አርቲስት ማስተዋል በፌዴሬሽኑ ምን ትሰራለች ?
የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት ሆና የተመረጠችው አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን በቀጣይ ለመስራት ስላሰበችው እቅድ አብራርታለች።
አርቲስቷ “ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መስራች እንደመሆኗ አሁን ያለችበት ሁኔታ ጥሩ አይደለም “ ስትል የከተማዋን እግርኳስ ሁኔታ ገልፃለች።
“ ከተማዋ በዋናነት ያስፈልጋታል ብዬ የማስበው የገንዘብ ድጋፍ ነው “ ያለችው አርቲስት ማስተዋል “ ከ ኤምባሲዎች ጋር ጠንካራ ስራ በመሰራት ስፖንሰሮችና ፈንዶችን የማምጣት እቅድ አለኝ " ብላለች።
በተጨማሪም ከተለያዩ ባለሀብቶች እና ድርጅቶች ጋር በመስራት የከተማዋን እግርኳስ በገንዘብ ለማገዝ ማቀዷን አርቲስቷ ጨምራ ተናግራለች።
ምንጭ - AMN
@tikvahethsport @kidusyoftahe