т н σ υ g н т°ρ α ι 𝔫 т ι и g 🎴


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


B l a c k o u t ☔️

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


Ratatouille

2007

Family/Comedy

1h 51m


[Overview]

Kingsman: The Secret Service (2014)፡

ይሄ የፊልሙ የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን  ጸረ-ማህበራዊ እና በወቅቱ ስራ አጥ የሆነው Eggsy Unwin የተባለ ወጣት በምስጢር የስለላ ድርጅት ውስጥ እንደ ሚስጥራዊ ወኪል ሆኖ በመቀጠር የሚያሳልፈውን ፈተና ያሳያል።

Kingsman: The Golden Circle (2017)፡

እየጠነከሩ የመጡት ጠላቶቻቸው በሁለተኛ ክፍል ላይ ዋና መሥሪያ ቤታቸውን ጠላቶቻቸው ካፈነዱ በኋላ በሕይወት የተረፉት የኪንግስማን ቡድን ወኪሎች ከአሜሪካ አቻቸው ጋር በመሆን  የአደንዛዥ ዕፅ ቡድኑን ለማስቆም የሚሄዱበትን ርቀት ያሳያል።

The King's Man (2021)፡

ሦስተኛው ክፍል ላይ ወደኋላ ታሪኩን መለስ በማድረግ ፊልሙ ስለኪንግስማን ድርጅትን መነሻ፡ አመጣጥን የሚያሳይ ሲሆን በ20ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ ላይ አንድ ኃያል ቡድን ዓለም ወደ ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ እንድትገባ ሲያደርግ የነበረውን ጥረት ለማክሸፍ አንድ ገለልተኛ የስለላ ድርጅት እኩይ እቅዳቸውን ለማክሸፍ በስውር  መሰባሰብ እና መስራት ይጀምራል ይሄ ቡድን በኋላ ላይ መለያ ስሙን "The Kingsman" በማለት ራሱን አደራጅቶ ጠላቶችን መዋጋት ይጀምራል።



[Review]

በእርግጥ ፊልሙ መሰረቱ የሕፃናት ኮሚክ መፅሀፍት ቢሆንም በአንደኛ እና ሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ስለተመሰረቱ እና ስለተጠናከሩ የተለያዩ አለም ላይ ስላሉ ሚስጥራዊ ቡድኖች አፅንኦት ይሰጣል።በፊልሙ ውስጥ ስውር የስላላ ቡድኖችን ለአንድ ሃገር ያለው እጅግ ከፍተኛ አስፈላጊነት እና የተለያዩ ከውጪም ሆነ ከውስጥ ለሚነሱ ጠላቶች ፍቱን መድሃኒት መሆን እንደሚችል ያሳያል። ሁለተኛው ክፍል The Golden Circle ላይ በተለይ በላብራቶሪ ስለሚመረሩቱ ሰውሰራሽ ቫይረሶች በደንብ ያሳያል። በሌሎች በሽታ እና ሞት ላይ የራሳቸውን ቁማር መጫወት የሚፈልጉ ስግብግብ ሰዎች በምንኖርባት ዓለም ላይ እንዳሉ ለማስገንዘብ የሚሞሞክር እጅግ በጣም አሪፍ ድርጊት የበዛበት ፊልም ነው።


#The_Kingsman_Series@thoughts_painting


"Oppenheimer" የተሰኘው ፊልም (2023) በታዋቂው ዳይሬክተር ክሪስቶፈር ኖላን የተሰራ ሲሆን ስለ ጄ. ሮበርት ኦፔንሃይመር፣ የአቶሚክ ቦምብን በመስራት ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ሳይንቲስት ታሪክ ይተርካል። ፊልሙ የኦፔንሃይመርን ህይወት፣ ከአስተማሪነቱ ጀምሮ የአቶሚክ ቦምብን ለመስራት የተደረገውን "ማንሃተን ፕሮጀክት"ን እስከመሩበት ጊዜ እንዲሁም ከጦርነቱ በኋላ በነበሩት የፖለቲካ ውዝግቦች ውስጥ ያለፉትን ፈተናዎች ያሳያል።

እና የክሪስቶፈር ኖላን አድናቂ ከሆናችሁ ወይም ስለ ታሪክ እና ሳይንስ የበለጠ ለማወቅ ፍላጎት ካላችሁ ይህን ፊልም እንዳያመልጣችሁ።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
#S2E6
«Already Broken»

ይሄ Scene ለእኔ የሙሉ Peaky Blinders የመጨረሻው Coldest moment ነው! አይኑ ውስጥ የሚታየኝ የነበረው ስር የሰደደ መከራን የመላመድ እና በገዛ ራሱ እሳት ሕመምን መላመድን ነው።Cillain Murphy እዚህ ላይ ብቻ አደለም Oppenheimer ላይ የሚገርም ገፀባህርይን የመላበስ ችሎታውን አሳይቷል።


"አደጋው የት ና ምን እንደሆነ አውቄያለሁ። መጥፎው ነገር ያንን አደጋ  እንዴት መቋቋም እንዳለብኝ አለማወቄ ነው።"

📽️;  Blade Runner 2049

የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልም ሲሆን። ስለ ሰው ልጅ ማንነት፣ ትዝታዎች፣ ነፍስ እና ህልውና ጥልቅ ፍልስፍናዊ ጥያቄዎችን የሚያጭር ፊልም ነው።
ፊልሙ በዋናነት የሚያጠነጥነው በወደ ፊት ጊዜ ውስጥ "ሪፕሊካንት" በሚባሉት ሰው ሰራሽ ፍጡራን እና በሰው ልጆች መካከል ባለው ደብዘዝ ያለ መስመር ላይ ነው። "ኬ" የተባለው ገፀ ባህሪይ የራሱን አመጣጥ ሲያፈላልግ፣ እውነተኛ መሆን ማለት የሥጋ እና የደም ውጤት መሆን ነው ወይስ ደግሞ የልብ ትርታ፣ የትዝታዎች ስብስብ እና የእኔነት ስሜት?

ትዝታዎች እውን ቢሆኑም ባይሆኑም ለማንነታችን የሚኖራቸውን ሚና ምንድን ነው እንዲሁም የእኛን ማንነት የምንገነባው ከራሳችን ልምዶች እና ትዝታዎች ነው ወይስ ሌሎች ከሰጡን ፍቅር እና ግንኙነቶች?
የምናየው፣ የምናስታውሰው እና የምንሰማው ሁሉ ምን ያህል እውን ነው? በተለይ በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዓለም ውስጥ።
ማን ነኝ? ከየት መጣሁ? የሕይወቴ ትርጉም ምንድነው? የሚሉትን ዘላለማዊ የሚመስሉ ጥያቄዎች በፊልሙ ውስጥ ተጨምቀው እናገኛቸዋለን። እውነተኛ ህይወት እና ማንነት ምን ማለት እንደሆነ ደጋግመን እንድናሰላስል የሚያደርገን ድንቅ ፊልም ነው።


ትራንስጀንደር 🤓

716 0 11 10 46

በአለማችን ላይ ከ2000 በላይ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ከ4.6 ቢልዮን በላይ ሰዎች እስከአሁን የታየ ወደፊትም የሚታይ 600 ሚልዮን በላይ ሰዎች ክርስቶስ እንዲቀበሉ ምክንያት መሆን የቻለ የ1979 The Jesus የተሰኘው የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ነው። የታሪኩ መአከል የሆነው የሉቃስ ወንጌልን ትንተና የተጠቀመ ሲሆን በፊልሙ ከኢየሱስ ስቃይ የበለጠ ትምህርታዊ ሃሳቦቹ ላይ ያጠነጥናል። እኛም ልጅ እያለን የፋሲካ ሰሞን ቅዳሜ ማታ 5:00 ሰአት ላይ የኢትዮጵያ ፊልም ላይ በተደጋጋሚ ያየነው ፊልም ነው።አሁን ድረስ እንደአዲስ የምየው እና መቼም ይሰለቸኛል ብዬ የማላስበው ፊልም ነው።ስለኢየሱስ የሕይወት ታሪክ ከዚህ ውጪ ብዙ የተሰሩ ቢኖሩም በብዙሃኑ ዘንድ የቀሩት  ሁለት ናቸው The Jesus  እና The Passion of Christ! The Passion of Christ በሚል ጊቢሰን ዳይሬክተርነት የቀረበ የኢየሱስ መከራና ስቃይ በዋናነት ለማሳየት የታለመ ፊልም ሲሆን አሁን ሁለተኛ ክፍሉን በቅርብ ቀናት ለእይታ አቅርቦል መጠሪያውንም "The Passion of the Christ: Resurrection" ይሰኛል።


