" ሲ3ኤአይ (C3 AI) በተባለና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ አለው ብለን ባመነው ተቋም እንደ ግለሰብ ከ200 ሺ ብር በላይ ተጭበርብረናል " - በኦንላይን ስራ የተጭበረበሩ ግለሰቦች
" ሲ3ኤአይ (C3 AI) በሚል ስም ' በትርፍ ሰዓት ኦላይን ላይ በመስራት ታተርፋላችሁ ' ተብለን ሥራ ብለን በገባንበት ተጭበርብረናል " ያሉ ቅሬታ አቅራቢዎች
- ከጅማ፣
- ከጎንደር፣
- ከአዲስ አበባ፣
- ከባህርዳር፣
- ከባሌሮቤ እና ከበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አስገብተዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ " ትሰሩታላችሁ " የተባሉት ሥራ በተዘጋጁ ድረ-ገጾች ላይ ይወጣሉ የተባሉ ሰርቨሮችን መከራየት እና የሚገኘውን ኮሚሽን መካፈል እንደነበር ገልፀዋል።
አዳዲስ አባላት በስራቸው ሲያስመዘግቡም ደረጃቸው ከፍ እያለ እንደሚሄድ ተናግረዋል።
በመጀመሪያ ብር እንደሚያስገቡ ለምሳሌ ፦ 1,000 ብር ከሆነ አትርፋችኃል ተብሎ 2,000 ብር ሆኖ እንደሚላክላቸው በዚህም እንዲያምኑ ተደርገው ብዙ ብር እንደሚልኩ ከዛ ግን ነገሩ የውሃ ሽታ እንደሆነባቸው ጠቁመዋል።
ሥራ ነው ብለው ሲሰሩበት የነበሩበት ሁለት ድረ-ገጾች ካልፈው ሰኞ ሚያዚያ 13 ቀን ከቀኑ 6 ሰዓት በኋላ ዝግትግት ብሎ መጥፋቱን ተናግረዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " ከ200 ሺህ ብር በላይ ተጭበርብረናል " ያሉ በርካታ ሰዎችን ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን #በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ " ተጨበረበርን " ያሉም አሉ።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ " ድርጅቱ " በተለያዩ ዋና ዋና የሚባሉ ሚዲያዎች እንደ አሻም ቴሌቪዥን ፣ ናሁ ቴሌቪዥን ፣ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ባላገሩ ቴሌቪዥን እንዲሁም የተለያዩ በርካታ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የዘገባ ሽፋን ማግኘቱ እንድናምነው አድርጎናል ብለዋል።
" ድርጅቱ " ለመቄዶኒያ አረጋዊያን መርጃ ማኅበር ድጋፍ አድርጎ እንደነበር በእነዚህ የሚዲያ ተቋማት የዜና ሽፋን ማግኘቱን ለማወቅ ተችሏል።
በመቄዶኒያ አረጋዊያን መርጃ ማኅበር ላይ ድጋፍ ለማድረግ አስተባባሪ የነበሩትና ማርኬቲንግ ማናጀር የተባሉት አቶ ጌታቸው ጫኔ ናቸው።
አቶ ጌታቸውንም ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዋል።
በምላሻቸውም " እኔ ወደ ስራ የገባሁት ከ5 ወር በፊት ነው፣ የገባሁትም እንደማንኛውም ሰው በዋትስአፕ በተላከልኝ መልዕክት የ500 ብር ገዝቸ ነው፣ ድርጅቱን በማመኔ ከግሌ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጊያለሁ፣ በዚህም ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶብኛል " ብለዋል።
አያይዘውም " የማወራቸው ሰዎች ሀገር ውስጥ የሌሉ እና በዋትስአፕ ላይ ብቻ ነው፣ በአካል ከሀገር ውስጥ ያገኘሁት ሰው የለም " ሲሉ አስረድተዋል።
የመቄዶንያው ዝግጅት እንዴት ተካሄደ ?
" ድርጅቱ " ቡድን ለሚሰበስቡ ሰዎች የስብሰባ እና የበጎ አድራጎት ሥራ እንዲሰሩ ገንዘብ እንደሚሰጥ ፤ በእሳቸው ቡድን ያሉ ሰዎችን በማስተባበርም እራት ማብላታቸውን ተናግረዋል።
እነዚህን ሰዎች ለማሰባሰብ እንዲሁም ድጋፍ ለማድረግ ገንዘቡ ከየት መጣ ?
አቶ ጌታቸው ለዚህ ሥራ ከውጪ በእሳቸው አካውንት 500 ሺህ ብር እንደገባላቸው በመግለጽ ከዚህ ውስጥ 160 ሺ ብር ወጪ በማድረግ ለአረጋውያኑ ግብዣ እንዳደረጉ፤ ቀሪው ገንዘብ ከቡድናቸው ጋር አዲስ አበባ ላላቸው ስብሰባ የምግብ፤ ትራንስፖርት እና ማደሪያ ወጪ እንደተደረገ ተናግረዋል።
እናንተ የተቋሙ አመራሮች ናችሁ ?
አቶ ጌታቸው ፥ " እኛ ሌሎችን ለማገዝ፤ መረጃ ለመስጠት፤ ለማስተባበር ፊት ለፊት ስለወጣን እንጂ የተለየ ያገኘነው ወይም ሰዎች በእኛ በግል አካውንት ያስገቡት ብር የለም " ሲሉ የእነሱ ሥራ ማስተባበር እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ በርካታ ቅሬታ አቅራቢዎች " የተጭበረበርንበት መንገድ ይለያል " ብለው የገለጹ ሲሆን ይህንም እንዴት እንደሆነ አስረድተዋል።
ምን አሉ ?
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ሲስሪ ኤአይ ቴክኖሎጂ / SEE THREE AI TECHNOLOGY PLC በሚል ስም እንዲሁም በኢ ትሬድ ማረጋገጫ 0093931744 ቲን ቁጥር መኖሩ።
- በቅርቡ በስካይ ላይት ሆቴል ትልቅ ዝግጅት ለማድረግ ታቅዶ፤ የአዳራሽ ክፍያ ከተስማሙት 1 ሚሊዮን ብር ግማሹን መክፈሉን የባንክ ስቴትመንትና የሆቴሉን ደረሰኝ በግሩፖች ላይ መጋራቱ፤ በዚህም ብዙዎች ተስፋ እንዲያደርጉ መደረጉ።
- ገንዘቡ የሚገባው ሆነ ክፍያ የሚፈጸመው በአንድ ሂሳብ ቁጥር 1000687201888 በሚል መሆኑ።
እንድናምን አድርጎናል ሲሉ ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው አካላት ለማጣራት ጥረት አድርጓል።
➡️ በንግድ ፈቃዱ ላይ በሥራ አስኪያጅነት የተጠቀሰውን ግለሰብ ለማግኘት ቢጥርም አልተሳካም ፤ ስልክ አይሰራም ቴሌግራም ላይም አይመልስም።
➡️ ንግድ ፈቃዱን በተመለከተ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና ገቢዎች ቢሮ በኩል ለማጣራት ጥረት እያደረግን ነው።
➡️ የባንክ አካውንቱን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉዳዩን ያሳወቀ ሲሆን የባንኩን ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።
➡️ ስካይ ላይት ሆቴል ተዘጋጅቷል ለተባለው ዝግጅት በእርግጥም ለሆቴሉ የተከፈለ ነገር መኖሩንና ዝግጅቱ መያዙን ለማጣራት ጥያቄ አቅርበናል።
የብዙዎች ጥያቄ ገንዘብ ሲወጣ ሲገባ የነበረበት አካውንት በአስቸኳይ ይታገድልን የሚል ሲሆን የሚመለከተው የህግ አካልም አስፈላጊውን ማጣራት ያድርግልን ሲሉ ጠይቀዋል።
🔴ቅሬታ አቅራቢዎች ላነሱት ጉዳይ " ምላሽ እሰጣለሁ ፤ አብራራለሁ ፥ አስረዳለሁ " የሚል የትኛውም ወገን ከመጣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስተናግዳል።
#እንድታውቁት ፦ C3 AI የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ የሚሰራ ነው። ነገር ግን ባደረግነው ማጣራት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በዚህ ተቋም ስም ገንዘብ የሚሰበስቡ አሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia