ጤና ሚንስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከዛሬ ጀምሮ አገር ዓቀፍ የፖሊዮ ክትባት መስጠት ይጀምራሉ። በክትባት ዘመቻው፣ በዘጠኝ ክልሎች እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለኾኑ 13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሕጻናት ክትባቱ ይሠጣል ተብሏል። ለአራት ቀናት በሚቆየው የክትባት ዘመቻ ቀደም ሲል የተከተቡ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የኾኑ ሕጻናት ጭምር መከተብ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል። ለክትባቱ ዘመቻ 85 ሺሕ የጤና ሠራተኞች እንደተሠማሩ ኢንስቲትዩቱ ያሠራጨው መረጃ ያመለክታል።
#WAZEMA
#WAZEMA