ልባችን ለምን አይድረቅ⁉️
ቀኑን ሙሉ ሚዲያ ላይ ነን
ስልካችን ምናልባትም አላህ ያዘነለት ሲቀር ሽንት ቤት ስንገብ እንኳ አይለየንም ስንበላ ስልክ ነው ስንቀመጥ ስልክ ነው ሰላት አሰላምተን ከጨረስን በኋላ አዝካሮች እንኳ በቅጡ ሳንል ሮጠን ስልክ ላይ ነን የጧትና የማታ አዝካሮች በቅጡ አንልም ሲደብረን ወደ ስልካችን ነው ስንደሰትም ስልካችን ላይ ነን አዳር ልክ እንቅልፍ መጥቶ እስኪወስደን ስልኩ ላይ ነን ታቅፈነው ሲነጋ እቅፋችን ውስጥ ነው የምናገኘው ስልኩ በቃ በእያንዳንዱ ሁኔታችን ስልካችን ከእኛ ሊርቅ አልፈቀድንም በተለይ wifi የምንጠቀም ሰዎች ያው አይቆጥርብኝም የሚለው ሀሳብ ይዘን ማለት ነው። ጤነኛ እንቅልፍ አንተኛ የአላህን ተአምራቶች ማስተንተን ትተናል በቀኑም ይሁን በማታው ክፍለጊዜ ቁርአኑ ቀራን ቢባል ሁለት ሰፍሃ አላህ የመራው ከሆነ አምስት፣ስድስት ሰፍሃ ይቀራል እሱም በመረጋጋት፣በማስተንተን አይደለም ለብለብ ነው ……………ኧረ የኛ ጉድ አያልቅም።
ታዳ ልባችን ምን ያርጥበው ምንስ መፍትሄ አለው❓ ከአይናችን እንባ ርቋል አላህን ፈርቶ፣ ወንጀልን አስታውሶ፣ እሳትን አስታውሶ ማልቀስ እየተረሳ ነው መተዛዘን የለም ዝምድና መቀጠል የለም ለኔ እንጂ ለኛ የሚባል ነገር ጠፍቷል ውሸት እንደ ልምድ ተወስዷል እውነተኝነት መንምኗል ያአላህ ተዘርዝሮ ለማያልቀው ጥፋታችን ይቅር በለን🤲🤲
Copy