" ትርፍ ተሳፋሪዎች ከሌሉ አገልግሎት መስጠት ይከብደኛል " - የአዲስ አበባ የአውቶብስ አገልግሎት ድርጅት
ከወንበሮች በተጨማሪ ቆመው የሚሄዱ ተሳፋሪዎች ከሌሉ መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚቸገር የአዲስ አበባ የአውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡
በከተማዋ አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶች አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን በብዛት አሳፍረው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
" ተገልጋዮችን ከአቅም በላይ እንዲጨናነቁ ማድረግ ለምን አስፈለገ ? ተጠቃሚ ደንበኞችን የሚመጥን የአውቶብስ ቁጥር ማሟላት ያልተቻለውስ ለምንድን ነው ? " በሚል ከአሐዱ የተጠየቀው የአዲስ አበባ የአውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ምላሽ ያለው ሰጥቷል።
የድርጅቱ የቴክኒክ አገልግሎትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታምሩ ፉፋ ፤ " ይህ የተደረገው የአውቶብሶችን መለዋወጫ እና የነዳጅ ወጭን ጨምሮ ሁሉንም አስፈላጊ ወጪዎች በራሱ እንዲሸፍን የተሰጠውን መመሪያ ለመተግበር በወንበር ልክ ብቻ አሳፍሮ መንቀሳቀስ የሚያዋጣ ሆኖ ባለመገኘቱ ነው " ብለዋል፡፡
በተለይ የከተማዋን ረጅም ርቀት የሚጓዙ አውቶብሶች ብዙ ተገልጋዮችን አሳፍረው የመጓዝ ግዴታ እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ታምሩ፤ " አውቶብሶቹ በሚያሳፍሩበት አካባቢ ረጃጅም ሰልፎች ቢኖሩም ቆመው የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር ግን አነስተኛ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ደንበኞች 'ቀጣይ ተረኛ አውቶቡስ ይመጣል' ብለው እንዲያምኑ የተገነባው ሀሳብ ጥሩ ቢሆንም፤ ድርጅቱን ኪሳራ ላይ የሚጥል እና አውቶብሶቹ ሲመላለሱ መያዝ ያለባቸውን ሰው ልክ ይዘው እንዳይመላለሱ አድርጓል ሲሉም አክለዋል፡፡
" በብልሽት ምክንያት የቆሙ አውቶቡሶችን መለዋወጫ አሟልቶ ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ ለማድረግ እና ሌሎችም ወጪዎችን ለመሸፈን ቆመው የሚሄዱ ደንበኞችን መጫን ግዴታ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
በተጨማሪ በመታወቂያ የሚገለገሉ ደንበኞችን አስመልክቶ አዲስ እየተሻሻለ ያለ አሰራር መኖሩ የተገለጸ ሲሆን ፤ ይህ አሰራርም መደበኛ ተጠቃሚዎች ላይ የተፈጠረውን ቅሬታ የሚፈታ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
እየተሸሻለ ያለው አስራር ተግባራዊ ሲደረግ፤ ሃሰተኛ መታወቂያዎችን የሚጠቀሙ አካላትን ለመለየት ያስችላልም ተብሏል፡፡
Credit - Ahadu / አሐዱ
@tikvahethiopia