“በሌሎች ተብሎ የተገለጸው ቃጠሎ በምርመራው ያልተደረሰባቸው ማለት ነው” - ፌደራል ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ በ2017 ዓ/ም በ6 ወራት በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የተከሰቱ 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎችን መንስኤ “በፎረንሲክ ምርመራ” ማጣራቱን የሚገልጽ ውጤት ይፋ አድርጓል።
50 ቃጠሎዎች በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ፣ 11 በመካኒካል ችግር ፣ 10 ሆን ተብሎ ፣ 17 በቸልተኝነት፣ 15 በሌሎች ምክያቶች የደረሱ መሆናቸውን ገልጿል።
አጠቃላይ ባለፉት 6 ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 96 እና በክልሎች ደግሞ 7 በአጠቃላይ እንደ ሀገር 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ደርሰው የአደጋ መንስኤዎችን ማጣራቱን ጨምሮ ገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር የተከሰተ አደጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።
በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤት፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1965 ንግድ ቤቶች፣ በ6 ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ አመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ 15 ቃጠሎ በሌሎች ምክንያቶች እንደተከሰቱ ገልጿችኋል፤ ሌሎች ሲባል ምንድን ናቸው? የሚልና ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለፌደራል ፓሊስ አቅርቧል።
በፌደራል ፓሊስ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀይላን አብዲ፣ “በሌሎች ተብሎ የተገለጸው ቃጠሎ ስቲል በምርመራው ያልተደረሰባቸው ማለት ነው” ሲሉ መልሰዋል።
“ለምሳሌ እሳት አደጋ ይደርስና ከዛ ቦታ ላይ ለማስረጃ የሚሆኑ ኢቪደንሶችን፣ ማስረጃዎችን ማጥፋት፣ ቁሳቁሶችን ጠራርጎ ማውጣት እሳቱ ከጠፋ በኋላ። አሁን ይሄ አይነት ቃጠሎ በምን እንደተፈጠረ አይታወቅም” ብለዋል።
“ሆን ተብሎ በሰው” የደረሱ 10 ቃጠሎች በፈጸሙ እርምጃ ተወስዷባቸዋል? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ የሰጡን ምላሽ፣ ደግሞ፣ “ተጠያቄ ይሆናሉ ተጣርቶ። ይሄ ፕሮሰስ ላይ ነው። ኢቪደንሱ ተገኝቷል። በዚህ ኢቪደንስ መሰረት ይጠየቃሉ” የሚል ነው።
“ለምሳሌ አንድ ሰው ‘ራሱን አቃጥሎ ነው የሞተው’ ብሎ ሰው ቢገድል ኢቪደንሱ ሲገኝ፣ ግድያው በሰው መሆኑ ሲረጋገጥ ለግድያውም ተጠያቂ ነው የሚሆነው” ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን ያክል ሰዎች ናቸው? “ሆን” ብለው በማቃጠል የተጠረጠሩት? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ኃላፊው፣ “አሁን ስለእሳቱ ብቻ ነው መግለጽ የፈለግነው። ወደፊት ይገለጻል” ከማለት ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
በቸልተኝነት የደረሰ ቃጠሎ ማለትስ ምን ማለት ነው? ለሚለው ጥያቄም፣ “ለምሳሌ ሻማ አቀጣጥሎ ሳያጠፋ ቢተኛ፣ ተሽከርካሪ ላይ ጌጁ ሙቀት መጨመሩን እያሳዬ አሽከርካሪው እርምጃ ካልወሰደ በቸልተኝነት ይቃጠላል እንደዛ ማለት ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“በቸልተኝነት ማለት ባልተገባ ሁኔታ ወይም በነግሊጀንስ ማለት ነው” ነው ያሉት አቶ ጀይሉ።
ደረሱ በተባሉት 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ምን ያክል ንብረት እንደወመስ ታውቋል? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ፣ “እሱ ሌላ ነው። አሁን ዋናው ነገር በምን ተቃጠለ የሚለው ነው የተጣራው” ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia