" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከድምጺ ወያነ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?
ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፤ የትግራይ አመራሮች በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐበይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳይ በነበራቸው ቆይታ በክልሉ ጉዳይ የሃሳብ ልዩነት አልነበራቸውም ብለዋል፡፡
ነገር ግን " የትግራይ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆነው የህዝቡ ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡
በአዲስ አበባው ውይይት በደብረፅዮን (ዶ/ር) ይሁን በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ልኡካን እንዲሁም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተወካዮች መካከል በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮች ዙሪካ ያለልዩነት መስማማታቸውን ገልጸዋል።
በወቅቱ " የፌደራል መንግሰት የትግራይ ችግሮች እንዲፈቱ አላገዝክም " በማለት ወቀሳ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።
" የፌደራል መንግስት ' ጉባኤ እንድናካሂድ ፤ የትግራይ ፓለቲካ እንድናስተካክል ጊዜ ስጠን በማለት ዕድል እና ጊዚያችሁን አባክናቹሃል ' በማለት መልሶልናል " ሲሉ አብራርተዋል።
ሌተናል ጄነራሉ ፥ " በመሃከላችን እየታየ ያለው ክፉኛ መሳሳብ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዳይረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዳይመለሱ አደገኛ መሰናክል ሆኗል " ብለዋል።
የፕሪቶሪያ ውል በይፋ የተቃወመ የለም ፤ በተግባር ግን ውሉን የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተግባር የሚፈፀሙ አካላት አሉ ብለዋል።
" የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመተግበር ብቻ ነው አቃፊ መንግስት ማቋቋም የሚቻለው " በማለትም አስረግጠዋል።
" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" እኛም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት ዓለምአቀፋዊ ወሰኖች የመጠበቅ እና የማስከበር ስልጣን አለው፤ ይህንኑ ስልጣኑ ተጠቅሞ በቦታው የሚገኙ የውጭ ሃይሎች አውጥቶ የግዛት አንድነት እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት ጠይቀናል " ብለዋል።
በዚህ ምክንያት " ' ከሃዲዎች ' በሚል ስማችንን ማጠልሸት ተገቢ አይደለም " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፤ በፌደራል መ/ቤቶች የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ ምክንያት የህዝቡ ድምፅ በተገቢው መንገድ ሊሰማ ባለመቻሉ ምክንያት ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ውክልና እንዲመለስ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ መቅረቡን ሌተናል ጀነራሉ አሳውቀዋል።
በተጨማሪ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል አንቀፅ 8 ዓለምቀፍ ወሰኖች በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ስለሚያዝ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ እና ከሱዳን የሚያገናኙ ወሰኖች ጠባቂ ስለሌላቸው የውጭ ሃይሎች እየገቡ ግፎች እየፈፀሙ ፣ ወርቅ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ወንጀሎች እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ወሰኖቹ በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።
#Tigray #TPLF
@tikvahethiopia