التوحيد دعوت الأنبياء ተውሂድ የነብያት ጥሪ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


በዚህ ቻናል ላይ ዲነል ኢስላምን
—ከቁርአንና ከሀዲስ
—የኡለማዎች ንግግርና ፈትዋዎች በአላህ ፍቃድ ይለቀቃል።

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ሱብሀነሏህ እንዴት የሚደንቅ የፅናት ታሪክ ነው
------
በ1977 በኢትዮጵያ በነበረው ድርቅ ምክኒያት የተፈጠረውን ርሃብ ተከትሎ የተከሰተውን ይህን አሳዛኝ ታሪክ ሌላ ሰው ቢያወራው ኖሮ ለማመን ይከብድ ነበር ነገር ግን ይህን ታሪክ የሚናገሩት ኩዌይታዊ ሼኸ ዶ/ር አብዱራህማን አስ-ሰሚጥ ናቸውና ለማመን እንገደዳለን አላህ ይማራቸውና በአፍሪካ አህጉር ከ11ሚሊዮን በላይ ሠዎችን ያሰለሙ ሸይኽ ናቸው

ታሪኩ እንዲህ ነው በ1977 አንድ የክርሰትያን በጎ አድራጊ ማህበር ከሰሜን አሜሪካ እርዳታ ለመሰጠት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣና በቀጥታ ድርቅና ርሃብ ወደ ተከሰተበት ገጠር ሂደው እርዳታ መሰጠት ይጀምራሉ ከዚያም የመስጂድ ኢማም የሆኑ አንድ ትልቅ ሠው እርዳታ ለመቀበል ይመጣሉ አሜሪካዊው እርዳታ ሰጪ ሲያያቸው የሀይማኖት አባት መሆናቸውን አውቆ ክርሰትያን እንዲሆኑ ጠየቃቸው እሳቸውም «ክርሰትያን አልሆንም የምትሰጠኝ ከሆነ ሰጠኝ» አሉት አሜሪካዊውም «እሺ አሁን በህዝብ ፊት በውሸት ክርሰትያን ሁኜያለሁ በል እና የፈለግከውን እሰጥሃለሁ» አላቸው እሳቸውም «በውሸትም በእውነትም አልልም ሀይማኖቴን አልቀይርም አሉት» ሰውየው ተናደደ እና «በቃ የሚሰጥ የለንም» ብሎ መለሳቸው ኢማሙ ባዶ እጃቸውን ወደ ቤታቸው ተመለሱ የሳቸው ቤተሰብም ጨርሶ እርዳታ ሳያገኝ ቀረ ፥

ከ3 ወራት በኋላ ይህን ታሪክ የሰሙት ኩዌታዊ ሸይኽ አብዱራህማን እንዲህ ይላሉ «ይህን ወሬ ከሰማሁኝ በኋላ በቀጥታ ከኩዌት ወደ ኢትዮጵያ ሄድኩኝ እና እኚህ ኢማም ወደ ሚኖሩባት አካባቢ ተጓዝን እንደ ደርሰን በአካባቢው ሰው የሚባል የለም ሁሉም ድርቁን ሽሽት አካባቢውን ለቀውት ሄደዋል ይዘውኝ የሄዱት ሰዎች የኢማሙን ቤት አሳዩኝና በራቸውን አንኳኳን የሚከፍትልን ስናጣ በሩን ገፋ አድርጌ ገባሁ ያየሁት ነገር እጅግ ዘግናኝ እና አስደንጋጭ ነበር አይኔን ማመን ከበደኝ ኢማሙ ሚሰታቸው እና ልጆቻቸው ሁሉም እንደተኙ በርሃብ ሙተዋል የአጥንታቸው ሃይከል ብቻ ተኝቶ አገኘሁት ፥ «በርሃብ እንሞታለን እንጂ ሀይማኖታችንን አንቀይርም» ብለው የሞቱ የሀበሻ ቤተሰብ አይቼ ተመለሰኩኝ ፥ በተጨማሪ እነዚያ በክርሰትና ስም ይዘውት የመጡት እርዳታ የኛ የአረብ አገሮች እና የሌሎች የመላው የአለም ህዝብ አዋጥተን ለተባበሩት መንግሰታት ድርጅት በሰብአዊነት የሰጠነው እርዳታ ነበር እነርሱ ግን በእንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ አከፋፍለውታል» ሲሉ ታሪኩን ያጠቃልላሉ

Abdulfetah Mahmud
copy




ልባችን ለምን አይድረቅ⁉️

ቀኑን ሙሉ ሚዲያ ላይ ነን
ስልካችን ምናልባትም አላህ ያዘነለት ሲቀር  ሽንት ቤት ስንገብ እንኳ  አይለየንም ስንበላ ስልክ ነው ስንቀመጥ ስልክ ነው ሰላት አሰላምተን ከጨረስን በኋላ  አዝካሮች እንኳ በቅጡ ሳንል ሮጠን ስልክ ላይ ነን የጧትና የማታ አዝካሮች በቅጡ አንልም ሲደብረን ወደ ስልካችን ነው ስንደሰትም ስልካችን ላይ ነን  አዳር ልክ እንቅልፍ መጥቶ እስኪወስደን ስልኩ ላይ ነን ታቅፈነው ሲነጋ እቅፋችን ውስጥ ነው የምናገኘው ስልኩ በቃ  በእያንዳንዱ ሁኔታችን ስልካችን ከእኛ ሊርቅ አልፈቀድንም  በተለይ wifi የምንጠቀም ሰዎች ያው አይቆጥርብኝም የሚለው ሀሳብ ይዘን ማለት ነው። ጤነኛ እንቅልፍ አንተኛ የአላህን ተአምራቶች  ማስተንተን ትተናል በቀኑም ይሁን በማታው ክፍለጊዜ  ቁርአኑ  ቀራን ቢባል  ሁለት ሰፍሃ  አላህ የመራው ከሆነ  አምስት፣ስድስት ሰፍሃ ይቀራል እሱም በመረጋጋት፣በማስተንተን አይደለም  ለብለብ ነው  ……………ኧረ የኛ ጉድ አያልቅም።

ታዳ  ልባችን ምን ያርጥበው ምንስ መፍትሄ አለው❓ ከአይናችን እንባ  ርቋል  አላህን ፈርቶ፣ ወንጀልን አስታውሶ፣ እሳትን  አስታውሶ ማልቀስ   እየተረሳ ነው መተዛዘን የለም ዝምድና መቀጠል የለም  ለኔ እንጂ  ለኛ የሚባል ነገር ጠፍቷል ውሸት  እንደ ልምድ ተወስዷል  እውነተኝነት  መንምኗል ያአላህ  ተዘርዝሮ ለማያልቀው ጥፋታችን  ይቅር በለን🤲🤲
Copy


👉 ዓሹራእና ምንዳው
ዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው ።
ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናቸው መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት ። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ ። ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩ ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሚቀጥለው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በሚታረድበት ጊዜ በመድረሱ ጭንቅ ውስጥ ገባች ። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ ። እናት ምን ይዋጣት !!!!!?
አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ ። ወረወረችውም ። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች ። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባ ። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው ። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው !!! ። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት ።
ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች !!! ። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ ። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ ።
የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው ። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው ። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው ። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ : –

" صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ "
رواه مسلم ( 1162).
" የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ።
የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ "።

ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል ።
Copy


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ኢብኑ ጀውዚይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ:-
"በአላህ ይሁንብኝ! ለቀብር ባለቤቶች ተመኙ ቢባሉ ኖሮ ከረመዷን አንዲትን ቀን ይመኙ ነበር።"
📚:التبصرة (٨٧/٢)

አልሐምዱ'ሊላህ !


Forward from: Fuad Mohammed
‏عاجل :

‏رؤية هلال شهر رمضان في سدير..
‏وغداً السبت أول أيام رمضان بالسعودية .
ነገ የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ነው

ምስጋና ለታላቁ አሏህ ይገባል

https://t.me/Muhammedsirage


✔️ የረመዳን አቀባበል

➡️ ከረመዳን አቀባበል አኳያ ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ ።

⬅️قسام الناس في إستقبال شهر رمضان
⬅️قال الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله:
➡️ሸይኽ ሱለይማ አሩሀይሊይ አላህ ይጠብቃቸውና…
https://b.top4top.net/m_12102u71p1.mp3
⬅️والناس في استقباله أقسام:
➡️《ሰዎች ለረመዳን ካላቸው ጉጉትና አቀባበል እንዲሁም አጠቃቀም አንፃር በሁለት ይከፈላሉ።》

⬅️فهل أنت من القسم الفَرِح بحضوره، لأنّه يزداد به قُربًا وزُلفى إلى ربّه -جل وعلا-؟
➡️《ለመሆኑ አንተ(ቺ) ከሁለቱ ከየተኞቹ ነህ(ሽ)??!!!!!!!!!!!
➡️《የረመዳን ወር በመምጣቱ እጅግ ተደስተው ከሚቀበሉትና በተገቢ መንገድ ሊጠቀሙበት ቀድመው በቂ ዝግጅት ከሚያደርጉት??? ውይስ……???》
⬅️《 وهذا شأن المؤمنين،……》
➡️《የአማኞች(የሙእሚኖች) ባህሪ የምንዳ መሸመቺያ፣ወንጀልን ማስማሪያና ወደ ፈጣሪያቸው አላህ መቃረቢያ የሆነ የዒባዳ አይነት፣ወቅትና ቦታ የማግኘቱ እድል ባጋጠማቸው አጋጣሚ ሁሉ እጅጉን ተደስተው በእድሉ ለመጠቀም ደፋ ቀና ማለታቸው ነው።》

⬅️،{ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ (57) قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُون
📚َ (58)}[يونس58-57].
➡️ልቅናው እጅጉን የላቀው አላህ ይህንን በተመለከተ……
➡️《እናንተ የሰው ልጆች ሆይ አዕምሮ ውስጥ ላለ የተሳሳተ አመለካከት ፍቱን መፍትሄ የሆነ፣ለአማኞች(ለሙእሚኖች) መመሪያና እዝነት የሆነ መመከሪያ(መገፀጪያ) መፅሐፍ(ቁርአን) መቶላቹሀል።》
በመሆኑም በአላህ ችሮታ(ተጨማሪ ስጦታ) ማለትም በቁርአን እና በእዝነቱ(በነብዩ ﷺ መላክ) አማኞች(ሙእሚኖች) ይደሰቱ(ሊደሰቱ ይገባል)።》ይለናል።
📚ሱረቱ ዩኑስ(57_58)

⬅️《وعلى رأس هؤلاء حبيبنا ورسولنا صلى الله عليه وسلم ، يقول ابن عباس رضي الله عنه : كان رسول الله صلى الله عليه وسلم أجود الناس، وكان أجود ما يكون في رمضان حين يلقاه جبريل في كل ليلة فيُدارسه القرآن.》
➡️《እውነት የነብዩ ﷺ ተከታዮች ከሆን…
ዓብደላህ ኢብኑ አባስ እንደዘገቡት(ነብዩ ﷺ በጣም ቸር የነበሩ ሲሆን በእጅጉ ቸርነታቸው የሚንረው ደግሞ የረመዳን ወር መግባትን ተከትሎ ነበር።》ብለዋል።

⬅️《وصِنفٌ -يا عباد الله- يفرح برمضان، لا للعبادة والقُرب من الرحمن، وإنما من أجل حلاوة
السّهَر في رمضان، ومن أجل العادات، ومن أجل المسلسلات وبرامج الفضائيّات، فتراه يسأل عند قدوم رمضان: ما هي المسلسلات التي ستُعرَض؟ وما هي المُسابَقات التي يُدعَى
الناس للمشاركة فيها؟ ونحو هذا، وهذا -يا عباد الله- دليل على ضعف الإيمان ومرض القلب.》
➡️《ሌለኞቹ ግን በረመዳን መምጣት አነሰም በዛም ተደሳቾች ሲሆኑ ነገር ግን የሚደሰቱት ረመዳ ይዞት የመጣውን ግዙፍ የምንዳ አይነት ጠንክሮ ለመሸመት ሳይሆን በዘልማድ በረመዳን ወር ውስጥ የሚኖረውን የቤት ውስጥና የመስጂዶች ድምቀት፣የምግብ ዝግጅት፣በየቴሌቪዢን ስርጭቶች ረመዳንን የተመለከቱ ተከታታይ ድራማና የተለያዩ ውደድሮችን ለመከታተልና በዋዛ ግዜውን ላማባከን ሲሉ ነው።》

➡️ይህ በቀጥታ የኢማን ድክመት ምልክት ነውና
በፍጥነት ራሳችንን በማረም ከውዲሁ በራሳችን ላይ የእርምት እርምጃ በመውስድ የባህሪ ለውጥ በማምጣት ረመዳንን ለተደነገገለት አላማና ግብ ልናውለውና በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።》
📚المصدر
📚 للإستماع والتحميل على الرابط :

መጋቢት 23/07/2014 ዓ ል
ሻዕባን 29/08/1443ዓ ሂ

✍ አቡ ኢብራሂም

https://telegram.me/alfikhul_islamiyah






Forward from: التوحيد دعوت الأنبياء ተውሂድ የነብያት ጥሪ
◾️የጁመዓ ቀን ሱናዎች
➖➖➖➖➖➖➖➖
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من والصلاة على النبي
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
♦️ገላን መታጠብ
♦️ሽቶ መቀባት
♦️ሲዋክ መጠቀም
♦️ጥሩ ልብስ መልበስ
♦️ሱረቱ ከህፍን መቅራት
♦️በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
♦️በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد

https://t.me/tewehidyenbiyatteri


Forward from: Abu huzeifah seid
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እሮመዷን እና ጁሙዓ እየጠበቀ የሚሰግድ ሰዉ ፆሙ ሶላቱ ይጠቅመዋልን??
በተደጋጋሚ መክረነዋል??
በተለይ ሀገራችን የረመዷን እና የጁሙዓ ቀን ኩፍይት ከራሱ ጣል አድርጎ መስጅድ የሚገባዉ ብዙ ነዉ


ፆመኛ ሆኖ ምራቅን መዋጥ
~~ ~~~
ምራቅን መዋጥ ፆምን የሚያበላሽ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ቦታ ከተቀመጡ አካባቢያቸውን ምራቅ በምራቅ ሲያደርጉት ያጋጥማል፡፡ ምራቅ ፆም ያበላሻልን?
1. መደበኛ ወይም ከወትሮው ያልበዛ ከሆነ
ከተለመደው ያልተጋነነ ምራቅ ከአፍ አውጥተው ካልመለሱት በስተቀር ባለበት ሁኔታ ቢዋጥ ፆም እንደማያበላሽ ኢብኑ ሐዝምና ነወዊ #ኢጅማዕ ጠቅሰዋል፡፡
2. ታስቦበት ባልሆነ መንገድ ከበዛና ከተጠራቀመስ?
ሆን ብለን ሳናጠራቅመው እንዲሁ ወሬ ስናወራ ወይም ቁርኣን ስንቀራ፣… ምራቃችን ሊበዛ ይችላል፡፡ ይህንንስ የዋጠ ፆሙ ይበላሻል? ነወዊ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ሳይታሰብበት ብዙ ምራቅ ቢጠራቀም፣ ለምሳሌ ንግግሩ በመብዛቱና መሰል ሰበብ የተነሳ ሆን ብሎ ሳያደርገው ቢበዛና ቢውጠው (በሻፍዒያ መዝሀብ) ያለ ልዩነት ፆሙ አልተበላሸም፡፡” ይሄ የብዙ ዑለማዎች አቋም ነው፡፡
3. ታስቦበት ከተጠራቀመስ?
አንድ ሰው ስራየ ብሎ ምራቁን ካጠራቀመ በኋላ ቢወጠው ፆሙ ይበላሻል ወይስ አይበላሸም በሚለው ላይ ውዝግብ አለበት፡፡ በሻፍዒያ መዝሀብ ትክክለኛው አቋም ሐንበልያም ዘንድ እንዲሁ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለው ነው፡፡ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚንም ረሒመሁላህ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለውን መርጠዋል፡፡ ሆኖም ግን እራስን ከውዝግብ ማራቅ ተገቢ ነውና መጠንቀቁ ሰላማዊ ምርጫ ነው፡፡

አክታን መዋጥስ?
~~~
4. ከአቅም በላይ ከሆነ
ማስወገድ በማይችለው መልኩ ከጭንቅላቱ ቀጥታ ወደታች የሚወርድ አክታ ከሆነ ሊጠነቀቀው አይችልም፡፡ አላህ ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ነገር አይዝም፡፡
5. መቆጣጠር ሲቻል ቢዋጥስ?
ነገር ግን ስራዬ ብሎ አውጥቶ አፉ ጋር ካደረሰው በኋላ መትፋት ሲችል ቢውጠው ፆሙ ይበላሻል ያሉ ዐሊሞች አሉ፡፡ ከፊሎቹ ግን ይህም ቢሆን አይበላሽም ብለዋል፡፡ ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ “ፆሙ አይበላሽም” የሚለውን መርጠዋል፡፡ ታዲያ “ፆሙ አያበላሽም” ይበሉ እንጂ ድርጊቱ ፆመኛ ለሆነም ይሁን ላልሆነ ነው ሐራም እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ አንደኛ አፀያፊ ነው፡፡ ሁለተኛ ምናልባትም በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን የተሸከመ ሊሆን ስለሚችል ወደ ሆድ ሲገባ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚል ነው፡፡ [ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 6/428] እራስን ከውዝግብ ለማራቅ ሲባል መራቁም እራሱን የቻለ ዋጋ አለው፡፡ ወልላሁ አዕለም፡፡
-
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 14/2010)
https://t.me/IbnuMunewor


♦️ኢስላማዊ ስርዓቶችና መልካም ምግባሮች

▪️የአነጋገር ስረአቶች
〰 〰 〰 〰

♦️የሰማውን ሁሉ አለማውራት፣
➡️ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወስለም እንድህ ብለዋል የሰማውን ሁሉ ማውራት ለአንድ ሰው በቂ ሀጢአት ነው። በሌላ ዘገባም እንድህ ብለዋል የሰማውን ሁሉ ማውራት ለውሽታምነቱ በቂነው።

📚(ሙስሊምዘግቦታል

♦️እውነተኛ ቢሆን እንኳን ክርክርን መተው፣
➡️ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል። እውነተኛ ቢሆን እንኳን ክርክርን የተወ የጀነት ዙሪያ ቤት እንደሚኖረው ዋስ እ
ሆንለታለሁ።

📚(አቡዳውድ ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል

♦️ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ ከመዋሸት መጠንቀቅ፣
➡️ነብዩ ስለሏሁ አለይሁ ወሰለምእንድህ ብለዋል ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ የሚዋሽ ሰው ወየውለት ወየው
ለት።

📚አቡዳውድ አህመድ ቲርሚዚይ ዳሪሚይ ዘግበውታል

♦️ንግግርን ለታላቅ ቅድሚያ መስጠት:-
➡️ራፊዕ ኢብን ኽዲጅና ሰሕል ኢብን ሀስማ እንደዘገቡት አብደሏህ ኢብኑ ሰሕልና ሙሐይሳ ወደኽይበር በሃዱበት ተለያዩና አብደላህ ተገደለ ከዚያ አብዱራሕማን ሁወይሳና ሙሐይሳ ወደ ነብዩ ሰለሏሁአለይሂ ወስለም በመምጣት ስለጓደኛቸው ለመናገር አብዱራህማን ሲጀምር ከሌሎች ልጅ ነበርና ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ታላቅን አስቀድም አሉት።

📚ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል

♦️ንግግርን አቋርጦ ጣልቃ አለመግባት
➡️አቡሁረይራ እንዳሉት ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ተቀምጠው ለህዝቦች ንግግር እያደረጉ ሳሉ አንድ የገጠር ሰው መጣና ቂያማ መቸነው ? አላቸው ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም መልስ ሳይሰጡት ንግግራቸውን ሲቀጥሉ አንዳንድ ሰው ሰውዬው ያለውን ሰምተዋል ምላሽ ያልሰጡት ግን ንግግሩን ስላልወደዱነው አሉ። አንዳንዱ ደግሞ ኧረ አልሰሙም አሉ ።ነብዩም ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ንግግራቸውን ከጨረሱ በሗላ ስለቂያማ የጠየቀው የት አለ? አሉ እነርሱም ይሀውና የአላህ መልእክተኛ ሆይ አላቸው እሳቸውም አደራ ሲጠፋ ቂያማን ተጠባበቅ አሉት እሱም እንዴት ነው የሚጠፋው? ሲላቸው እንድህ ብለው መለሱለት ጉዳዮችን የማይገባቸው ሰዎች ማስተናገድ ሲጀምሩ ቂያማን ጠብቅ አሉት።

📚
ቡኻ
ሪ ዘግቦታል

♦️በርጋታ መናገር:-
➡️ አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት እያከታተሉ አያወሩም ነበር። በንግግራቸው ክፍተት እያደረጉ ግልጽ አድርገው ስለሚያወሩ ንግግር ልባቸውን አድማጭ ይሸመድደዋል

📚ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል።

♦️ድምጽን ዝግ በማድረግ በቀስታ መናገር
➡️አሏህ ሱብሃነሁ ተዓላ እንድህ ብሏል
وَٱغْضُضْ مِن صَوْتِكَ ۚ إِنَّ أَنكَرَ ٱلْأَصْوَٰتِ لَصَوْتُ ٱلْحَمِيرِ
« ከድምጽህ ዝቅ አድርግ፡፡ ከድምጾች ሁሉ አስከፊው የአህዮች ድምጽ ነውና

♦️ሰዎች ሊረዱት በሚችሉ አቅም ማናገር
➡️ዓሊይ ረዲየሏሁ አንሁ እንድህ ብለዋል ሰዎች በሚረዱት አነጋግሯቸው አላህና መልእክተኛው በንግግራችሁ ምክንያት እንዲስተባበሉ ትፈልጋላችሁን?

📚ቡኻሪ ዘግበውታል

♦️አድማጭ እስኪሰማ ንግግርን መደጋገም:-
➡️አነስ እንደዘገቡት ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም አንድን ነገር ሲናገሩ አድማጭ እስኪረዳ ሶስት ግዜ ይደጋግሙ ነበር።

📚(ቡኻሪ ዘግቦታል

♦️ከንግግር በፊት ሰላምታን ማስቀደም:-
➡️ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ሰላምታ ከንግግር ይቀድማል።

📚(ቲርሚዚይ ዘግቦታል

♦️ሶስት ሰዎች አንድ ላይ ካሉ ሁለቱ ተነጥለው ማውራት የለባቸውም :-
➡️ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ሶስት ከሆናችሁ ከሌሎች ሰዎች እስክትቀላቀሉ ሁለታችሁ ለብቻ በግል እንዳታወሩ አንዱ ይከፈዋልና።

📚(አቡዳውድ ቲርሚዚይና ሃኪም ዘግበውታል

♦️ጆይን በማለት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እንዲህ ዓይነት ትእዛዝ ባለበት ነው የጴንጤ፣ የጆሆቫ ሴት ሰባኪያን በየጎዳናው የሚርመሰመሱት? የኦርቶዶክስ ሴት ዘማሪያን እንደ አሸን የፈሉት? "ምእመናት" ሆይ! ስለምን ለጳውሎስ ትእዛዝ ጀርባችሁን ሰጣችሁ? ምነው በማህበር ዝም ብትሉ?!
=
https://t.me/IbnuMunewor






ወንጀል በአደባባይ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/4207



20 last posts shown.

93

subscribers
Channel statistics