በተያዘው የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ከታቀደው የተማሪ ቁጥር የተመዘገበው በአስር ሚሊዮን ያነሰ እንደሆነ ተገለፀ።
በመላ ሀገሪቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች ከ32 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የተመዘገቡት ግን 21.7 ሚሊዮን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።
የተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከዕቅድ በታች የሆነው በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተቋማቸውን የሦስት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል።
ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ይህን ለማስተካከል የመምህራን ባንክ ማቋቋምን ጨምሮ የተለያዩ የማትጊያ ስርዓቶች ይዘረጋሉ ብለዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete