በጂንካ ከተማ አንዲት እናት 4 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች።
° ''ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም ፤እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ'' ወላጅ አባት
በጂንካ ከተማ በትላንትናው ዕለት የካቲት 18 አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታውቆ ነበር።
እናት ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን በሆስፒታሉ መውለዷን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሚስጥሩ ሀምዴክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ህጻናቱ አሁን በምን ጤንነት ላይ ይገኛሉ ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ከአራቱ አንዷ ጨቅላ ትንሽ ኪሎዋ አነስ ስላል በአይ.ሲ ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከመሆኑ ወጭ ሌሎች ህፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ ናቸው ሲሉ ነግረውናል።
ዶ/ር ሚሥጢሩ አክለውም፥ እናትም በጥሩ ጤንነት ላይ ናት እንደምትገኝ እና ልጆቿን በኦፕራሲዮን በመወልዷ በትንሹ እስከ 3 ቀን በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላት እንደምትቆይ አስረድተዋል።
ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ እንዲህ አይነት ነገር ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑንም የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
የልጆቹ ወላጅ አባት ምን አሉ?
የእነዚህ አራት ልጆች አባት አቶ አንጁሎ አዲስ ይባላል። ባለቤቱ 4 ልጆች ስለተገላገለችበት፤ እሱም የአራት ልጆች አባት ስለሆነበት አጋጣሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ባለቤቱ አራት ልጆች እንዳረገዘች እስክትወልድ ድረስ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረና አራት ልጅ መሆኑን ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ መስማታቸውን ነው የነገረን። ይህንን ሲያቅም ደስታ እና ድንጋጤ የተቀላቀለበት ስሜት ተሰማኝ ብሏል።
ከጂንካ ራቅ ብሎ በሚገኝ በቦታ እንደሚኖሩ የገለጸው አቶ አንጁሎ፤ ወደ ጂንካ የመጡትም ለህክምና ክትትል እንደሆነ ነው የገለጸው።
በትዳራቸው እነዚህ አራት ልጆች የመጀመሪያ እንዳልዎኑ የሚናገረው አባት ከዚህ በፊት አንድ ልጅ መውለዳቸውንና እድሜውም አሁን ላይ የ4 ዓመት እንደሆነው ጠቅሷል።
"ልጆቹ ትንሽ ሰውነታቸው ቀጫጫ ከመሆኑ ውጭ ደህና ናቸው። እናታቸው ማርታ ታከለም ጡቷ ወተት እንደፈለገ አሁን ላይ አይወጣትም እንጂ እሷም ጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች" ሲል አሁን ስላሉበት ሁኔታ አስረድቶናል።
"እኔ አሁን ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም፤ እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን" ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
በተፈጥሮ በአንድ ጊዜ አራት ህጻናትን መጸነስ የሚከሰተው ከ700ሺ እርግዝናዎች በአንዱ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine