"እኔን ጨምሮ የተ.መ.ድና የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረቦች ደህና ነን" - ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)፣ የመን ውስጥ ከአየር ጥቃት መትረፋቸውን ገልጸዋል።
"እኔን ጨምሮ የተ.መ.ድና የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረቦች ደህና ነን" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ባልደረባቸው እንደቆሰለና አንድ ሰው እንደተገደለ ፅፈዋል።
ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ በእስር ላይ የሚገኙ የተ.መ.ድ ሰራተኞች እንዲለቀቁና በየመን ያለው የሰብዓዊ እርዳታ እንድሻሻል ምክክር መደረጉን አስታውቀዋል።
ተልዕኳቸውን ጨርሰው በመመለስ ላይ እያሉ እስራዔል በሰንዓ አየር ማረፊያ ላይ በፈጸመችው ጥቃት አንድ ባልደረባቸው እንደቆሰለና ሌላ በቦታው የነበረ ግለሰብ ህይወቱ እንዳለፈ አብራርተዋል።
የተጎዳው የአየር ማረፊያ እስከሚጠገን በስፍራው እንደሚቆዩም ገልጸዋል። #WHO
@ThiqahEth