#ደመወዝ
" የደመወዝ ጭማሪ ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " - የገንዘብ ሚኒስቴር
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ፤ ከመስከረም ወር 2017 ጀምሮ የሚጨመር ደመወዝ በካቢኔ መፅደቁን አሳውቀዋል።
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ትኩረት ያደረገ የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን አመልክተዋል።
አቶ አህመድ " የተወሰነ የደመወዝ ጭማሪ ለኑሮ ድጎማ ጭምር እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ በካቢኔ ፀድቋል ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ ይደረጋል። የደመወዝ ጭማሪው ከ91 እስከ 92 ቢሊዮን ብር መካከል ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ይሆናል " ብለዋል።
በነባሩ በጀት የተወሰነ መግባቱን ፤ በተጨማሪ በጀትነትም የሚታወጅ መኖሩን ጠቁመዋል።
" ሲቪል ሰርቫንቱ አጠቃላይ የመንግሥት ሰራተኛው በሁሉም መስክ በፀጥታም በሌሎችም ዘርፍ ያሉትን የኑሮ ጫና ለመቋቋም የሚያስችለውን ድጋፍ ለማድረግ መንግሥት በከፍተኛ ቁርጠኝነት ተገባበት ነው " ሲሉ አቶ አህመድ ተናግረዋል።
" የባለፉት ሁለት ወራት የኢንፍሌሽን አፈጻጸም በሚታይበት ጊዜ እንደተሰጋው አይደለም። የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ ነው ያለው። የተወስነ ጭማሪ በአንዳንድ እቃዎች ላይ እንጂ በአብዛኛው የተረጋጋ ሁኔታ ነው ያለው። " ብለዋል።
" እንደዛም ሆኖ የደመወዝ ጭማሪው እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የሰራተኛውን ቋሚ ደመወዝተኛ ገቢ ያለውን ዝቅተኛውን ትኩረት አድርገን የዝቅተኛውን በጣም ከፍተኛ ጭማሪ አድርገናል የላይኛውን ዝቅተኛ ጭማሪ አድርገን ነው የተሰራው ዝርዝሩ በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ ይደረጋል " ሲሉ ተደምጠዋል። #TE