የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ፣ ከባላፈው ሳምንት ጀምሮ በኑዌር ዞን የተከሠተው አጣዳፊ ተቅማጥ ኮሌራ መኾኑ በላቦራቶሪ ምርመራ እንደተረጋገጠ አስታውቋል። በወረርሽኙ ካለፈው ሐሙስ እስከ ትናንት ድረስ 14 ታማሚዎች እንደሞቱና በጋምቤላ ከተማ የተያዙ ሦስት ሰዎችን ጨምሮ 200 ገደማ ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ ቢሮው መናገሩን ዶቸቨለ ዘግቧል። በሽታው በኑዌር ዞን፣ በአኮቦ፣ ላሬ፣ ማኮይ እና ዎንታዎ ወረዳዎች በፍጥነት እየተስፋፋ እንደኾነ ቢሮው ባሠራጨው መረጃ ገልጧል። የዓለም ጤና ድርጅት፣ ለሕክምናና ለበሽታው መከላከያና መቆጣጠሪያ የሚውል ቁሳቁሶች ለግሷል።