CARRIE 1976




Forrest Gump
This sad scene 💔


"መጥፎ በሆነ አለም ውስጥ ጥሩ ሰዎች አይኖሩም። መጥፎ ነገሮችን የሚያደርጉ ሰወች ብቻ ናቸው ያሉት ነገር ግን ያለፈው ምንም ይሁን ማንነታችን ሚወሰነው አሁን በምናደርገው ነገር ነው ።"


"አንዳንድ ጊዜ ለመትረፍ ብቸኛው መንገድ እነሱ እንደሚያስቡህ ጭራቅ መሆን ነው። ደግነት በዚህ አለም ውስጥ ድክመት ነው።"


"ተስፋ በዚህ ጨካኝ አለም ውስጥ የሞት ፍርድ ነው። ሰወች እንዲታለሉ ና እንዳይወስኑ ያደርጋቸዋል። እዚህ የምትተርፈው በማመን ሳይሆን በመጠራጠር ነው። ካላመንህ ተስፋ ሊኖርህ አይችልም።"


#sony

📽️: In to the badlands


Repost ☄️


"The problem with the world is that the intelligent people are full of doubts, while the stupid ones are full of confidence."

----Charles Bukowski 💯

@qok_12


🪔Forrest Gump

Forrest Gump ፣ የአዕምሮ ችግር ያለበት ግን ደግ ልብ ያለው ሰው፣ አስደናቂ ሕይወቱን ይተርካል። ከልጅነቱ አንስቶ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካን ታሪክ ውስጥ ያልፋል ---የኳስ ኮከብ፣ የጦር ጀግና፣ የሽሪምፕ ንጉሥና አባት ይሆናል። ፍቅርን ፍለጋው እና ለሰዎች ያለው መልካምነት የፊልሙ ዋና ጭብጥ ነው።



እጅግ ከባዱ ተጋጣሚህ ማን እንደሆነ ታውቃለህ?ይሄ መስታወቱ ፊት ለፊት የምታየው ሰው ነው!ሁሌም ወደ ሪንግ በገባህ ቁጥር እሱን ትገጥመዋለህ፡ይሄ የቦክሲንግ ሕግ በሕይወት ውስጥ እንደሚሰራ አምናለሁ!

🆁🅾🅲🅺🆈 🅱🅰🅻🅱🅾🅰

#Creed_2015


❝ሕይወቴን ሙሉ ለነገሮች ግዴለሽ ለመሆን ጥሬያለሁ. . .

-

ነገርግን አንድ የተረዳሁት ነገር ሴቶች እና ሕፃናት ብቻ ናቸው ይሄንን ማድረግ የሚችሉት! ❞

📽️ : The Godfather

846 0 11 1 25

ሳላየው እኔስ አስተውዬ ጥሬውን ከገለባ
ትንሽ እውቀቴ ዛሬ አጠፋኝ በቃ  ይዞኝ ገደል ገባ
ኋላ ቀር እያልኩኝ ሳጣጥል ስነቀው የበፊቱን
ህይወቴን መሠረት ምሰሶዬን አጣሁት ድጋፉን
💚💛❤️


"ጀግንነት ማለት በጣም በፈራህበት ሰአት ማድረግ ያለብህን ስታደርግ ነው"

📽️: Rango


ርዕስ : ቁራኛዬ
ዘውግ : ታሪክ
ደራሲ : ሞገስ ታፈሰ

ፊልሙ በ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩት የፍርድ አሰጣጥ ላይ ተመስርቶ ነው የተሰራው ቁራኛዬ ላይ። ቁራኛዬ በ ንጉስ አፄ ምንሊክ እና ከዛም በፊት የነበረ የፍድ አሰጣጥ ስርአት ነው ታዲያ የፍርድ አሰጣጡ ለየት ይላል እንዴት አትልም?

ለምሳሌ የሆነ ሰው ቤተሰብህን ቢገልብህ ወይ ንጀል ቢሰራብህ እና ወንጀሉ ከበድ የሚል ሆኖ በ አከባቢው ሽማግሌዎች ጉዳዩ ካልተፈታ አንተና ተበዳይህ ወደ ከፍተኛ ፍትህ ወዳለበት ወደ እንጦጦ መምጣት ቢጠበቅባቹሁ ፡ ቃል ያስገቡህና ተከሳሽና ከሳሽ የሚለብሱትን ነጠላ ጋቢ(ጋቢ በጊዜው ሁሉም ሰው ያደርግ ነበር) ይቋጠርና ስንቅን ተቋጥሮላቸው አብረው እየበሉ አብረው እየጠጡ ግብር ውሀ እየከፈሉ(እየተፀዳዱ) ሳይነካኩ ብዙ ተጉዘው ለፍርድ ይቀርባሉ። ታዲያ በዚህ ሁሉ ጉዞ ውስጥ ነጠላ ጋቢያቸውን መፍታት እና አንዱ አንዱን ማጥቃት አይችሉም እነሱም ለቃላቸው ታማኝ ናቸውና አይነካኩም። ፍርድ ቦታ ሲደርሱ ግን ጋቢያቸው ይፈተና ክርክር ይጀምራሉ። ቀጠሮም ከተሰጠ ተመልሶ ጋቢያቸው ይቋጠርና አብረው ዳግም ይጓዛሉ ታዲያ ሲተኙም አይለያዩም። ደመኛህ በመንገድ ቢታመም ራሱ ተሸክመህ ተንከባክበህ በሸንጎ ማቅረብ አለብህ። ይገርማል ለስርአቱ የሚገዙበት መጠን።

ታዲያ ይህ ፊልም ይህን ስርአት ነው የሚያሳየን። አንድ የቆሎ ተማሪ ዳረጎቱን ሊያደርስ በንተስሟ ለማርያም እያለ ሲለምን የልጅነት ወዳጁን ለባላባት የተዳረችውን ፍቅሩን ያገኛታል። ታዲያ ፍቅራቸው ዳግም ይቀሰቀስና ካለልጋ በወደቁበት ቅፅበት የህግ ባሏ ይደርስባቸዋል። ታዲያ ጉዳዩን በ ከፍተኛ ፍርድ ለማሰጠት ወደ እንጦጦ ነጠላ ጋቢያቸው ተቋጥሮ ፍርድ መከታተል ይጀምራሉ። አብረው በሚጓዙበት ጊዜ ያለውን ውጣ ውረድ የሚያሳይ ነው።

ታዲያ የሰው ሚስጥ የነጠቀ ሰው ቆለጡ ባደባባይ ይቀጠቀጣል ይላል። ፍርዱን ንግስት ዘውዲቱ ይበይኑታል ምን ይሆን መጨረሻው? ሸንጎ ላይም የሚታየው ግጥማዊ ይዘት ያለው የችሎት ክርክር ጉሩም ነው። ድንቅ ፊልም በሁሉ የተዋጣለት ነው።

ይህን ስርአት እና ሌባ ሻይ የሚባለውን ስርአት ልጅ እያሱ እንደሻረው በታሪክ መዛግብት ተፅፍ እናገኛለን። ፊልሙን ተጋበዙልኝ😎


ከመ ይዘብጠኒ ይዘብጥሆ

20 last posts shown.