ርዕስ : ቁራኛዬ
ዘውግ : ታሪክ
ደራሲ : ሞገስ ታፈሰ
ፊልሙ በ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩት የፍርድ አሰጣጥ ላይ ተመስርቶ ነው የተሰራው ቁራኛዬ ላይ። ቁራኛዬ በ ንጉስ አፄ ምንሊክ እና ከዛም በፊት የነበረ የፍድ አሰጣጥ ስርአት ነው ታዲያ የፍርድ አሰጣጡ ለየት ይላል እንዴት አትልም?
ለምሳሌ የሆነ ሰው ቤተሰብህን ቢገልብህ ወይ ንጀል ቢሰራብህ እና ወንጀሉ ከበድ የሚል ሆኖ በ አከባቢው ሽማግሌዎች ጉዳዩ ካልተፈታ አንተና ተበዳይህ ወደ ከፍተኛ ፍትህ ወዳለበት ወደ እንጦጦ መምጣት ቢጠበቅባቹሁ ፡ ቃል ያስገቡህና ተከሳሽና ከሳሽ የሚለብሱትን ነጠላ ጋቢ(ጋቢ በጊዜው ሁሉም ሰው ያደርግ ነበር) ይቋጠርና ስንቅን ተቋጥሮላቸው አብረው እየበሉ አብረው እየጠጡ ግብር ውሀ እየከፈሉ(እየተፀዳዱ) ሳይነካኩ ብዙ ተጉዘው ለፍርድ ይቀርባሉ። ታዲያ በዚህ ሁሉ ጉዞ ውስጥ ነጠላ ጋቢያቸውን መፍታት እና አንዱ አንዱን ማጥቃት አይችሉም እነሱም ለቃላቸው ታማኝ ናቸውና አይነካኩም። ፍርድ ቦታ ሲደርሱ ግን ጋቢያቸው ይፈተና ክርክር ይጀምራሉ። ቀጠሮም ከተሰጠ ተመልሶ ጋቢያቸው ይቋጠርና አብረው ዳግም ይጓዛሉ ታዲያ ሲተኙም አይለያዩም። ደመኛህ በመንገድ ቢታመም ራሱ ተሸክመህ ተንከባክበህ በሸንጎ ማቅረብ አለብህ። ይገርማል ለስርአቱ የሚገዙበት መጠን።
ታዲያ ይህ ፊልም ይህን ስርአት ነው የሚያሳየን። አንድ የቆሎ ተማሪ ዳረጎቱን ሊያደርስ በንተስሟ ለማርያም እያለ ሲለምን የልጅነት ወዳጁን ለባላባት የተዳረችውን ፍቅሩን ያገኛታል። ታዲያ ፍቅራቸው ዳግም ይቀሰቀስና ካለልጋ በወደቁበት ቅፅበት የህግ ባሏ ይደርስባቸዋል። ታዲያ ጉዳዩን በ ከፍተኛ ፍርድ ለማሰጠት ወደ እንጦጦ ነጠላ ጋቢያቸው ተቋጥሮ ፍርድ መከታተል ይጀምራሉ። አብረው በሚጓዙበት ጊዜ ያለውን ውጣ ውረድ የሚያሳይ ነው።
ታዲያ የሰው ሚስጥ የነጠቀ ሰው ቆለጡ ባደባባይ ይቀጠቀጣል ይላል። ፍርዱን ንግስት ዘውዲቱ ይበይኑታል ምን ይሆን መጨረሻው? ሸንጎ ላይም የሚታየው ግጥማዊ ይዘት ያለው የችሎት ክርክር ጉሩም ነው። ድንቅ ፊልም በሁሉ የተዋጣለት ነው።
ይህን ስርአት እና ሌባ ሻይ የሚባለውን ስርአት ልጅ እያሱ እንደሻረው በታሪክ መዛግብት ተፅፍ እናገኛለን። ፊልሙን ተጋበዙልኝ😎