" የኑሮ ውዶነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል " - ተቃዋሚ ፓርቲዎች
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ (ኮከስ) ምን አለ ?
- የመድረክ
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)
- የኅብር ኢትዮጵያ
- የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ
- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
- የኢሕአፓ ... ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ በወቅታዊ ሁኔታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጫ ልኳል።
ኮከሱ ምን አለ ?
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከሱ ገዢውን የብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር በእጅጉ ኮንኗል።
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ " የአገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ከዕለት-ወደ ዕለት ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዙ ነው " ብሏል።
ይህም ለሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ እየዳረገን ነው ሲል ወቅሷል።
" ፖለቲካችን የተለመደውን የአፈናና አግላይነት፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ጠቅላይነት አጠናክሮ ቀጥሏል " ያለው ኮከሱ " የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአጃቢነት፣ ህዝብ ከአገልጋይነት ያለፈ የፖለቲካ መብታቸውን የማንሳት ህገመንግስታዊ መብት ተነፍጓቸው በወንጀል ተቆጥሮባቸው ፀጥ-ለጥ ብለው እንዲገዙ ተፈርዶባቸው በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ናቸው " ብሏል።
ኢኮኖሚው ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ ተሸጋግሮ ለተለያዩ የልማት መሰረተ ልማት አውታሮች ሊውል የሚችል የዓመታዊ በጀት ከፍተኛውን ድርሻ ለጦርነትና ጸጥታ ማስከበር ግብዓቶች እንዲውል ተደርጓል ሲል ወቅሷል።
" ልማትና ዕድገት ከቀለም-ቅብ ያለፈ መሰረት እንዳይኖረው ተገደናል " ሲልም አክሏል።
" የኑሮ ውድነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል " ሲልም ገልጿል።
ኮከሱ " ማኅበራዊ ህይወታችን በሥራ አጥነት፣ መፈናቀል፣ የማኅበራዊ ተቋማት መዳከምና የአገልግሎት መቋረጥ ወይም መቀንጨር፣ የሠራተኞች ብሶት መገለጫቸው ከሆነ ውሎ አድሯል " ብሏል።
" በየአቅጣጫው የሚነሱት ጥያቄዎችም የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው " ሲል ገልጿል።
" ከትምህርትና ጤና አገልግሎት ተቋማትና ሠራተኞች የሚሰማው ጩሄት በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል " ሲልም አመልክቷል።
ኮከሱ፦
- " ግጭትና ጦርነትን እያስፋፉ - የይስሙላ አግላይ የምክክርና ውይይት ስብከት ሊቆም ይገባል " ብሏል። " መንግስት / ገዢው ፓርቲ / ከማስመሰል ተላቆ ራሱንና የአገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ለሁሉን አካታችና አሳታፊ ተዓማኒና በባለድርሻ አካላትና አስፈጻሚዎች ተቀባይነት ያለው ሃቀኛ የምክክር ፣ ድርድር ፣ ውይይት መድረክ እንዲያመቻች ሽግግሩ በመጨናገፉ የቀጠለውና የተስፋፋው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።
- የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ማጠናከር ዓላማና ተልዕኮ ይዞ ፤ የገዢውን ፓርቲ ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ያቋቋሙት የጋራ ምክር ቤት ከተቋቋመበት ዓላማና ተልዕኮ እየራቀ የገዢው ፓርቲ ታዛዥ ጉዳይ ፈጻሚና አስፈጻሚ እንዲሆነ ጫና እየተደረገበት ነው " ብሏል።
- " የፖለቲካ ድርጅቶች ሃሳብ መለዋወጫ እንዲሆን የመሠረቱትን የጋራ ምክር ቤትን ብልጽግና ቀስ በቀስ በስልታዊውና በሚታወቀው የኢህአዴግ አካሄድና ዘዴዎች አሽመድምዶታል " ሲል ገልጿል።
- " ህወሓት መር የነበረው ኢህአዴግ ይሠራቸው የነበሩት ዕመቃዎች፣ ጥሰቶች፣ ተንኮልና ደባዎች፣ አስርጎ የማስገባትና የመከፋፈል ሤራዎች፣አሁን በወራሹ ብልጽግና ደምቀውና ጎልተው ያለድብብቆሽና ይሉኝታ እየተደገሙ ነው " ሲል ወቅሷል።
- " ብልጽግና በአደባባይ ኃሳብን በነጻነትና ያለመሸማቀቅ የመግለጽ መብት መከበርን ቢሰብክም በተግባር ግን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በአዋጅ፣ በመመሪያና ደንብ እያፈነ ይገኛል " ሲል ከሷል።
- " ሽግግር በሌለበት የሽግግር ፍትህ ውዳሴ " ከንቱ ነው በማለት ከመንግስት/ የገዢ ፓርቲ ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ጠይቋል። በመንግሥት አደራጅነት የሚቋቋም የሽግግር ፍትህ ተቋም ከዚህ በፊት ከተቋቋሙትና ያለውጤትና ሪፖርት ከተበተኑት ኮሚሽኖች የተለየ ውጤት አይጠበቅም ብሏል። ለአካታች፣ አሳታፊና ተዓማኒ የሽግግር ሂደትና ተቀባይነት ያለው ህጋዊ የፍትህ ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ እንዲተገበርና ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ አቅርቧል።
- " የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና የዲሞክራሲ አጋሮች እየተበረታቱ ሳይሆን እየተሸማቀቁ ነው " ብሏል።
- " ዕለት ከዕለት የገዥው ብልጽግና አምባገነዊነትና አማቂነት እየጎላና እየተበራከተ ነው የመጣው " ያለ ሲሆን " የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ መጥቶ ተኮማትሯል። " ሲል ገልጿል። " በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ነፃነትና ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና በመግለጫዎች እንዲወሰን ተደርጓል " ሲልም ወቅሷል። " ሠላማዊ ሠልፍ ለመጥራት መዘጋጀት፣ ህገመንግሥት የሚፈቅደው መብት ሆኖ ሳለ- ያሳስራል፣ ለከፋም ጉዳት ይዳርጋል " ብሏል።
- " በገዥው የብልጽግና ፓርቲ ሹመኞች፣ ሃላፊነት በጎደለው ፍላጎትና ውሳኔ፣ በዋና ከተማችን ‹የኮርደር ልማት› በሚል የተጀመረው የመኖሪያና ንግድ ቤቶችንና ህንጻዎችን በማፍረስ ህዝብን በማፈናቀል ለከፍተኛ ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቀውስና ለጎዳና ተዳዳሪነት አጋልጧል " ብሏል። " ይህ ኅብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ከፖለቲካ ገለልተኛ ሙያዊ ጥናት ውጪ የሚደረገው ዜጋ አሰቃይ እርምጃ ወደ ክልል ከተሞች እየተዛመተና ሥቃዩን በመላ አገሪቱ እያዳረሰ ነው " ሲል ተቃውሟል። " ግቡ ለቀጣዩ ምርጫ የቅስቀሳ ግብዓት ነው " ብሏል። " የኮርደር ልማት በገዥዎች የረጅም ጊዜ አብሮነታቸውና ማኅበረ-ኢኮኖሚ ቁርኝታቸው የማይፈለገውን የማኅበረሰብ አባላት ማፈናቀልና መበተን ስለሆነ ሥራው ያለምንም ተጠያቂነት፣ በማናለብኝነት መንፈስ፣ በጥድፊያ እየተካሄደ ነው " ሲል ወቅሷል።
- " በርካታ የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ወደ ጎን ተብለዋል። ውዱን የአገርና ህዝብ ሃብት ከመንገድ ስፋትና፣ ህንጻ መቀባትና ሣር መትከል አልፎ ለቤተመንግሥት ግንባታ ጭምር እየዋለ መሆኑ ለዜጎች ህይወትና ኑሮ ደንታ ማጣት- ኢሰብዐዊነት ነው " ሲል ወቅሷል።
ኮከሱን መንግስትን " ጦርነትን እንደ መግዣ ሥልቱ እየተጠቀመ ነው " በሚል ወቅሶ እንዲህ አይነት መንግሥት " የሠላምና ልማት ጠንቅ ነው " ብሏል።
" አገሪቱ ከገባችበትና ካለችበት እጅግ አሳሳቢና ፖለቲካዊ ማህበረ-ኢኮኖሚ ምስቅልቅል እንድትወጣ፣ በየአቅጣጫው ከሚሰማውና ህዝባዊ የህልውና ጥያቄ፣ ከሚታየው የትጥቅ ትግል መፍትሄ ለመስጠት ተኩስ ቆሞ ሃቀኛ፣ ሁሉን-አቀፍ፣ አሳታፊ፣ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ ለማውረድ ተዓማኒ ውይይት/ምክክርና ድርድር እንዲደረግ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia