ምን እየሆንን ነው ?
ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ የክርስትናችን መልክ ባንድም በሌላም መንገድ ስርዓት የሚባል ነገር እያጣ መጥቷል፤ ትናንት ላይ እንደ እግዚአብሔር ቃል ብዙ ልክ ያልነበሩ ነገሮች አሁን ላይ ግን ተደጋግመው ስለሚደረጉ ብቻ ትክክል መሆን ጀምረዋል፤ በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ስንፀየፋቸው የነበሩ ኃጢአቶች አሁን አሁን በቤተ-ክርስቲያን ደረጃ እንኳን እውቅና እየተሰጣቸው ነው ፤ የእግዚአብሔር ፅድቅ በዘመን አመጣሹ Democracy አሳፋሪ እየሆነ ፣ የኛ ቅጥ ያጣ ነውር ደግሞ በአደባባይ ይጨበጨብለታል 😡 የውላቹ የተወደዳቹ እኛ አገልግሎታችን ለ Media ፍጆታ፣ ጌታን እንድናሳይበት የተሰጠንን መድረክ ደግሞ ለራስ ክብርና ለታይታ እንድናደርገው አይደለም የተጠራነው፤ መቼም ቢሆን ደግሞ የኛ ስህተት በታዋቂ ሰዎች ስለተደገፈ እና ህዝብ ስላጨበጨበለት ብቻ ትክክል አይሆንም፤ የሁላችንም ሀሳብ ልክ የሚሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ከተስማማ ብቻ ነው ካለዚያ ልክ ናቸው ያልናቸው እውነታዎቻችን ሁሉ ስህተት ይሆናል፤ ክርስትናችንም ቢሆን የእውነት የሚሆነው ዘመን ከሚያመጣው ስልጣኔና በየዘመኑ ከሚነሳው የሰዎች ትምህርት በላይ በእግዚአብሔር እውነት ላይ ከተመሰረተ ብቻ ነው።
@thedayofpentecost