200 ካሬ በሆነ የእርሻ መሬት ላይ የካናቢስ ዕጽ ሲያመርቱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ላንቴ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በእርሻ ማሳ ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ሲያመርቱ የነበሩ ግለሰቦችን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊሲ መምሪያ አስታዉቋል።
የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃና ኢንተለጀንስ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ሳጅን ሙሉቀን ጋሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ተጠርጣሪዎቹ አቶ በላቸው በረሱ እና እልኩ ደፋር የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ እጹን ሲያመርቱ የተገኙትም በጎርካ ወረዳ ጎልቤ ቀበሌ ላንቴ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ተጠርጣሪዎቹ፥ 10 በ 20 በሆነ የእርሻ መሬት ላይ ዕፁን ሲያመርቱ ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ አስፈላጊዉን ክትትል በማድረግ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ማዋላቸዉንም ተናግረዋል።
ከምርመራና ክስ ሂደቱ ጎን ለጎን ከግሌሰቦቹ ጋር በዕፅ ዝዉዉሩም ሆነ የአቅርቦት ተስስር ግንኘነት ያላቸዉን ሰዎች የመከታተልና በሕብረተሰቡም ዘንድ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ በበኩላቸው አንድ ኩንታል ካናብስ በቲቢኤስ ሞተር ሳይክል ተጭኖ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቅሰዋል።
እስከ እርሻ ማሣ በተደረገው ኦፕሬሽንም '' አራት ክምር በአጠቃላይ እስከ 120 ኪ.ግ የሚመዘን ካናብስ አደገኛ ዕፅ በመያዝ የምርመራ ሂደት እየተጣራ '' መሆኑን አብራርተዋል።
የፌደራል ፖሊስ መረጃና ደህንነት፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንድሁም የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃና ኢንቴለጄንስ ዲቪዥን በጋራ በመቀናጀት አደንዛዥ ዕፁን ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ኮማንደር አሸናፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
ይህ ህገ ወጥ ተግባር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ክሳራ የሚያስከትልና ወጣቶችን ወደ አላስፈላግ ወንጀል የሚመራ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንድያደርግ አሳስበዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine