ሦስት አዳዲስ ክትባቶች በያዝነው ዓመት መጨረሻ እንደሚሰጡ ተገለጸ።
በትላንትናው ዕለት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የማህጸን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት በዘመቻ መልክ መሰጠት ተጀምሯል።
ለ 5 ቀናት የሚቆየው የክትባት ዘመቻው ከ 9-14 አመት የእድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ ልጃገረዶች የሚሰጥ ሲሆን በዘመቻው 7.5 ሚሊየን ልጃገረዶችን ለመከተብ በእቅድ ተይዟል።
ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ በመፈለጋቸው በአዲስ አበባ እና በሶማሊ ክልል የክትባት ዘመቻው ያልተጀመረ ሲሆን ከ5 ቀናት በኋላ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የማህጸን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት በኢትዮጵያ መስጠት የተጀመረው ከስድስት ዓመት በፊት ቢሆንም በነበረው የክትባት እጥረት ምክንያት 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች ብቻ ክትባቱ ሲሰጥ ቆይቷል።
በአሁኑ ዘመቻ በቂ ክምችት በመኖሩ ክትባቱ ሊሰጣቸው የሚገባቸውን ከ 9 -14 አመት የእድሜ ክልል ያሉ ልጃገረዶችን የሚያካትት ይሆናል ተብሏል።
"በአሁኑ ዘመቻ አንድ ጊዜ በዘመቻ መልክ ተሰጥቶ ከዚህ በኋላ ግን እድሜያቸው 9 ዓመት ሲደርስ እንደማንኛውም ክትባት መጥተው የሚከተቡበትን መንገድ ለማመቻቸት እንዲቻል የክትባት ዘመቻው ተጀምሯል" ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የክትባት አገልግሎት ዴስክ ሃላፊ አቶ መልካሙ አያሌው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በማህጸን ጫፍ ካንሰር በየአመቱ ከ 8ሺ በላይ ሴቶች ሲያዙ ከ 5 ሺ በላይ ሴቶች ደግሞ ለሞት እንደሚዳረጉ ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ኮቪድን ጨምሮ 13 ክትባቶች በመደበኛው የክትባት መርሃ ግብር እየተሰጡ የሚገኙ ሲሆን በ 2017 መጨረሻ ላይ ሦስት ተጨማሪ አዳዲስ ክትባቶችን በመጨመር ቁጥሩን ወደ 16 ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል።
የሚጀመሩት አዳዲስ ክትባቶች
°ለህጻናት የሚሰጥ የወባ መከላከያ ክትባት
°ህጻናት እንደተወለዱ በ 24 ሰዓት ውስጥ የሚወስዱት የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት እና
° የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባት ናቸው።
@tikvahethmagazine