የሚጮህ ደም 🗣️
የሰው ደም በባህሪው ለእግዚአብሔር የሚሰማው ድምፅ አለው ብዬ አምናለሁ ትዝ ካላቹ ቃየል አቤልን ከገደለው በኋላ የአቤል ደም ወደ እግዚአብሔር እንደጮኽ መጽሐፍ በግልፅ ይነግረናል ልክ እንደ አቤልም እስከ ዛሬ ድረስ የሰዎች ደም ለፍርድ ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ ለምን አትፈርድም ፣ አታይም ወይ የሚሉ የደም ጩኽቶች በእግዚአብሔር ዘንድ እስከ አሁን ድረስ ይሰማሉ፤ ከዛሬ ሁለት ሺ አመታት በፊት መስቀል ላይ የታረደው የእግዚአብሔር በግ ደም ብቻ ግን ለህዝቦች ምህረት ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ የሌሎች ሰዎች ደም ለፍርድ ሲጮኽ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ግን ለህዝቦች ምህረት ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ አሁን አብ የሚሰማው መስቀል ላይ የታረደውን የገዛ ልጁን ደም ነው ይሄ ክቡር ደም ደግሞ ይቅርታ እና ምህረት እንጂ ፍርድን ወደኛ ለማምጣት አይጮህም ለዛም ነው መጽሐፍ “የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል” ብሎ ያለን ፤ እኛም በዚህ ምክንያት ነው በሙሉ ልብ ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ያለ ጠበቃችን ነው ለማለት ድፍረትን ያገኘነው።
@thedayofpentecost