#Hawassa
በሀዋሳ ከተማ የተጀመረዉ ተሽከሪካዎችን በአይነትና በታርጋ ለይቶ በተወሰኑ ማደያዎች የመደለደሉ ስራ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ ለጥቁር ገበያ ወይንም ለሕገወጥ ግብይት ዳርጎናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል።
የሞተር ሳይክል እና የሚንባስ ታክሲ አሽከሪካሪ ቅሬታ አቅራቢዎች የተሽከርካሪ ምደባ ሥርዓቱ ችግር ፈቺ አለመሆኑን አስረድተዋል።
"ከማለዳ ጀምሮ ተሰልፈን ዉለን በተለያዩ ምክንቶች ሳንቀዳ የምንመለስበት አጋጣሚ ስላለ ተሰልፎ ከመዋል ይልቅ አዝማሚያዎችን አይተን በየመንገድ ዳሩ በዉሃ ሃይላዶች በ70እና 80ብር ልዩነት ለመግዛት እንገደዳለን" ሲሉ ነው የገለጹት።
አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎችና በየዕለቱ ከንግድና ገበያ ልማት መስሪ ቤቶች የሚመደቡ ባለመያዎች ጭምር የዚሁ ችግር ተባባሪዎች ናቸዉ ሲሉ አሽከሪካሪዎቹ ይናገራሉ።
በተጨማሪም ተራ ጠብቀዉ ከሚሰለፉት ባልተናነሰ በሰበብ አስባቡ ያለተራቸዉ እየገቡ የሚቀዱ ተሽከሪካሪዎች በህወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ለሚሸጡ ቤንዚኖች አቀባዮች ናቸዉ ብለዉ እንደሚያምኑም ተናግረዋል።
ስምንትና ሰባት ሊትር ለመቅዳት ብዙ ጊዜ ተሰልፈን እናድራለን የሚሉት የባጃጅ አሽከሪካሪዎች ይህ በመሸሽና ስራ ፈቶ ከመዋል አብዛኛው የባጃጅና ኪዩት አሽከርካሪ ከጥቁር ገበያ ከመደበኛው እጥፍ በሚባል ዋጋ በመገዛት በታሪፍ ላይ ያልተገባ ጭማሪ ለማድረግ እንደሚገደዱ ተናግረዋል።
በመንግስት ሞተር ሣይክልና መኪኖች ጭምር ለጥቁር ገበያዉ አሳላፊ ሆነዉ የሚሰሩ አካላት እንዳሉ በግልፅ እናያለን የሚሉት አሽከርካሪዎቹ በየማደያዉ አከባቢ የሚስተዋሉ መረባበሾችን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ሄደዉ የሚቀዱባቸዉን ቦታዎች ጭምር እንደሚጠቁሙ ገልፀዋል።
በከተማዋ ረጃጅም የቤንዝን ሰልፎች እንዲስተዋሉና የጥቁር ገበያዉ እንዲስፋፋ #የአቅርቦት_እጥረት ዋነኛ ምክንያት ነዉ ሲል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ይገልጻል።
አክሎም ለመፍትሔ ተብለው በየጊዜዉ የሚወሰዱ እርምጃዎች እየተለመዱ ሲመጡ ሌላ ችግር ይዘዉ መምጣታቸዉን በማጠን በየጊዜው አዳዲስ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነዉ ሲል ገልጿል።
የምደባ ስርዓቱ በየማደያዉ የቀረበዉን ቤንዚን በአግባቡ ለመጠቀም እንጂ ለጥቁር ገበያው ምክንያት ሆኗል የሚል ቅሬታ ግን እስካሁን ቀርቦላቸዉ እንደማያውቅ መምሪያው ገልጿል።
በቀጣይ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ በማሰባሰብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት እንደሚጥርም አስታውቋል።
📌 ይህ ዘገባ ከመጠናቀሩ ሁለት ቀናት አስቀድሞ ህዳር የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ችሎት ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethmagazine