" እገዳው ተነስቷል " - ኢሰመኮ
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኅዳር ወር 2017 ዓ.ም. ፦
- የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣
- የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች
- ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ 3 በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶችን በድጋሚ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከልን ማገዱ ይታወሳል።
ኢሰመኮ ታኅሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ እገዳዎች በሲቪል ምኅዳሩ እና በማኅበር የመደራጀት መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል።
በተጨማሪም ኢሰመኮ በድርጅቶቹ እገዳ ላይ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ ያከናወነ ሲሆን የደረሰባቸውን ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ለሚመለከታቸው አካላት ማጋራቱን አመልክቷል።
ኢሰመኮ በተለይ አዲስ በተሾሙት ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በኩል ጉዳዩን በልዩ ትኩረት በመከታተል ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና እገዳ ከተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ለጉዳዩ መፍትሔ ለማስገኘት ሢሠራ እንደቆየ ጠቁሟል።
ይህ የኢሰመኮ ጥረት ውጤት በማስገኘቱ በ4ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ከዛሬ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የተነሳ በመሆኑን ኢሰመኮ አሳውቋል።
@tikvahethiopia