5ጂ በአርባ ምንጭ በይፋ ማስጀመራችንን ተከትሎ በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡክ የአርባምንጭ ከተማን በስማርት ሲቲ እና ዲጂታል ሶሉሽኖች ያለመ ውይይት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ ከከተማዋ አስተዳዳር ከንቲባ እና የሥራ ኃላፊዎች ጋር አደረገ።
የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት የደረሰበት ደረጃ የቀረበ ሲሆን ከተማዋን ለነዋሪዎቿ፣ ለጎብኚዎች እና ለኢንቨስትመንት በሴፍ ሲቲ ሶሉሽን ምቹ እና ደህንነቷ የተጠበቀ ለማድረግ የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል፡፡
ውይይቱ ኩባንያችን የዘረጋውን ግዙፍ መሰረተ ልማት በመጠቀም የመስተዳድሩን መሬት አስተዳደር ጨምሮ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብር፣ ቱሪዝም ያሉ ቁልፍ አገልግሎቶችን በዲጂታል ሶሉሽኖች ማዘመንን ያካተተ ነው፡፡
ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን መሆን መደላድል የሆነውን የዲጂታል መታወቂያ ለዜጎች ለማዳረስ ኩባንያችን ለሚያደርገው ጥረት የትብብር ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህም ኩባንያችን ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝም ተብራርቷል፡፡
የከተማዋ የኮሪደር ልማት ከመስተዳድሩ ጋር በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑ የተወደሰ ሲሆን ይህም አገልግሎት እንዳይቋረጥ እና ሀብት እንዳይባክን ሚና መጫወቱ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም ኩባንያችን በዲጂታል ላይብረሪ፣ በችግኝ ተከላ እና ለዝቅተኛ ገቢ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያ በመለገስ ላከናወነው አርአያነት ያለው ተግባር ምስጋና ቀርቧል።
ለተደረገልን አቀባበል እና ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!