የሎተሪ ዕድለኛው የደረሰውን መኪና መሸጥ ይፈልጋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲወጣ ባዘጋጀው የቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ የሁለተኛ ዕጣ ዕድለኛ በመሆን የ1500 ሲ.ሲ የቤት አውቶሞቢል መኪና እድለኛ እንደሆኑ ተነግሯቸው ነበር።
ታዲያ የቤት ኦቶሞቢል ቁልፍ በእጃቸው ይዘው ፎቶ ቢነሱም፥ ተሽከርካሪው ግን በእጃቸው እንዳልገባ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሸምሱ በቶቶቦላ ሎተሪ እጣ እድለኛ የሆነበትን ኦቶሞቢል ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ተረክበዋል።
ታዲያ አሁን ላይ እድለኛው መኪናውን መሸጥ እንደሚፈልግ ገልጿል። መኪናውን መሸጥ የፈለገበት ምክንያትም ወደ ገንዘብ ተቀይረው ጥሩ ቢዝነስ ለመጀመር መሆኑን ገልጿል።
መረጃውን ቅሬታውን ተከታትሎ ሲዘግብ ከነበረው ዳራሮ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽንን ማግኘታችንን እንገልጻለን።
@tikvahethmagazine