#ጥቆማ
የ2017/2024 ዓለምአቀፍ የንግድ ስራ ፈጠራ ሳምንት ህዳር 9 – 17, 2017 ዓ.ም ‹ኢንተርፕሪነርሽፕ ለሁሉም › በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፉን የአንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር በህዳር ወር የግንዛቤ ማስጨበጫና መረጃ ሰጭ በሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ሆኖ የሚከበር ይሆናል፡፡
ቅዳሜ ህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሰት የሥራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት የሙሉ ቀን የፓናል ውይይትና የመክክር መድረክ ይካሄዳል፡፡
እሁድ ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽት ከ12 ፡ 00 (ስዓት) ጀምሮ ወሰን አካባቢ የእሳት ዳር ጨዋታ (ስቶሪ ቴሊንግ) ልምድ የማካፋል ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡
በህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በአፍሪካ ህብርት አዳራሽ ከጠዋቱ ሶስት ስዓት ጀምሮ ለግማሽን ቀን የአፍሪካ ተወካዩች በተገኙበት ስለኢንተርፕረነርሽፕ እና ተያያዥ የቴክኒክና ሙያ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ይደረጋል፡፡
በመጨረሻም የፕሮግራሙ ማጠቃለያ በኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከስዓት በኃላ 8፡00 ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው የስነምህዳሩ ተዋንያን በተገኙበት የእውቅና ፕሮግራም እና ማጠቃለያ ይካሂዳል፡፡
በዘርፉ ያሉ ተዋንያን በዝግጅቶቹ እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።
@tikvahethmagazine