ቢጂአይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመርቆ ለማህብረሰቡ አስረከበ
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ ያስገነባውን አባ ገዳ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የምረቃ ስነ-ስርዓት በዛሬው እለት አስመርቋል።
ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ያለቀው በ 6ወራት ጊዜ ውስጥ ሲሆን ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት መጀመራቸው ተነግሯል።
600 ህፃናት ተማሪዎችን በፈረቃ ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው ይህ ትምህርት ቤት 9 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት የቢጂአይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሄርቬ ሚልሃድ ተናግረዋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማው እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ባለድርሻ አካላት ትምህርት ቤቱ እንደ አጥር ያሉ አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉለት ጠይቀዋል።
ቢጂአይ በማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ በሰራው ስራ በዘንድሮው አመት ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በትምህርት፣ ጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ላይ ማውጣቱን የ
ዋና ስራ አስፈፃሚው ጠቅሰዋል።
ኩባንያው ዛሬ በባቱ ከተማ ያስመረቀውን ፕሮጀከት ጨምሮ በሐዋሳ፤ በጕራጌ ዞን ዘቢዳር እና በኮምቦልቻ ባሉ ከተሞች የትምህርት መሰረተ ልማትን በመገባት ለነዋሪዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
በዘቢዳርና በኮምቦልቻ ያሉ ት/ቤት ግንባታዎች በቅርቡ ለማህበረሰቡ እንደሚያስረክብም ኩባንያው አሳውቋል።
@tikvahethmagazine