የ11 ዓመት ህፃንን አሰገድዶ የደፈረ ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ
በሰላምበር ከተማ አስተዳዳር ዳንባዬ ቀበሌ የ11 ዓመት ህፃንን አሰገድዶ የደፈረ ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የሰላምበር ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
አቶ ካስትሮ ካባሎ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይ የሆነችውን ህፃን ሐሴት አዲማሱን በቀን 06/10/2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3:30 አካባቢ በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ በማስገድድ የግብረ ሥጋ ድፈረት ወንጀል መፈፀሙ ተገልጿል።
በዚህም ግለሰቡ የኢፌዴሪ የወንጀለኛ መቅጫ አንቀፅ 627 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ጥፋተኛ መባሉን የጋሞ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ተከሳሹ ጥፋተኛ የተባለው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 627/1/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ሲሆን ወንጀሉ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 21/2006 መሰረት ደረጃ 1 እርከን 31 ነዉ።
ይህም የወንጀል እርከን ከ15 ዓመት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆኑን ህጉ የሚደነግግ ሲሆን ወንጀለኛው ከዚህ በፊት ምንም የወንጀል ሪከርድ የሌለው መሆኑ በማቅለያነት ተይዟል ተብሏል።
@tikvahethmagazine