“ የግል ትምህርት ቤቶችን መፈናፈኛ የሚያሳጣ፣ አለመፈለጋችንን በግልጽ ያስረዳ ረቂቅ ዐዋጅ ነው ” - የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማኀበር
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወደ ቋሚ ኮሚቴ መራው የተባለው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ ዐዋጅ ላይ ብርቱ ተቃውሞ እንዳለው የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ገለጸ።
የማኀበሩ ፕሬዜዳንት አቶ አበራ ጣሰው፣ “ የግል ትምህርት ቤቶችን መፈናፈኛ የሚያሳጣ፣ አለመፈለጋችንን በግልጽ ያስረዳ ረቂቅ ዐዋጅ ነው ” ሲሉ ተችተውታል።
ፕሬዜዳንቱ በዝርዝም ምን አሉ ?
“ በረቂቁ ብዙ ነገሮች መሻሻል አለባቸው። አንኳር አንኮር የሆኑትን ለማንሳት፦
አንዱ ‘አንድ የግል ትምህርት ቤት ት/ቤት ሆኖ ለመቀጠል ‘የ6 ወራት የሰራተኞችን ደመወዝ በዝግ ሂሳብ ቁጥር ማስቀመጥ አለበት’ የሚለው ነው።
ይሄ ገንዘብ ከተቀመጠ በኋላ መቼ እንደሚወጣ አይታወቅም፣ Forever እንዲቀመጥ ነው እንድምታው። ምክንያቱም ገንዘቡ ከወጣ ፈቃድ ይነጠቃል።
አንደኛ የትምህርት ሥራ እንደንኛውም ድርጅት ንግድ ነው። በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በላሎች የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ነጋዴዎች ያለምንም ዋስትና ስራቸውን እያከናወኑ ነው ያሉት።
ዋስትና መሠረቱ ጥርጣሬ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች ሳይጠረጠሩ የትምህርት ሥራ ተጠርጣሪ ሆኖ ‘ዋስትና ካልያዝክ አትሰራም’ መባሉ አሳዛኝ ነው።
የገል ትምህርት ቤቶች ተርፏቸው የ6 ወራት ደመወዝ በአካውንት ማስቀመጥ አይችሉም። ስለዚህ ይሄ ረቂቅ ሕግ ሆኖ ከቀጠለ ትምህርት ቤቶች ሥራቸውን አይቀጥሉም።
ምናልባት ሌላ ንብረት ያላቸው ከባንክ ተበድረው በአካውንት ቢያስቀምጡ እንኳ 19% ወለድ ይከፍላሉ፣ ገንዘቡን በቶሎ መመለስ ስለሚያዳግት አመታት ይወስዳል። ወለዱም ዋናው ገንዘብም ተንገዳግደው ከፍለው እንኳ መቀጠል አይችሁም። ስለዚህ ይሄ ፈጽሞ የሚተገበር አይሆንም።
ሁለተኛ ማንም ሰራተኛ የትም ይስራ ዬት በአሰሪና ሠራተኛ ህግ ነው የሚዳኘው። ስለዚህ ረቂቅ ዐዋጁ ያለ ቦታው ነው የተቀመጠው።
ሌላው የበላይ አካል ማነው? ከትምህርት ቤት ውጪ ያለ የመንግስት አካል ነው? ወይስ ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ የትምህርት አመራሮች ናቸው? የሚለው በረቂቁ ግልጽ አይደለም።
ሕግ ይከበር እንላለን እዚህ አገር የሚያሳዝነው ነገር ግን በዬአካባቢው ራሳችን ሕግ አውጪ ሆነን ቁጭ እንላለን።
ሕግ ይከበር ስንል እኮ ሕግ የማውጣት ስልጣን ያለው አካል የሚያወጣውን ሕግ ለማክበር እንጂ እያንዳንዳችን እየፈበረክን የምንወጣባቸውን ሕጎች ለማክበር አይደለም።
ስለዚህ በሕግ አውጪው አካል የወጣው ህግ ‘ትምህርት ቤቶች እንደማንኛውም አይነት ንግድ ነጋዴዎች ናቸው’ ብሏል። ድርጅቶችምሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ናቸውና መጀመሪያ ይህንን ሲመሰርቱ እኮ በአገሪቱ የሚሰራ ሥራ አለ ብለውናል።
የኢንቨስትመንት ፓሊሲው፣ ሕገ መንግስቱ የሚያሰራ ሆኖ ሳለ በመሃል እየመጡ እንደዚህ አይነት ችግር የሚፈጥሩ ከሆነ ያሉ ትምህርት ቤቶች አይቀጥሉም፤ ሌሎች ትምህርት ሊከፈቱ አይችሉም። ምክንያቱም በዬቦታው ያለው እንቅፋት ነው ” ብለዋል።
ጉዳዩን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገ ይሻሻል የሚል ተስፋ እንዳለውም ማኀበሩ ገልጿል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia