ማንችስተር ዩናይትድ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀሉ !
ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል ጋር ያደረገውን የኤፌ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ በመለያ ምት 5ለ3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።
ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
የቀያይ ሴጣኖቹን ግብ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሲያስቆጥር ለአርሰናል ጋብሬል ማግሀሌስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ለእንግሊዝ ኤፌ ካፕ አራተኛ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
አርሰናል በበኩላቸው ከውድድሩ ውጪ ለመሆን ተገደዋል።
በጨዋታው ቱርካዊው የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አልታይ ባይንዲር አንድ የፍፁም ቅጣት ምት ማዳን ችሏል።
በተጨማሪም አንድ የመለያ ምት በማዳን ማንችስተር ዩናይትድ ወደቀጣዩ ዙር እንዲቀላቀል ወሳኝ ሚና ተጫውቷል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe