በጥምቀት በዓል ስርቆት በፈጸሙ ተከሳሾች የፍርድ ውሳኔ ተላለፈባቸው።
በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በጊዜያዊነት በተቋቋሙት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ምርመራ ማካሄዱን በተወሰኑት ላይም የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
የቅጣት ውሳኔው እዚያው በቦታው ላይ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ካጠናቀቀና አቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተ በኋላ፥ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በበዓሉ ስፍራ በተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት መወሰኑ ነው የገለጸው።
ለአብነትም አበበ ቢቂላ ስታዲዮም በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ከሁለት ግለሰቦች ኪስ ውስጥ 2 ሞባይል ስልኮችን ሰርቆ እጅ ከፍንጅ በተያዘው ብርሃኑ አበበ የተባለ ተጠርጣሪ በ2 አመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።
በተመሳሳይ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ በነበረው የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራ ከአንዲት ግለሰብ ላይ ሞባይል ስልክ ሰርቆ በድጋሚ ከሌላ ሰው ላይ ሊሰርቅ ሲሞክር የነበረው ታዘበው ሞላ የተባለው ይኸው ተከሳሽ ክሱ ታይቶ በ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ፈርዶበታል።
በጃን ሜዳ በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ሥነ-ስርዓት ላይ ደግሞ ወንጀል የፈፀሙ 21 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ ይገኛል ተብሏል፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ የወንጀል ፍሬ የሆኑ እና የተለያየ አይነት ሞዴል ያላቸው ዘጠኝ ሞባይል ስልኮች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡
@tikvahethmagazine