" ትኩረት መነፈጋችን እጅጉን አሳዝኖናል " - የሽርካ ወረዳ ነዋሪዎች
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹን ዋቢ በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ከታገቱት ውስጥ የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ሰዎች ገንዘብ ከፍለው ተለቀዋል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችም ግድያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎች አመልክተዋል።
ታጣቂዎች ከ80 በላይ ከብቶችን መውሰዳቸውም ተነግሯል።
ሀገረ ስብከቱ በየዓመቱ በሚካሄደው በ43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ2016 ዓ.ም 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልጾ ነበር።
በተጨማሪ ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሪፖርቱን አቅርቦ ነበር።
በዚሁ ሪፖርት በጀጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ተፈናቅለዋል።
ባለፈው ኅዳር 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ የ13 ዓመት ታዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያ ላይ ተወስደው መገደላቸውን 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁ መገለጹ አይዘነጋል።
የዚህ አካባቢ ጉዳይ በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ሆነ በመንግሥት ትኩረት ተነፍጎታል ሲሉ ነዋሪዎች ወቅሰዋል።
ነዋሪዎቹ ግድያና ስደት እንዲሁም የሀብት ዝርፊያ ሰሚ ያጣና በወረዳው ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ የአካባቢው ምእመናን በትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።
" የማይጠቅሙና አንዳች ፋይዳ የሌላቸው ጉዳዮችን ሲዘግቡ የሚስተዋሉ ሚዲያዎች የእኛ ሞት እንደምን ቀለላቸው ? እንዲሁም ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በወረዳችን እየተፈጸመ ያለው ግፍ ትኩረት አለመሰጠቱ እጅጉን አሳዝኖናል " ሲሉ ወቅሰዋል።
" መንግሥትም የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት በመገንዘብ ሞታችንን ሊያስቆምና መፍትሔ ሊያመጣ ይገባዋል " ሲሉ ማሳሰባቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia