጫት
🎙 በጠ/ሚ
አብይ አህመድ እና
🎙 በመጅሊሱ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቱፋ

አብይ አህመድ
    => ጫት ከእስልምና ጋር ግንኙነት የለውም
    => ጫት ከረመዷን ጋር ግንኙነት የለውም
    => ጫት ልጆቻችንን ጨረሳቸው
    => ጫትን ቀስ በቀስ እናጥፋ!

ኢብራሂም ቱፋ
    ~> ጫት ቢቃም ምን አገባህ ባንተ ብር አልተገዛ
    ~> የሚቅም ይቃም የማይቅም ይተው!
    ~> ጫት አትቃሙ ማለት ሀሜት ነው
    ~> ብትፈልግ ቃም ከሱ ጋራ!!!

➝ እኛኮ ግራ ገባን ማነው ፖለቲከኛው? ማነው ሀይማኖተኛው???

➧➧➧  ነገሩ ሆነና የተገላቢጦሽ
አህያ ወደቤት ውሻ ወደ ግጦሽ


⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

ሀሳብ  ካለዎ 
⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/AbuImranAselefybot


Forward from: AI-IKHILAS
✨✨✨✨✨✨

ኢብራሂም ቢን አብዱል ዋሂድ አልመቅዲሲይ --- ዲያእ አልመቅዲሲይን ወደ ዒልም ጉዞ ሊሄድ ሲል እንዲህ ሲል መከረው፦
"ቁርዐንን መቅራትን አብዛ መቼም አትተወው ነገሩ እንዲህ ነው የምትፈልገው ነገር ሁሉ ቁርዐንን በቀራህ ቁጥር ይገራልሀል"

= ዲያእ እንዲህ ይላል ፦
"ይህንን ምክር ተቀብዬ ተገበርኩት ብዙ ጊዜም ሞከርኩት እራሴን ስመለከተው ቁርዐንን የቀራሁኝ ጊዜ ሀዲስን ማዳመጥና መሀፈዝ የሚቀለኝና ቁርአንን ያላነበብኩ ጊዜ የሚከብደኝ ሆኜ አገኘሁት"

❓የከበደህ ነገር አለን?!
❓እንዲሳካ  ምትፈልገው  ነገርስ?!
❗️ቁርዐንን ላይ ሙጭጭ በል ያኔ ምትፈልገው ነገር ገር እና ቅርብ ይሆንልሀል ልብህንም በብርሀኑ ያስደስትልሀል።

ይ🀄ላ🀄ሉን
https://t.me/AlIkhilasmedresa


Forward from: AI-IKHILAS
“ሽርክ” የወንጀሎች ሁሉ ቁንጮ

وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال : سمعت رسول الله ﷺ يقول : قال الله تعالى : "أنا أغنى الشركاء عن الشرك ، من عمل عملا أشرك فيه معي غيري تركته وشركه" رواه مسلم: ٢٩٨٥
አቡሁረይራ (ረዲየሏሁዓንሁ) ከረሱል ﷺ ሰምተው ባስተላለፉት “ሐዲስ አል'ቁድስ” አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
“ከተጋሪዎች ሁሉ መጋራት የተብቃቃሁ ነኝ ፤ ከእኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እርሱን ከነማጋራቱ እተወዋለሁ፡፡” ሙስሊም: 2985
ይህ ሐዲስ ከዑለሞች ዘንድ “ሐዲሰ አል'ቁድስ” በመባል ይጠራል፡፡
ረሱል ﷺ አንድን ሐዲስ ወደ አላህ ካዛመዱት “ሐዲስ አል'ቁድስ” በመባል ይጠራል፡፡ ወደአላህ ካልተዛመደ ግን “ሐዲስ አን'ነበውይ” በመባል ይጠራል፡፡ (¹)
አላህ ሸሪካ የሌለው ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነው፡፡ አንድ ሰው በሚሰራው ስራ የአላህን እና የሰዎችን ውዴታ የሚሻ ከሆነ ስራው ተቀባይነት ያጣል፡፡ ግማሹን ተቀብሎ ግማሹን ይተወዋል አይባልም፡፡ ከሰዎች ውዳሴን ፈልጎ ሶደቃ ቢሶድቅ አላህ ከእርሱ አይቀበለውም፡፡ ከሰዎች ሙገሳን ፈልጎ ሶላት ቢሰግድ አላህ ከእርሱ አይቀበለውም፡፡ አላህ ከተጋሪዎች ማጋራት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡
አንድ ሰው ሶላቱን ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ “እከሌ ማሻ አላህ ይሰግዳል! ሶላትን ያበዛል!” የሚል የሰዎችን አድናቆት የሚፈልግ ከሆነ ሩኩኡን ሱጁዱን ቂያሙን መቀመጡን ሁሉ ቢያስረዝም አይኑ ከሱጁድ ቦታ ተተክሎ ቢቆይ ሶላቱን አላህ አይቀበለውም፡፡ አላህ ከዚህ ሰው ሶላት የተብቃቃ ነው፡፡
“እከሌ ለጋስና ቸር ነው፡፡ ሶደቃ ለምስኪኖች ይሶድቃል፡፡” መባልን ሽቶ ለምስኪኖች ገንዘብ የሚሰጥ እና ዘወትር የሚያበላ ቢሆን እንኳ ከአላህ ዘንድ ስራው ተቀባይነት አያገኝም፡፡
አንድ ሙኽሊስ (አምልኮቱን ለአላህ ብሎ የሚፈጽም ሰው) በዒባዳው አፈጻጸም ላይ ሪያዕ (ለይዩልኝ) ገባብኝ ብሎ ቀልቡን ቢሰማውና ከሰይጣን መሆኑን አውቆ ወዲያውኑ ቢከላከለው በአምልኮቱ ላይ የሚያመጣው ችግር የለም፡፡ ሰይጣን ሁልጊዜ ሙኽሊስ የሆኑ ሰዎችን ይፈታተናቸዋል፡፡ ስለዚህ ለሰይጣን ተገዥ መሆን ሳይሆን የሚያመጣውን ፈተና በጽናት መወጣት ነው የሚገባው፡፡ እርሱን በመስጋት ወይም ሪያእ (ለይዩልኝ) ይገባብኛል ብሎ በመስጋት ኢባዳውን ማቋረጥ የለበትም፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው በአቋማችን ላይ መጽናት ብቻ ነው፡፡ እኛ ከጠነከርን ሰይጣን በፍርሃት ወደኋላ ይሸሻል፡፡
﴿مِن شَرِّ الْوَسْوَاسِ الْخَنَّاسِ﴾ الناس: ٤
“ብቅ እልም ባይ ከሆነው ጎትጓች (ሰይጣን) ክፋት (እጠበቃለሁ) በል፡፡” (ናስ: 4)
ሶላቱን ሙኽሊስ ሆኖ ጀምሮ ሪያዕ (ይዩልኝ) ገባበት ከዚያም ምንም ሳይከላከለው አምልኮቱን እስኪጨርስ በዚያው ቀጠለ ሶላቱ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ይበላሽበታል፡፡ ምክንያቱም ሶላት መጨረሻው ከተበላሸ የመጀመሪያውም ይበላሻል፡፡
በዒባዳችን ውስጥ ሪያዕን (ለይዩልኝ) ልንፈራ ይገባል፡፡ ሪያእን ፈርተን ደግሞ ዐዒባዳን ፍጹም መተው የለብንም፡፡ ሰይጣን ወደ ሰዎች ይመጣና “አትስገድ” “አትቅራ” ምክንያቱም ሪያዕ ይሆንብሃል፡፡” ይለዋል፡፡ “ሶላትህን በኹሹዕ (አላህን በመፍራት) አትስገድ ሪያዕ ይሆንብሃል፡፡” ይለዋል፡፡ ሰይጣን ይህን በማለቱ ከዒባዳ የሚዘናጉ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ የሰይጣን ተንኮል መሆኑን አውቀን በዒባዳችን ላይ መጽናት ነው የሚገባን፡፡ ለሰይጣን ቅንጣት ያክል በር መክፈት አይገባንም፡፡ ይልቁንም አላህን መፍራት መረጋጋት ለሶላታችን አንኳርና በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ ሰይጣንን እየተከላከልን አላህ በሚፈልገው መንገድ ኢባዳችንን ከፈጸምን ምንም አይጎዳንም፡፡ ይህን ካደረግን ሰይጣን ወደኋላ ሸሽቶ የሚደበቅ አካል ነው፡፡ (²)

የሰው ልጅ በሐቂቃ ካየነው በሁለት ክስተቶች የተከበበ ነው፡-
1ኛ፡- ወደዒባዳ ከመግባቱ በፊት፤
ለምሳሌ፡- ሰይጣን ይመጣና “ሰዎች ስለሚያወድሱህ አትስራ” በማለት ከዒባዳ እንዲዳከም ያደርገዋል፡፡
2ኛ፡- ወደዒባዳው ከገባ በኋላ፤
ዒባዳ ውስጥ ከገባ በኋላ ሰይጣን እየወሰወሰ ዒባዳውን ሊያበላሽበት ይሞክራል፡፡ በዚህ ሰዓት በአላህ እየተጠበቀ ሰይጣንን መከላከልና ወደኋላ እንዲሸሽ ማድረግ ነው ያለበት፡፡
በዚህ ቦታ የሚከተለው ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
ዒባዳን ጨርሰን ካበቃን በኋላ ሰዎች ቢያወድሱንና ብንደሰት ዒባዳችን ሊበላሽ ይችላል?
መልሱ፡- ዒባዳችን ሊበላሽ አይችልም የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም ዒባዳዋ በሰላማዊና በኢኽላስ ተፈጽማለች፡፡ እኛ ውዳሴን ሳንፈልግ ብንወደስ ይህ አላህ በዚህ በዱንያ ላይ ያደረገው የሙእሚኖች ፈጣን ብስራት ነው፡፡ አላህ እኛን ሳንፈልገው የውዳሴ ቦታ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ይህ ምንም ችግር የለውም፡፡ ሰዎች አወደሱት እርሱም ውዳሴያቸውን ሰማ “የመልካም ውዳሴ ቦታ ያደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው” ቢል ችግር የለውም፡፡ ዋናው ነገር ዒባዳችን ካበቃ በኋላ በፈጸምናት ዒባዳ ላይ ተነስተው ሰዎች ቢያወድሱን እና እኛ ብንደሰት በዒባዳችን ላይ የሚያመጣው ችግር የለም፡፡ ብቻ ግን ከውዳሴው ተነስተን በነፍሳችን በመደነቅ ሌሎች የአላህ ባሮችን ለመናቅ እና ዝቅ ለማድረግ ምክንያት ከሆነ ግን ይህ ስራችንን የሚያበላሽ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በልቦናው ምንም ትዝ ሳይለው ዒባዳውን በመልካም በመጨረሱ አላህ መልካም ስራ ገጠመኝ ብሎ አላህን አመሰገነ ተደሰተ ይህ ዒባዳውን ፍጹም አይጎዳውም፡፡
ይህን አስመልክቶ የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-
"من سرته حسنته وساءته سيئته فذلك مؤمن" الترمذي: ٢١٦٥، احمد: ١١٤
“መልካም ስራው ያስደሰተው መጥፎ ስራው ያስከፋው ይህ ሰው ሙእሚን ነው፡፡” ቲርሚዚይ: 2165, አህመድ: 114
አላህ ከትልቁም ከትንሹም ሽርክ ሁላችንን ይጠብቀን!

شرح رياض الصالحين لفضيلة الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين رحمه الله ٦/ ٣٤٠
==========================
(¹) ይህን አገላለፅ ዑለሞች የሚጠቁሙት በሁለቱ ሐዲሶች መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት እንጅ "ሐዲስ አንነበዊይ" ወህይ (ራዕይ) አይደለም ለማለት ታስቦበት አይደለም። ምክንያቱም ነብያችን ﷺ አላህ እንዳለው:–
﴿ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَى۞إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَى﴾ النجم: ٣-٤
"ከልብ ወለድም አይናገርም። እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራዕይ እንጅ ሌላ አይደለም።" አንነጅም: 3‐4

(²) ፉዶይል ብን ዒያድ (ዓለይሂረህመቱላህ) "ለሰዎች ሲባል ሥራን መተው ይህ ከሪያዕ (ከይዩልኝ) ነው።" ብለዋል። አል`አዝካር ሊነወዊይ ገፅ/19

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة


Forward from: AI-IKHILAS
የዳዕዋ መንሐጅ /አካሄድ/ በቤት ውስጥ
ቤት ውስጥ ያለው ዳዕዋ እና የልጆች የአስተዳደግ ስርዓት ፤ የኢስላማዊ ትምህርት አቀራረብ እና ተግባራዊነት ፤ ከመስጅድ እና ከትምህርት ቤት ለየት ማለት አለበት፡፡ በዚህ ላይ በተለይ ሙስሊሞች አናሳ በሆኑበትና የልጆች አስተዳደግ
በስርዓት በማይመራበት አካባቢ ፤ በቤት ውስጥ የሚደረገው ዳዕዋ አንገብጋቢነትና
የሴቶች ተሳትፎ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡
ሙስሊም እህቶቻችን በዳዕዋው ስራ እንዲሰማሩና ውጤት እንዲያመጡ
ከተፈለገ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-
✓ ሸሪዓዊ እውቀት ፤
✓ በእውቀት መስራት ፤
✓ ባወቁት ነገር ዳዕዋ ማድረግ እና
✓ ችግሮች ሲያጋጥሙ ትዕግስት ማድረግ ናቸው፡፡

የዳዕዋውን መንሐጅ በሚከተለው መልኩ አላህ ግልጽ አድርጎታል፡- ِ
ይህች መንገዴ ናት ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ
ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም በል፡፡” ዩሱፍ


በዚህ መሰረት ዒልም (እውቀት) ለዳዕዋ ዝግጅት ዋና መሰረቱ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የቤት ውስጥ ዳዕዋ መሰረቶች
በቤት ውስጥ ለሚደረገው ዳዕዋ መሰረቶቹ በርካታ ሲሆኑ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርጉንን ዋና ዋና የሚባሉትን እንደሚከተለው ለመጠቆም እንሞክራለን፡-
1. ኢማን እና እውቀትን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ ትምህርቶች/
2. ስነ-ምግባርን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ትምህርቶች/
3. ሞራልን በማነጽ ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች/ ትምህርቶች/
4. ማህበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
5. አካላዊ ጥንካሬን የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
6. ጾታዊ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
7. ዳዕዋን አስመልክቶ የሚሰጡ ስልጠናዎች /ትምህርቶች/
https://t.me/AlIkhilasmedresa


Forward from: AI-IKHILAS
ህጻንን ከሶፍ ማራቅ በሸሪዓ እንዴት ይታያል”

ጥያቄ፡ - አንድ ህጻን በሶፍ ውስጥ ተቀምጦ እያለ ከተቀመጠበት ቦታ ማራቅ ይቻላል?

መልስ፡- ህጻንን ከተቀመጠበት ሶፍ ማራቅ አይገባም፡፡
ለዚህ ማስረጃው የሚሆነው የሚከተለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ሐዲስ ነው፡-
"ال يقيم الرجل الرجل من مقامه ثم يجلس فيه"
“አንድ ሰው በዚያ ቦታ እርሱ ሊቀመጥ ዘንድ ሌላውን ከቦታው አያስነሳው፡፡” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡ የተከለከለበት ምክንያት በህጻኑ ላይ ድንበር መተላለፍ ፣ ቀልብን መስበር ፣ ከሶላት እንዲሸሽ ማድረግ እና ጥላቻን መዝራት በመሆኑ ነው፡፡ ሕጻናቶችን በአንድ ሶፍ
አድርገን ከኋላ ብናደርጋቸው እንኳ ጨዋታ ቀልድ በሶላት ውስጥ ይከሰት ነበር፡፡ ይህን
ስጋት ለማስወገድ በየሶፉ ጣልቃ አስገብተን ብናቆማቸው ችግር የለውም፡፡
https://t.me/AlIkhilasmedresa


Forward from: AI-IKHILAS
ሴት በጀናዛ ላይ መስገዷ እንዴት ይታያል?

አንዲት ሴት ወደመስጊድ በመሄድ በሟች ላይ መስገድ ትችላለች? በቤቷ ውስጥ በእርሱ ላይ ብትሰግድ ይበቃላታል? ከሁለቱ የቱ ነው በላጩ?
መልስ፡- በቤቷ በእርሱ ላይ መስገዷ በላጭ ነው፡፡ ከቤቷ ወጣ ከሰዎች ጋር ብትሰግድም
ችግር የለውም፡፡ ነገር ግን ከእኛ ዘንድ ይህ ነገር የታወቀ አይደለም፡፡
በተለይም ሟች ቤተሰብ ከሆነ በላጭ የሚሆንላት ወደመስጊድ ወጣ መስገዷ ሳይሆን
ከቤት መስገዷ ነው፡፡ ሟቹ ከውጭ ከሆነ ሶለተል ጋኢብ (የርቀት ሶላት) መስገድ አይገባትም፡፡
https://t.me/AlIkhilasmedresa


Forward from: AI-IKHILAS
ልቦና በህይወትና በሞት ደረጃ ከሆነ ልቦችን በሶስት ከፍለን መመልከት አንችላለን፡-

1. ሰላማዊ የሆነች ቀልብ፡ በማንኛውም መልኩ ሰላማዊ የሆነችና ሽርክ የሌለባት
ቀልብ ነች፡፡ ይልቁንም በመውደድ፣ በፍላጎት፣ በመመካት፣ ተጸጽታ በመመለስ፣
በመዋደቅ ፣ በመፍራት እና በተስፋ አላህን ጥርት አድርጋ ታመልካለች ፡፡
ከወደደች ለአላህ ብላ ትወዳለች ፤ ከጠላች ደግሞ ለአላህ ብላ ትጠላለች ፤
ከሰጠች ለኣላህ ብላ ትሰጣለች ፤ ከከለከለች ደግሞ ለአላህ ብላ ትከለክላለች ፤
በማንኛውም ነገሯ ዳኛዋ በረሡል صلى الله عليه وسلم ላይ የወረደው ህግ ነው ፤ በዓቂዳም
በንግግርም በተግባርም ከአላህ ህግ ውጭ ሌላን አታስቀድምም፡፡
2. የሞተች ቀልብ፡ ምንም ህይወት የሌላት ነች ፤ ጌታዋን አታውቅም፣ አትገዛም ፣
ትእዛዙን አታከብርም፣ አላህ የሚወደውን አትሰራም፤ ይልቁንም የአላህ ቁጣ
እና ጥላቻ ቢኖርበት እንኳ ከስሜቷ ጋር ነው የምትንቀሳቀሰው ፤ ፍርሃቷም፣
ተስፋዋም፣ ውዴታዋም ጥላቻዋም፣ ማላቋም ማዋረዷም ከአላህ ውጭ ነው፡፡
ስትወድም ስትጠላም ስትሰጥም ስትከለክልም ለስሜቷ ነው፡፡ ስሜትና የዱንያ
ፍላጎቷ ኢማሟ (መሪዋ) ፤ ማህይምነት ሹፌሯ ፤ ዝንጋቴ መርከቧ ነው፡፡
3. ህይወትና በሽታ የተቀላቀለባት ቀልብ፡ ይህች ቀልብ ሁለት ገጽታዎች ያሏት ሲሆን
አንዳንድ ጊዜ አንድኛው ገጽታ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛው ገጽታ ያሸንፋታል፡፡
እርሷ ከሁለቱ ወዳሸነፈው ትሆናለች ፡፡ በውስጧ የአላህ ውዴታ፣ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ተወኩል አላት፡፡ ይህ የህይወት ገጽታዋ ነው ፤ ስሜት፣ ምቀኝነት፣ ኩራት፣ በራስ መደነቅ እና የበላይነትን መፈለግ የጥፋትና የክስረት ገጽታዋ ነው፡፡
https://t.me/AlIkhilasmedresa


👍 መደመጥ ያለበት የባለትዳሮች ሀቅ የተዳሰሰበት ሙሀደራ ነው
የሴቶች ሀቅ ከባሎቻቸው ማግኘት ያለባቸው ሀቅ የተጠቀሰበት ት/ት ነው
ይደመጥ!!!
ይደመጥ!!!
ይደመጥ!!!
ይደመጥ!!!

https://t.me/sunah123


Forward from: AI-IKHILAS
ቁርኣንን ከምናልቅበት መንገዶች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1- ቁርኣንን ከመተው ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
2- ቁርኣንን ተገቢ የሆነ ንባብ ለማንበብ ከነፍሳችን ጋር መታገል፡፡
3- የቁርኣንን ሸሪዓዊ ብይን መውደድ ፣ ቁርኣን ለመጣበት መልዕክት
ተገዥ መሆን፣ በሰዎች ንግግር የአላህን ቃል አለመቃረን፡፡
4- ቁርኣንን ለአላህ ብሎ እንጅ ለይዩልኝና ታዋቂነትን ለመፈለግ ብሎ
አለመቅራት፡፡
5- የቁርኣን ባለቤት የሆነውን አላህ ክብር ማወቅ፡፡
6-ቁርኣን ከንግግሩ ሁሉ በላጭ መሆኑን ፤ እርሱን የመሰለ ከዚህ
በፊት ያልነበረ ፣ ለወደፊትም ሊኖር እንደማይችል ማመን፡፡
7- በቁርኣን ፍቅር ልባችንን ማስዋብ፡፡
8- ቁርኣን ጉድለት የሌለበት ፤ እርስ በርሱ የማይቃረን ፤
በማንኛውም መልኩ ሙሉ መሆኑን ማመን፡፡
9- ከቁርኣን አንድንም ሳንቃወም ሙሉ በሙሉ መቀበል፡፡
10- በቁርኣን ከማሾፍ መጠንቀቅ፡፡
11- ቁርኣን በዱንያም ይሁን በአኼራ ለሰው ልጆች
የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ሰብስቦ ይዟል ብሎ ማመን፡፡
12- ቁርኣንን ለማያውቀው ህብረተሰብ ማብራራት፤ የቁርኣንን ጽንሰ ሐሳብ ለማጣመም የሚሞክሩ መሰሪዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ፡፡
13- ቁርኣንን የጠላት መጫወቻ አለማድረግ፡፡
14- ጀናብተኛ ሆኖ ቁርኣንን አለመቅራት ፤ ንጹህ ሆኖ እንጅ ቁርኣንን አለመንካት ፡፡
15- እግር ወደቁርኣን ባለመዘርጋት ፤ ቁርኣንን ልክ እንደትራስ ባለመደገፍ ፤ ቁርኣንን ምድር ላይ ባለመጣል የቁርኣንን ክብር መጠበቅ፡፡
16- ግንዛቤን አጥርቶ ንጽሕናን ጠብቆ እና ሙሉ ፍላጎት ኖሮት ቁርኣንን መቅራት፡፡

ዩሱፍ አህመድ ሃፊዘሁሏህ አጭር ፅሁፍ የተወሰደ
👇👇

https://t.me/AlIkhilasmedresa


🟢የ.የሕያ አል ሐጁሪ ጭፍን ተከታይ የሆነው ከማል ሙሀመድ የተባለው ግለሰብ ለተናገረው ደካማ ንግግር ምላሽ

👉የተነሳውን ነጥብ ሸፍነህ ያልተነሳውን አታንሳ።
👉 በሀቅ ላይ ከሆነ ስምምነት ተፈላጊ ነው።

🟢የተነሱት ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች
👌የሰሊም ተልቢሶች
👌የኡማው መለያየት ሰበቦች
👌የሰሊም ሁኔታና የእናንተ አቀባበል።
ወዘተ ነበሩኮ

ከኩራትና እልህ ውጡና ለሀቅ እጅ ስጡ ሂዝቢያንም ራቁ።

🎙በኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ (ሀፊዘሁላህ)
https://t.me/Abuhemewiya




ሰሊመል ሂላሊ ከጓደኛው ዐልዩል ሀለብይ ጋር በጀምዕያ ጥቅም ተጣልቶ ተለያይቶ በቲክ – ቶክና ዩ – ቲዩብ ሀገር የሚያውቀው ሰውዬ ኢትዮዽያ መጥቶ ጀማልና አብራር ኢማም አድርገው ተቀብለውት መጨረሻ ላይ ወደ ሙመዪዓነት ዳዕዋ አደረገላቸው ። እነርሱም በደስታ ተቀብለው ዳዕዋውን ያሰራጩ ጀመር ።
በዳዕዋው ላይ ካነሳቸው ነጥቦች
– ዑለሞች በሚንሀጅ ፣ በፍቅህ እንዲሁም ዒልምይ ( ዐቀድይ ) በኾኑ ጉዳዮች ተኸላልፈው በውዴታቸው ላይ ተፅኖ አላሳደረም ። ‼
– ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ዑሰይሚን ከሸይኽ አልባንይና ከሸይኽ ሙቅቢል ጋር ተኸላልፈዋል ። ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ከሸይኽ ዑሰይሚን ጋር ተኸላልፈዋል ።
– ታሪከ ሶላት ይከፍራል አይከፍርም
– በካፊር መረዳት ይቻላል አይቻልም በሚልና በመሳሰሉት ።
– አንድ ሰው ተናዙል በማድረጉ ( የያዘውን ነገር በመልቀቁ ) አይጎዳም ። ብሎ ከአቋም መውረድ ችግር እንደሌለው አድማጮቹን ግቶ አበቃ ።
መግቢያው ላይ የተጠቀሱት የሚንሀጅ ፣ የፍቅህና ዒልምይ ( ዐቀድይ ) የሆኑ ጉዳዮች ብሎ ያመጣቸው ምሳሌዎች ሁሉ የፍቅህ ጉዳዮች ናቸው ። ይህን ሁሉ አብራርና ጀማል ተከታዮቻቸውም ሰምተው አፅድቀው ነው ማሰራጨት የጀመሩት ።

https://t.me/bahruteka

20 last posts shown.

745

subscribers
Channel statistics