"በጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በመቸገራቸን ትልቅ ፈተና ውስጥ ነን" የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት
ከሌሎች ወሮች በተለየ መልኩ በየዓመቱ ጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚቸገር የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በአገልግሎቱ የደም ለጋሾች መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ዶክተር መላሽ ገላው በ2016 አ.ም እንደ ሀገር 349 ሺ ዩኒት ደም መሰብሰቡን፤ ይህም የእቅዱን 82% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በተያዘው ዓመት 6 ወራት እንደሀገር 217 ሺ ዩኒት ደም በላይ መሰብሰቡን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 55 ሺ 300 ዩኒት ደም ከአዲስ አበባ ከተማ የተሰበሰበ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የጥር ወር ፈተና
ዶክተር መላሽ፥ ''በተለይ ከሌሎች ወሮች በተለየ መልኩ በየዓመቱ ጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በተለያዩ ምክንያቶች ስለምንቸገር ትልቅ ፈተና ውስጥ ነን '' ሲሉ ወቅቱ ደም ለመሰብሰብ አስቸጋሪ መሆኑን ያነሳሉ።
ለማሳያም፤ "ተማሪዎች ፈተና የሚፈተኑበትና ዕረፍት የሚሆኑበት ጊዜ መሆኑን፤ ስለሆነ ባለፍቱ 2 ሳምንታት ውስጥ ከትምህርት ቤቶች ምንም አይንት ደም አላገኘንም" ያሉት ዶ/ር መላሽ የበዓላት መደራረብም ተጽዕኖ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ከበዓላት ጋር ተያይዞሞ በተለያዩ ምክንያቶች ደም መሰብሰቢያ ቦታዎች ፈቃድ ባለማግኘታቸው በጥር ወር ከታሰበው 60% በታች የሆነውን ብቻ ማሳካት መቻላቸውን ነው የገለጹት።
ያለውን ክፍተት ለመሙላትም ከበጎፈቃደኞች ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው "ሚዲያዎችን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ደም ለመሰብሰብ እየሞከርን ነው "ብለዋል።
አክለውም "ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና እሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን የኮሪደር ልማቱን በሚመጥን መልኩ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ የደም መሰብሰቢያ ቦታዎችን ለማግኘት እየሰራን ነው" ሲሉ ነግረውናል።
በክልሎች የደም የመሰብሰብ ምጣኔን ለመጨመር ባለሙያዎችን ወደ ክልሎች በመላክ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያረጉ እየተደረገ ነው ያሉን ዶ/ር መላሽ፥ "የየክልሎች ጤና ቢሮዎች ደም ማሰባሰብ ላይ ትኩረት ሰጠው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል '' ሲሉ ገልፀዋል።
የሚመጡት ወራቶች ከዚህ የበለጠ የደም መሰብሰባችን ምጣኔ ሊቀንስ እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን ለዚህም ማህበረሰቡ ደም በመለገስ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine