#Ethio_Istanbul
የዲቦራ ፋውንዴሽን መሥራች አቶ አባዱላ ገመዳ የሆስፒታላችንን የኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል፤ ሥራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ለ 32 ሕፃናት የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና በነፃ ማከናወኑን እንዲሁም በተጨማሪም 4 ሺ ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና ማከናወኑን በዋና ሥራ አስፈፃሚያችን አቶ ብርሃን ተድላ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ሆስፒታላችን በቴክኖሎጂ በታገዙ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችና ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ ከ73 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ስፔሻሊስትና ሰብ-ስፔሻሊስት ባለሙያዎች በመታገዝ ዜጎቻችንን ለህክምና ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪና እንግልት ለማስቀረት እና ውጭ አገር የሚያስኬዱ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ ለመስጠት አላማው አድርጎ የተመሰረተ ነው።
አቶ አባዱላ ገመዳ ሆስፒታሉ ንፁህ፣ በሚገባ የተደራጀና በውጭ ሀገር በምንኼድበት ጊዜ የምናየው ዓይነት መሆኑን በመግለፅ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ የዲቦራ ፋውንዴሽንን ለማገዝ በውጭ ሀገር ከፍተኛ ሕክምና ከሚያስፈልጋቸው መካከል ለሁለት ሰዎች ሙሉ ወጪ በመሸፈን ሕክምና ለመስጠት ቃል ገብተዋል። በተጨማሪም ወደፊት በምናደርገው ትብብር አቅም በፈቀደ ሁሉ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።
(ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል)