ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ ልትጀምር ነው
ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል 100 ሜጋ ዋት ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ታንዛኒያ ለመሸጥ ማቀዷን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
ሽያጩ የሚጀመረው ሁለቱ አገራት የድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ሀይል ንግድን ለማካሄድ የሚያስችለውን ስምምነት ከጨረሱ በኋላ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የሃይል ሽያጭ መጠኑ ሁለቱ አገራት ከተነጋገሩ በኃላ ሊከለስ እንደሚችል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ሞገስ መኮነን መናገራቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ኬንያ እና ታንዛኒያ ኃይል ለማስተላለፍ ከፍተኛ የቮልቴጅ መስመሮችን መጠቀም የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ሲገለጽ ስምምነቱ በኬንያ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እንዲጸድቅ እየተጠበቀ ነው፡፡
ስምምነቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ኢትዮጵያ በወላይታ ሶዶ አቅጣጫ በተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር፤ በኬንያ ሱስዋ በኩል ወደ ሰሜን ታንዛኒያ የኃይል ሽያጭ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
@TikvahethMagazine