#ኢትዮጵያ
" ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ነው " - ቅዱስነታቸው
ዛሬ የሰላም ሚኒስቴር አንድ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ አዘጋጅቶ ነበር።
በዚህ መድረክ ላይም የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አዱዓለም ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት ፣ የመንግሥት ባለስልጣናት ፣ አባሳደሮች ጭምር ተገኝተው ነበር።
በመድረኩ ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?
(ከመልዕክታቸው የተወሰደ)
" ሰላም የሰው ልጆች ፍላጎት፣ የብዙ ምንዱባን የየዕለት ናፍቆት ነው። የበርካታ ዘመናት ቅርሶች፤ ጊዜ፣ ገንዘብ እና የሰው ጉልበት የፈሰሰባቸው ግንባታዎች በሰላም ማጣት በቅጽበት ይፈርሳሉ።
ሰላም ካለ የዓለም ሀብት ለሁሉም በቂ ነው። ሰላም ማጣት ግን ብዙ ሠራዊት፣ ብዙ የጦር መሳሪያ እንዲዘጋጅ እያደረገ ሀብትን ያወድማል።
ጦርነት ማለት ሀብትና ሕይወትን ወደሚነድ እሳት ውስጥ መጣል ነው።
የአንደኛና የሁለተኛ ዓለም ጦርነት፣ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ጠባሳው አሁንም የዓለምን መልክ አበላሽቶታል።
ሰላም በውስጥዋ ገራምነት፣ ትዕግሥት፣ ታዛዥነትና በትህትና ዝቅ ማለት ስለሚገኙ መራራ ትመስላለች፤ በውጤቷ ግን ሀገርን ከጥፋት፣ ሕዝብን ከመከራ ማትረፍ የሚቻል በመሆኑ ዋጋዋ ከፍ ያለ ነው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፦
° ሰላም የሆነው ክርስቶስ የሚሰበክባት፣
° የሰላም መልእክተኞች በውስጥዋ የሚመላለሱባት፣
° በግብረ ኃጢአት የወደቁት በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁባት የሰላም ድልድይ ስለሆነች በሥርዓተ ቅዳሴዋ ሰላምን ደጋግማ ታውጃለች፤ በጸሎቷ ለመላው ዓለም ሰላምን ትለምናለች፤ በጉልላትዋ ላይ የሰቀለችው መስቀልም ሰላምን የሚሰብክ ነው፤ የመስቀሉ ቅርፅ ወደ ላይና ወደ ጎን መሆኑም ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ሰላም መሆን እንዳለብን የሚያስገነዝበን ነው።
ታሪካችን እንደሚነግረን ወንድማማቾች ሲጋደሉ፣ በሕዝብ መካከል መተላለቅ ሲመጣ ቤተ ክርስቲያን ታቦት አክብራ፣ በእሳት መካከል ገብታ ሰላምን ስታወርድ የኖረች ናት።
በሀገር ውስጥ ግጭቶች በተፈጠሩበት ጊዜም የሰላም ጥሪን ያላስተላለፈችበት ቀንና ሰዓት አይገኝም፡፡
ሰላምን የመወያያ ርእስ አድርገን ስንሰባስብ በጦርነት መካከል የተጨነቁ ሕዝቦች፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ እና ምን እየተደረገ እንዳለ በውል የማይገነዘቡ ደካሞች ተስፋ ያደርጉናል።
ስለዚህ ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ስለሆነ ይህ ጉባኤ ከውይይት ባሻገር በተግባር ጭምር የሰላም ተምሳሌት መሆን እንደሚገባው ለማሳሰብ እንወዳለን። "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia