“ አርሰናል በዚህ አመት ሊጉን ያሸንፋል “ ጋሪ ኔቭል
የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል አርሰናል ከፕርሚየር ሊጉ የዋንጫ ፉክክር ወጥቷል የሚል እምነት እንደሌለው ተናግሯል።
ሊቨርፑል እና ማንችስተር ሲቲ በጥሩ አቋማቸው ላይ ናቸው ብዬ አላምንም የሚለው ጋሪ ኔቭል አርሰናል አሁንም ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑን አንስቷል።
ጋሪ ኔቭል ሲናገርም “ አርሰናል በዚህ አመት ፕርሚየር ሊጉን እንደሚያሸንፍ አሁንም አምናለሁ “ ሲል ተደምጧል።
መድፈኞቹ አሁንም ከዚህ በፊት እንዳደረጉት በሊጉ ሁለተኛ ዙር ትልቅ የማሸነፍ ግስጋሴን ሊያሳዩ እንደሚችሉ ጋሪ ኔቭል አክሎ ገልጿል።
አርሰናሎች ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል በሰባት ከማንችስተር ሲቲ ደግሞ በአምስት ነጥቦች ርቀው አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe