#AddisAbaba
ነገ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ እሁድ ከሚከበረው ከ1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።
ዝግ የሚሆኑት መንጋዶች የትኞቹ ናቸው ?
➡️ ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ በተመሳሳይ ከቦሌ አካባቢ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፣
➡️ ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣
➡️ ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፣
➡️ ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ -ሳንጆሴፍ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ፣
➡️ ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ቡልጋሪያ መብራት ላይ፣
➡️ ከቅድስት ልደታ ፀበል በAU ቅዱስ ሚካኤል መታጠፊያ ወደ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ፣
➡️ ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ፣
➡️ ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት ፈረሰኛ መብራት ላይ፣
➡️ ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ፣
➡️ ከመርካቶ አካባቢ በአቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ አቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ላይ
➡️ ከፒያሳ በባንኮዲሮማ መብራት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮዲሮማ መብራት ላይ፣
➡️ ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ሴቶች አደባባይ ላይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።
አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ ነው ተብሏል።
#AddisAbabPolice
@tikvahethiopia