Temari Podcast - ተማሪ ፖድካስት


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Education


የዩቲዩብ ቻናላችን መቀላቀል አትርሱ 👇👇👇
https://youtube.com/@temari_podcast?si=--vADFvenliwbocx

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Education
Statistics
Posts filter


የትንሳኤ በዓል አስመልክቶ ከፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጋር የተደረገ ቃለ መጠየቅ 👇👇

https://youtu.be/pENEiYvxE8Q


የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ

@Ministry_tricks


የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመመቀራቸው በፊት በየክልሉ ሄደው ለ1 አመት ያክል ማህበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ይደረጋሉ። የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

https://youtu.be/fpIHzjPdDpM


የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ ሆነ
****

ከሰኔ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መቀመጡ ተገልጿል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚመቻችም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝና ከከፍተኛ ትምህርት መረጃ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ጥራት ያለው መረጃ ለማግኘት እና የሚሰጡ ሀገር ሀቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል።

@Temari_podcast


#RemedialExam

የ2017 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ከማዕከል የሚሰጥ ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) በቀን መጋቢት 15/2017 ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል እንደሚሆን አስታውሰዋል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪዎች ከዚህ በፊት 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ይወስዱ የነበረ ሲሆን፤ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% ከማዕከል እንዲሰጥ በጥቅምት 2017 ዓ.ም መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህም የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በሚማሩበት ተቋም የሚሰጥ የተከታታይና የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡ ከዛም በማዕከል በሚሰጥ ፈተና የተማሪዎቹ መቀጠል እና አለመቀጠል የሚወሰን ይሆናል፡፡

እንዲሁም የሚካተቱት ኮንቴንቶች ከአዲሱ ሲላበስ ለ 12 ብቻ ፤ ከድሮው ሲላበስ ደግሞ ከ9-11 ያሉትን የሚያካትት ነው ። ተማሪዎቹ ሀይስኩል ላይ ያልተማሩትን አንፈትንም ተብሏል ።

Via: Remedial Tricks


#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት፣ ቅድመ-መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የአካሚክ ሠረተኞች መኖሪያ ህንጻ፣ ባለ አራት ወለል የታደሰ የንግድ ማዕከል ህንጻ እና የሠረተኞች መዝናኛ ላውንጅ የተመረቁ ፕሮጀክቶች መሆናቸው ተገልጿል።

ዕድሳት ተደርጎባቸውና ተገንብተው የተመረቁት ፕሮጀክቶች፥ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት እንዲሁም የተቋሙን ሠራተኞች እርካታ ለማምጣት ያግዛሉ ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲው የዳታ ማዕከል፣ የምርምር ፓርክ እና ዘርፈ-ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ አዳራሽ ግንባታዎች እያከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል።

@Temari_podcast


#MoE

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ ይገባል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።

በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

@Temari_podcast




በ2017 Entrance ፈተና ላይ ከ 10ኛ እና 11ኛ ክፍል የሚካተቱ ምዕራፎች / Common Units for grade 10 and 11 for entrance👇👇👇

https://youtu.be/qqOW0KAFVyI


"የ2017 የት/ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ስርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2017 የት/ዘመን ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ-12ኛ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንዲሁም ለስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በናሙናነት ተመርጠው የተሳተፉ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በ2016 የት/ዘመን ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 የት/ዘመን የሚፈተኑም አሉ፡፡

በመሆኑም በ2017 የት/ዘመን የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና "ከላይ የተገለፁትን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባና ሁሉንም ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል" ብሏል አገልግሎቱ።


የፈተና ዝግጅቱ:
1. ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣

2. ከ10ኛ ክፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣

3. ከ11ኛ ከፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣

4. ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

የኢኮኖሚክስ ትምህርት በአዲሱ ስራአተ ትምህርት የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ ይዘጋጃል ተብሏል።

@Temari_podcast


ከዚህ ቀደም 10ኛ ክፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ተማሪዎች ፈተናዉ የሚዘጋጀዉ በሁለቱ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ከሚገኙ የጋራ የሆኑ ጥያቄዎች ይዘጋጃል👇👇👇

https://youtu.be/H9Y51G_7dxw


ያነበብነውን አየረሳን ለተቸገርን ተማሪዎች መፍትሔ

https://youtu.be/SGtHq2Q6OCo




#Exit_Exam_Result

ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ተለቋል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።

@Temari_podcast


የመውጫ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል?

በርካታ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አድርሰውናል።

👉እስካሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት የመውጫ ፈተና ውጤት #ከሁለት ቀን በኋላ ይፋ ይደረጋል የሚል መረጃ ሰምተናል።

(በተጨማሪ መረጃ እንመለሳለን)

@Temari_podcast


የ2017 ኢንትራንስ ፈተና ዝግጅት ምን ይመስላል❓

https://youtu.be/7hSs-PTJyvs


የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ላለፉት 10 ቀናት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

በተጨማሪም በምስጉን ዋንጫ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተሸላሚ ሆኗል።

በማጠቃለያ መርሐግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ (ዶ/ር)÷ የውድድሩ ጠቀሜታ የጎላ በመሆኑ ሊቋረጥ እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡

ለውድድሩ መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ አካላትም ሚኒስቴር ዴኤታው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአምስት የተለያዩ የውድድር አይነቶች በ49 ዩኒቨርሲቲ መካከል በተካሄደው ውድድር 2 ሺህ 500 ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነውበታል ።

https://t.me/Temari_podcast



18 last posts shown.