ከሳምንት በኋላ ዛሬም የመርካቶ ሱቆች በአብዛኛው ዝግ ሆነዋል
(መሠረት ሚድያ)- በዛሬው እለት በርካታ የመርካቶ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ዝግ እንዳደረጉ ታውቋል፣ ምክንያቱ ደግሞ ከሰሞኑ በመንግስት አካላት እና በነጋዴዎች መካከል ውዝግብ የፈጠረው የገቢዎች የደረሰኝ አጠቃቀም ጉዳይ መሆኑ ታውቋል።
ነጋዴዎች እየተጠየቁ ያሉት የደረሰኝ ቅጣት እና የቅጣት አፈፃፀም ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ሲናገሩ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በበኩሉ በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ በመደረጉ ያነሱት ጉዳይ ነው ብሏል።
"በግምት ከዘጠና ፐርሰንት በላይ ሱቆች ዛሬ ዝግ ናቸው" ያለው አንድ ነጋዴ የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር የተሳተፉባቸው የኮንትሮባንድ ምርቶች ወደ ገበያ ያለደረሰኝ እየተበተኑ ነጋዴውን ደረሰኝ ቁረጥ ማለት አግባብ አይደለም ብሏል።
ሌላ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያለ የመርካቶ ነጋዴ የሱቅ መዝጋት አድማው "እስከ ስድት ቀን ሊቆይ ይችላል፣ እየተነጋገርን ነው" በማለት ለመሠረት ሚድያ ተናግሯል።
መንግስት ያለደረሰኝ ግብይት ሲፈፅም የተገኘ ነጋዴ ንብረቶቹ ይወረሳሉ በሚል 'ሀሰተኛ መረጃ' አንዳንድ ባለንብረቶችና ነጋዴዎች ሱቃቸውን የመዝጋትና እቃዎችን የማሽሽ ሁኔታዎች አሉ ቢልም ነጋዴዎቹ የዛሬ ሳምንት ገደማ ይርጋ ሀይሌ የገበያ ማዕከል ደረሰኝ አልተቆረጠም በሚል ምክንያት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ደንብ አስከባሪዎች እንሰወሰዱባቸው ተናግረዋል።
መረጃን ከመሠረት!
👉https://t.me/tewihd